Friday, October 30, 2015

‘‘..... ይሄ አንዱ ተልዕኮና የትግሉ አካል ነው!’’ ታጋይ ዘመነ ካሴ

በቅዱስ ዮሃንስ

ላለፉት 24 ዓመታት የሕወሓት ቅልብ የሆኑ የፌደራል ፖሊሶችና ወታደሮች የኢትዮጵያ ህዝብን እንዳሻቸው ሲረግጡ፤ ሲበድሉና ሲጨቁኑ፤ መብቱን ለመጠየቅ አደባባይ የወጣውን ህዝብ በጠራራ ፀሃይ ያለ ርህራሄ በጥይት እየቆሉ ሲገድሉ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ የደም እንባ ሲያስነቡ አንዳች እንኳ ትንፍሽ ሊሉ ያልፈቀዱ ሰዎች ትላንት የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ወታደር በነዚሁ የስርዓቱ አስፈፃሚ ፖሊሶች ላይ እርምጃ መውሰዱን ተከትሎ ማጉረምረም ምን የሚሉት ፈሊጥ ይሆን!?! ፈጽሞ ሊገባኝ ስላልቻለ ነው። ኧረ ጎበዝ በጣም ያስተዛዝባል። በነገራችን ላይ በአሁኑ ሰዓት የሕወሓት አስፈፃሚና ጠባቂ የሆኑ የፌደራል ፖሊሶችና ወታደሮች በቁጥር ጥቂቶች መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል። ቁጥራቸው ቀላል የሚይባሉ መለዮ ለባሾች ከነፃነት ሀይሎች ጋር ሚስጥራዊ ግንኙነት ፈጥረው የውስጥ አርበኝነት ተግባራቸውን በትጋት እየፈፀሙ እንደሚገኙ መዘንጋት የለበትም።


ለማነኛውም ወደ ዋናው ነጥቤ ስገባ በደንብ ሊሰመርበት የሚገባው አብይ ጉዳይ አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ የፈፀመው አኩሪ ጀብዶ አንዱ ተልዕኮና የትግሉ አካል መሆኑ ነው። ታጋይ ዘመነ ካሴ በኢሳት እንደነገረን። አዎ! የኢትዮጵያ ህዝብን የሚበድሉ፤ የሚጨቁኑና የሚገድሉ የሕወሓት አስፈፃሚዎችን ከምድረ ገፅ ማፅዳት። አስፈፃሚ አካላት ከሌሉ የሕዝብ ጠላት የሆነው የሕወሓት አገዛዝ ሊኖር ስለማይችል። ስለዚህ በሕወሓት ጉያ ስር ተወሽቀው የኢትዮጵያ ህዝብን እየበደሉና እያስለቀሱ ላሉ ግለሰቦች ሁሉ የማንቂያ ደውሉ ተደውሏል ማለት ነው። ከወዲሁ በደንብ ሊያስቡበት ይገባል። አዎ! ግለሰቦቹ ከእኩይ ድርጊታቸው በፍጥነት ታቅበው በሕዝብ ወገን በመሰለፍ የነፃነት ትግሉ አካል መሆን የሚገባቸው አጣዳፊ ሰዓት ላይ ተደርሷል። አለያ ትርፉ የከፋ ይሆናል። ሌላው ደግሞ አንዳንድ ተቃዋሚ ነን ባዮች ያልጠራ አቋማቸውን በጊዜ ቢፈትሹና ቢያስተካክሉ መልካም ይመስለኛል። የመወላወያ ሰዓት ረፍዷል። የኢትዮጵያ ህዝብ ከተያያዘው የነፃነት ትግል ጎን መሰለፍ አለያ ከጠላትና ከጨቋኞቹ ጎራ መሰለፍ። አዎ! ትግሉ አንድ ጥግ ላይ ብቻ መርገጥ ወደ ሚጠይቅበት ወሳኝ ምዕራፍ ተሸጋግሯል!

No comments:

Post a Comment