Saturday, January 3, 2015

“ለኢትዮጵያ አንድነት በጽናት እንቆማለን” - ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የአፍሪካ አሜሪካዊ ደራሲ፣ ገጣሚ፣ የዳንስ ተወዛዋዥ፣ ተዋናይ እንዲሁም የሙዚቃ አቀንቃኝ የሆነችው ማያ አንጌሉ እንዲህ በማለት አውጃ ነበር፣ “የእኛን ጀግኖች እና ጀግኒቶች ማስታወስ እና መዘከር እንዴት ያለ ጠቃሚ ነገር ነው!“እኛም እነዚህንም የሀገር ጀግኖች እና ጀግኒቶች ተራ በተራ እያነሳን እናክብራቸው፣ እናወድሳቸው ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ ሀገሪቱ ከገባችበት ማጥ ውስጥ እንድትወጣ ለማድረግ እና ነጻነት እና ዴሞክራሲ በሀገራችን እንዲሰፍን እራሳቸውን ለመስዋዕትነት ያቀረቡ የሀገር ዕንቁዎች ናቸውና፡፡

1ኛ) እስክንድር ነጋ፡ የሀገሪቱ መናገሻ ከተማ ከሆነችው ከመሀል አዲስ አበባ በስተደቡብ በኩል ወጣ ብሎ በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ከሚገኘው በአስከፊናቱ ከሚታወቀው ከመለስ ዜናዊ የቃሊቲ የማጎሪያ እስር ቤት ታስሮ በመሰቃየት ላይ ከሚገኘው ከታዋቂው እና የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ቀንዲል ከሆነው ከእስክንድር ነጋ እጅ በድብቅ በወጣ ደብዳቤው “በጽናት እቆማለሁ” በማለት ጽፏል፡፡

እስክንድር “በጽናት እቆማለሁ!” ሲል ዝም ብሎ ስለእራሱ ለመጻፍ ፈልጎ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን በማጎሪያው እስር ቤት በመሰቃየት ላይ ስላሉት የስራ ባልደረባ ጋዜጠኛ ጓደኞቹ፣ ጦማሪያን፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ስለሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ዓላማም ጭምር ነው፡፡ ከዚህም በላይ አንድ የህሊና እስረኛ ወይም ደግሞ አንድ የፖለቲካ እስረኛ ብቻውን በጽናት ሊቆም አይችልም፡፡ ብቻውንም በጽናት ቆሞ ብቻውን ውጤት ሊያመጣ እይችልም፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ኢትዮጵያ እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ ከሚጠራው የአምባገነን ወሮበላ ስብስብ መዳፍ ስር ወድቃ በመማቀቅ ላይ እያለች ለዚህ እኩይ ምግባር አራማጅ ዘረኛ ድርጅት የአደባባይ እስረኛ ምርኮኛ ሆኖ በጸጥታ ስለሚገኘው ከ90 ሚሊዮን በላይ ለሆነው ኢትዮጵያዊ/ያት ወገኑ ሁሉ መልዕክት ለማስተላለፍ አስቦ የጻፈው መሆኑን በድፍረት መናገር እችላለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ከወያኔ አምባገነን የወሮበላ ስብስብ ነጻ ለመውጣት እና እውነተኛ የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲ ለመገንባት በጽናት ትቆማለች፣ እናም ታሸንፋለች!

