Friday, January 30, 2015

ለህዝባዊ አመፅ ታጥቀን እንነሳ!

በቅዱስ ዮሃንስ

የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነቱን በትግሉ እንዲቀዳጅ በህብረት ለመታገል በያለበት እንደራጅ፡፡ ይህንን ለማለት ያነሳሳኝ ዋናው ጉዳይ ዘራኛውና አፋኙ ህውሀት መራሹ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በርካታ ዘግናኝ ወንጀሎችን ፈፅሟል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ያለ አግባብ ከመሬተታቸውና ከቤት ንብረታቸው መፈናቀል የዘረኛውን ስርዓት የተቃወሙትን የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ተኩስ በመክፈት በመቶ ሺህ በሚቆጠሩ ንፁሀን ላይ ግድያና የአካል ጉዳት ፈፅሟል፡፡ ብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለው የወደፊት ራዕያቸው ድቅድቅ ጨለማ ተላብሷል፡፡ የዞን 9 አባላት የመብትና ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ በማቅረባቸው እስር ቤት ተወርውረው የስነ ልቦና ጥቃት እየተፈፀመባቸው በሰቃይና በመከራ ህይወታቸውን እየመሩ ይገኛሉ፡፡ በወለጋ ክ/ሀገር በሺህ የሚቆጠር የአማራ ተወላጆች ላይ በኢህዴድ ካድሬዎች ጥቃት ደርሶባቸው ቤት ንብረታቸውን አጥተው ትቢያ ላይ ወድቀው ይገኛሉ። የጋንቤላ ተወላጆች ሌሎችም የሀገራችን ልጆች ላይ የስርዓቱን አስከፊነት በመቃወም ከሀገር ወደ ጎረቤት ሀገር በስደት የሚገኙትን ዜጎቻችንን በአፋኝ የፀጥታ ሀይል ሰራተኞች ታፍነው ከፍተኛ ድብደባና እንግልት ሰቆቃ ከተፈፀመባቸው በሁዋላ በሽብር ወንጀል ተፈርጀው ወደ ዘብጥያ ተወርውረዋል፡፡ እናት ሀገር ኢትዮጵያ ፋሽስታዊና አምባገነናዊ ወንጀል ሳቢያ ክብሯን፣ ነፃነቷን፣ ሰብአዊ መብቷን አጥታ ሊጆቿም መብት፣ ክብር ነፃነት አልባ ሆነው በወያኔ ፍርፋሪ ሆዳቸው ያበጠ በሆድ አደር ካድሬዎች እየተረገጡና እየተገረፉ እየተረገጡና እየተገረፉ ሰቆቃ ህይወት በቃሊቲ እየመሩ ይገኛሉ፡፡ ባጭሩ ከላይ እንደዘረዘርኩት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገውን ግፍና በደል ሳያበቃ በቅርበዩ ለፍትህ፣ ለመብት፣ ለዲሞክራሲ እኩልነት ብሎ የሞቀ ቤቱን ጥሎ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚታገለው ሀቀኛ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ የግንቦት 7 ዋና ፀሀፊ በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ላይ የፋሺስቱ ወያኔ መንግስት አፍኖና አግቶ ይገኛል፡፡

ስለዚህ ይኼንን ከፍተኛ ታጋይ ለማስፈታት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የፆታ የዘር የሃይማኖት ልዩነት ሳይኖረን በጋራ የተባበረ የጋራ ድምፃችንን ለዓለም አቀፍ ህብረተሰብ ማሳወቅ ግዴታን ሲሆን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ህውሀት ለመደምሰስ ቆርጠን ባንድ ላይ በተባበረ ክንድ የህወሃትት አፓርታይድ ስርአትን ለመደምሰስ እንደራጅ ጊዜው አሁን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነቱን በትግሉ እንዲቀዳጅ በጋራ ለመታገል በያለንበት እንደራጅ በጋራ እንነሳ! አገራችንን ከአውሬዎች ለማዳን ሁለገብ ትግል እናፋፍም የአንዳርጋቸው ፅጌን ራዕይ ለማሳካት ሁላችንም በቆራጥነት ለትግል እንነሳ፡፡

ድል የህዝብ ነው!

No comments:

Post a Comment