Tuesday, January 13, 2015

ጥንቅር በአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ዙሪያ


በቅዱስ ዮሃንስ

በግንቦት 7 የፍትህ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እና በኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የተደረገው ውህደት የትጥቅ ትግሉን ከዳር ሊያደርስ የሚችል ሐይል ይፈጥራል ሲሉ ኢትዮጵያውያን እምነታቸንና ድጋፋቸውን ገለጹ

ዘረኛውንና ከፋፋዩን የወያኔ አገዛዝን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ለማስወገድ በተለያዩ መንገዶች ሲታገሉ የቆዩት ሁለቱ ድርጅቶች ግንቦት 7 እና የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር በጥር 2 ቀን 2007 አ.ም በኤርትራ በተካሄደው ስምምነት ውህደቱ በደማቅ ስነስርአት መፈጸሙን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በኤርትራ ከተካሄደው ጉባየ ቀደም ብሎ የግንቦት 7 ንቅናቄ በሁሉም የአለም አህጉራት ማለትም አፍሪካን ጨምሮ በአውሮፓ፤ ኤስያና ሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ አባላቶቹ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ስፊ ምክክር ማድረጉ የተመለከተ ሲሆን ውህደቱ በሁሉም አባላት ዘንድ በሙሉ ድምጽ ይሁንታን አግኝቶ ውሳኔ መተላለፉን የደረሰን መረጃ ያሳያል። በኤርትራ በተካሄደው በዚህ ታርካዊ ስምምነት ከመላው አለም የተሰባሰቡ በርካታ የድርጅቶቹን አመራሮች ጨምሮ የሌሎች ድርጅት ተወካዮች በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን በመስራች ጉባየ አባላት ይሁንታን አግኝቶ የተመሰረተው አዲሱ ድርጅት አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ (አግኤደን) የሚል መጠሪያ እንደተሰጠው ለማወቅ ተችሏል።

በኢትዮጵያ የነፃነት ትግል መድረክ ተጨባጭ ለውጥ እንደሚያመጣ የተነገረለት ይህ ውህደት ከፋሺስታዊው አጋዘዝ ጋር በመሬት ላይ ለሚደረገው የትጥቅ ትግል ማርሽ ቀያሪ መሆኑ ተነግሯል። በጉባየው የተገኙት የአርበኞች ግንባር ሊቀመንበር አርበኛው መኣዛ ጌጡ የውህዱን እውን መሆንና አገራዊ ጠቀሜታውን ያጎላ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በተናጥል እየተደረገ ያለው ትግል ስንዝር ወደ ፊድ ማራመድ እንደማያስችል በመረዳት  ውህደቱ መፈጸሙን ታሪካዊና ለኢትዮጵያም ህዝብ አንድ የድል ምዕራፍ ያለው ክስተት ነው ሲሉ ገልጸውታል። የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ በበኩላቸው እንኳን ደስ ያላችሁ፤ በጉባያችሁ ላይ መገኘት ባልችልም ከዚህ በኋላ በየትኛውም እንቅስቃሴ ከጎናችሁ ታገኙኛላችሁ ሲሉ ቃል የገቡ ሲሆን ይህ ውህደቱ በስልጣን ላይ ያለውን ዘረኛውን የህወሃት አገዛዝ ማስወገድ ብቻ ሳይሆን ቀጣይ ለሚመሰረተው ዲሞክራሲያዊ ስርአት መሰረት የሚጥልም መሆን አለበት ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በጉባየው አንድነት ሃይል ነው በውህደቱ የተጀመረው ታሪካዊ ጉዞ ተጠናክሮ ይቀጥላል፤ ውህደቱ የአገራችን የትንሳኤ ምልክት ነው፤  ኢትዮጵያንና ህዝባችንን ከውርደት እንታደጋለን፤ ሞት ለፋሽስቱ ወያኔ፤ አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ጋር በመሆን የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ትግላችን በደማችን ይረጋገጣል የሚሉና ሌሎች በርካታ መፈክሮች በአዳራሹ ተስተጋብተዋል። ከእንግዲህ መለያየት የለም አንድ ሆነን ኢትዮጵያን ነፃ እናወጣለን ያለው አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ (አግኤደን) ለሌሎች በትጥቅ ትግል የተሰማሩ ድርጅቶችም እንዲቀላቀሉ ጥሪ ማቅረቡን ለማወቅ ችለናል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በትጥቅ ትግል የፋሽስቱ ወያኔ አገዛዝን በማስወገድ የኢትዮጵያን የመከራና የጨለማ ዘመን ለማክሰም የሚንቀሳቀሱት የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር እና የግንቦት 7 ንቅናቄ አንድ የመሆናቸው የብስራት ዜና ይፋ መደረጉን ተከትሎ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኖ ከመቀጠሉም በላይ በሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ድጋፍ እየተቸረው ሲሆን በተቃራኒው ውህደቱ በፋሺስቱ ወያኔ መንደር ከፍተኛ መደናገጥ መፍጠሩን የውስጥ ምንጮቻችን አመልክተዋል። የሁለቱን ድርጅቶች መዋሃድ ተከትሎ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የማህበራዊና የመወያያ መድረኮች ላይ በመገኘት ድጋፍና አጋርነታቸውን
እየገለጹ ሲሆን ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች በጋራ ሆነው መታገል ባለመቻላቸው በተናጠል ያደርጉት የነበረው የነፃነት ትግል ውጤት ባለማምጣቱ የፋሽስቱ ወያኔ አገዛዝ ለ 24 አመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ የተለያዩ ሰቆቃዎችን፤ በደሎችንና ግፎችን እየፈጸመ እንዲቀጥል እንዳስቻለው በመጠቆም ይሄ አሁን የተደረገው የሁለቱ ዲሞክራሲያዊ ሐይሎች ውህደት ይህንን ለወያኔ አገዛዝ የተመቻቸ ትግል ከቀልበሱም በላይ የነፃነት ትግሉን ያፋጥናል ሲሉ እምነታቸውን በመግለጽ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል። በተጨማሪም በአገር ቤት፤ በውጭና በጎረቤት አገር የሚኖር ማንኛውም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ከአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ (አግኤደን) ጎን በመሰለፍ የሞራል፤ የገንዘብና የሃሳብ ድጋፍ በመስጠት የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ ነፃነታ ናፋቂ ኢትዮጵያውያ ጥሪ እየቀረቡ እንደሚገኙ ለማወቅ ችለናል።

በመጨረሻም የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ በአገራችን ኢትዮጵያ የተንሰራፋውን ዘረኛና በታኝ ስርአት ከህዝብ ጫንቃ ላይ በማውረድና ሕዝባችን ከገባበት አዘቅት በማውጣት የስልጣን ባለቤት የሚሆኑበትን መንገድ ለማመቻቸት በሚደረገው የሞት ሽረት ትግል በጉጅሌው ወያኔ አገዛዝር ስር ተቀጥረው የሚያገለግሉ የመከላከያ ሰራዊት፤ የፖሊስ፤ የሚሊሻ፤ የአየር ሐይል አባላት እንዲሁም በአገዛዙ የተማረሩ በሌሎች ተቋማት ተቀጥረ የሚያገለግሉ ሰራተኞች፤ ገበሬዎች እና አገር ተረካቢ የሆነው ወጣት ትውልድ በነቂስ ወጥቶ እንዲቀላቀልና የታሪካዊው የነፃነት ትግል አካል እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።

No comments:

Post a Comment