እ.ኤ.አ በ2014 የተጠናቀቀውን አሮጌ ዓመት ምክንያት በማድረግ የእኔን ጀግና እስክንድር ነጋን እና የእኔን ጀግኒት ርዕዮት ዓለሙን እንደዚሁም በእነርሱም ስም ሁሉንም የፕሬስ ነጻነት የህሊና እስረኛ ጀግኖች እና ጀግኒቶች ኢትዮጵያውያን/ት የህሊና እና የፖለቲካ እስረኞች፣ ለምንም ለማንም ለድርድር ለማይቀርበው ነጻነት ምርኮኛ ለሆኑ ህዝቦች፣ ለነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫ ለሚታገሉ፣ ለመልካም አስተዳደር እና ለሰብአዊ መብት መከበር ለሚታገሉ ወገኖች ሁሉ ደወል በመደወል ድምጼን ከፍ አድርጌ በመናገር አወድሳቸዋለሁ፡፡ እነርሱን በማወደስ በኩራት እንዲህ እላለሁ፣ “እንደ ፖለቲካ እስረኛነታችሁ በጽናት ቆማችኋል! እኛም በጽናት ቆመናል! ኢትዮጵያ በአምላክ ቸርነት እንደ አንድ ሀገር ብሄር በጽናት ቆማለች፡፡ የእኛን ነጻነት በመግፈፍ በባርነት እና በሁለተኛ ዜጋነት በማስቀመጥ ሲበዘብዙን እና ሲመዘብሩን ለመቆየት ዕቅድ አውጥተው የቆሙት ሆድ አምላኩ ፍጡሮች ጽናት እስከሚሟሽሽ እና ደብዛው እስከሚጠፋ ድረስ በጽናት እንቆማለን፡፡ ድል አድራጊነት ለእውነት በጽናት ለቆሙት ብቻ የተሰጠ ጸጋ ነው!“

ሸክስፒር እንዲህ በማለት ጽፈው ነበር፣ “ጥቂቶች ታላቅ ሆነው ተወልደዋል፣ ጥቂቶች ታላቅነትን በሂደት ይጎናጸፋሉ፣ ጥቂቶች ደግሞ ሁኔታዎችና ፈተና ታላቅነትን ያጎናፅፋቸዋል፡፡“ እንደዚሁም በተመሳሳይ መልኩ በእኛ ጀግኖች እና ጀግኒቶች ላይ እምነትን መጣል ይቻላል የሚል እምነት አለኝ፡፡ እንደ እስክንድር እና ርዕዮት ያሉ ዜጎች (ሁሉንም በኢትዮጵያ በማጎሪያው እስር ቤት በመማቀቅ ላይ የሚገኙትን ሌሎችን የህሊና እስረኞች ይወክላሉ) ጀግኖች እና ጀግኒቶች ናቸው ምክንያቱም በሀገሪቱ ላይ ፈታኝ የሆነ አደገኛ ሁኔታ በተፈጠረበት ጊዜ ጀግንነት በእነርሱ ላይ እምነቱን ጥሏልና፡፡ የእነርሱን የህይወት ዕጣ ፈንታ ፈልገው ባገኙበት ጊዜ እንደ አብዛኞቻችን ፊት ለፊት መጋፈጥን እርም ብለው አላስወገዱም ወይም ደግሞ እንደ ግመል ሽንት ወደኋላ አልተስፈነጠሩም፣ እንደዚሁም እንደ ተልባ ስፍር አልተንሸራተቱም፡፡ እነዚህ የጀግንነት ተምሳሌቶች የአሽከርነት ወይም የለማኝነት ባህሪን አልተላበሱም፡፡ እነዚህ የጀግንነት ቀንዲሎች ሌሎች ለከርስ ብቻ የቆሙት ሆዳሞች እንደሚያደርጉት ሁሉ ስብዕናቸውን በቤሳ ሳንቲም አልለወጡም፣ እንደሌሎች ቆርጦ ቀጥሎች አይደሉም፣ በጽናት ከቆሙለት ዓላማ አንዲት ጋት ወደኋላ አላፈገፈጉም፡፡ ላመኑበት ዓላማ በጽናት ቆመዋል፣ ይቆማሉም፡፡ በወሮበላ የጫካ አገዛዝ ነጻነት በሌለው አጥር የሌለው አስርቤት ውስጥ እየሰገዱ እና እየተንገዳወሉ ከመኖር ይልቅ ያመኑበትን ዓላማ በማራመድ ነጻነትን ይዞ በእስር ቤት መኖርን መርጠዋል፡፡

እስክንድር እና ርዕዮት በጉልበታቸው የሚንበረከኩ ቢሆን ኖሮ፣ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በማጎንበስ ቢለምኑ ኖሮ፣ ወንጀለኛ ተብለው የተፈበረኩባቸውን የሸፍጥ መሰሪ የውንጀላ ክሶች አምነው ይቅርታ ቢጠይቁ ኖሮ፣ የአሳሪዎቻቸውን እግር ቢልሱ እና ይቅርታ እንዲደረግላቸው ቢለምኑ ኖሮ ከማጎሪያው እስር ቤት ይወጡ ነበር፡፡ ከእነዚህ የዓላማ ጽናት ተምሳሌቶች ቀደም ብሎ አሁን በህይወት በሌሉት መለስ ዜናዊ እና ደቀመዝሙሮቻቸው አማካይነት ይቅርታ እየተደረገላቸው እንደወጡት በርካታ ወገኖች ሁሉ ያለምንም ችግር ከማጎሪያው እስር ቤት ይወጡ ነበር፡፡ በሸፍጥ የፍብረካ ወንጀል ክስ አሸባሪ በሚል የገዥው ወሮበላ ስብስብ የማደናገሪያ ታፔላ ተለጥፎባቸው በዝንጀሮው የይስሙላ ፍርድ ቤት 11 ዓመታት በእስራት እንዲቀጡ ተበይኖባቸው የነበሩት ጆሀን ፔርሰን እና ማርቲን ሽብዬ በተመሳሳይ መልኩ ይቅርታ ጠይቀው እንዲወጡ ነበር የተፈለገው፡፡


መለስ በጥቃት ሰለባዎቻቸው ላይ የውሸት የፍብረካ ውንጀላ የጥፋተኝነት ክስ እንዲመሰረት ካደረገ በኋላ በህዝብ ፊት በአደባባይ አምነው ይቅርታ ጠይቀው እንዲወጡ ማድረግ የመጨረሻው የውርደት መቅጫ ወይም ማሸማቀቂያ መሳሪያው ነበር፡፡ ይህንን እኩይ ድርጊት እ.ኤ.አ በ2005 የተካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ ተከስቶ በነበረው ውዝግብ ምክንያት ሰብስበው በማጎሪያው እስር ቤት አጉረዋቸው በነበሩት በደርዘን በሚቆጠሩ የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎች ላይ ተግብረውታል፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያ በሆነችው ሴት የፖለቲካ ፓርቲ መሪ በነበረችው በብርቱካን ሚደቅሳ ላይ ሁለት ጊዜ ተግብረውታል፡፡ አቶ መለስ በማጎሪያው እስር ቤቱ እየተንገዳወሉ እና እየተልፈሰፈሱ ምንም ዓይነት ወንጀል ያልሰሩትን ንጹሀን ኢትዮጵያውያን/ት እንደ ሀቀኛ ሰው ለምነው በማታለል እያግባቡ እና እያሳመኑ ለአቶ መለስ እብሪተኛ ዓላማ ይቅርታን እንዲጠይቁ እና ከማጎሪያው እስር ቤት በይቅርታ እንዲወጡ የሚያደርጉ ካድሬዎች ነበረው፡፡ አቶ መለስ የራሱን ብልሹ አመራር እና ፖሊሲን የሚቃወሙትን ንጹሀን ዜጎችን ሁሉ በህዝብ ፊት በአደባባይ ማዋረድ ትልቅ እርካታን ይሰጠው ነበር፣ በንጹሀን ዜጎች ላይ የሚፈጽሙት ይህ እኩይ ድርጊት የእርሳቸውን በሰዎች ስቃይ እና ውርደት ላይ ጮቤ የሚረግጠውን የክፋት ነብሱን በደስታ ባህር ውስጥ እንዲዋኝ ያደርገዋል፡፡ ይቅርታ ጠይቀው የውርደት ካባን ተከናንበው እንዲወጡ የሚያደርገው የገዥው አካል ዲያብሎሳዊ ባህሪ አሁንም ቢሆን ለእስክንድር እና ለርዕዮት ክፍት ሆኖ እየጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ የጽናት ተምሳሌቶች ይጸየፉታል እንጅ አይፈልጉትም፡፡ እነዚህ የጽናት ባለሟሎች ባልሰሩት ጥፋት ላይ የሚቀርብላቸውን የይቅርታ ጥያቄ መሰረተ ቢስ በማለት እንዲህ የሚል መልዕከትን ያስተላልፋሉ፣ “ለአንድ ነጻ ለሆነ ወንድ ወይም ሴት ይቅርታ ልትሰጡ አትችሉም፣ የሞራል ስብዕናውም በፍጹም የላችሁም…የእናንተን ይቅርታ ተሸክማችሁ የትም መሄድ ትችላላችሁ፣ የእናንተ በቅጥፈት እና በሸፍጥ የተሞላ ተራ እና የወረደ የወሮበሎች ይቅርታ በአፍንጫው ይውጣ…!“

በአደጋ ምክንያት አካላቸውን ማንቀሳቀስ የማይችሉት እና ሽባ የሆኑት የሆሊውድ ፊልም ዋና አዘጋጅ የነበሩት ክርስቶፈር ሪቭ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ጀግና በርካታ ውጥንቅጥ መሰናክሎች በበዙበት ወቅት እራሱን ፈልጎ የሚያገኝ እና ለፍትሀዊ ዓላማው በጽናት የሚቆም እና ለተግባራዊነቱ ያለማሰለስ የሚታገል ተራ ግለሰብ ነው፡፡“ እስክንድር፣ ርዕዮት እና ሌሎችም ዜጎች መሰናክሎች እና ችግሮች በበዙበት ወቅት እራሳቸውን ፈልገው ያገኙ እና ለፍትሀዊ ዓላማ በጽናት በመቆም ለስኬታማነታቸው በቆራጥነት ያለማወላወል የሚታገሉ ተራ ዜጎች ናቸው፡፡ ለዚህም ነው እስክንድር፣ ርዕዮት እና ሌሎች የኢትዮጵያ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ሁሉ ለእኔ ጀግኖች እና ጀግኒቶች የሆኑት፡፡ ሁሉም ለዓላማቸው እና ለዓላማዎቻቸው ስኬታማነት ብቻ በጽናት የሚታገሉ ናቸው፡፡

ድፍረት ጀግናነት እና ጀግኒነት የተዋቀሩበት የሞራል ብቃት ውጤት ነው፡፡ ይህንን ጉዳይ በማስመልከት ሮበርት ኤፍ ኬኔዲ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “የሞራል ድፍረት… በጣም ስቃይ የበዛባትን ወደ መልካም ነገር ለመለወጥ በለውጥ ፈላጊ ሰዎች አማካይነት የሚደረግ አንድ አስፈላጊ እና ዋና የጥራት መለኪያ ነገር ነው፡፡“ በእያንዳንዱ ጊዜ አንድ ሰው ለዓላማ ሲቆም፣ ወይም የሌሎችን ህይወት ለማሻሻል በጽናት ሲታገል ወይም ደግሞ ኢፍትሀዊነትን ሲዋጋ በተለያዩ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ኃይል እና ድፍረት ማዕከል በመሆን የጭቆና እና የብዝበዛ ስርዓትን መንግሎ በመጣል ለተስፋ መለምለም የመሰረት ድንጋይ የሚሆን ማዕበላዊ መልዕክት ሊያስተላልፍ/ልታስተላልፍ ይችላል/ትችላለች፡፡

እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ እና ሌሎችም ጀግኖች እና ጀግኒቶች የፖለቲካ እስረኞች እውነተኛ የሞራል ድፍረት አላቸው፡፡ እነዚህ የጽናት ቀንዲሎች ለፕሬስ ነጻነት እና ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት፣ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እና ለሰብአዊ መበቶች መከበር በጽናት ቆመዋል፡፡ ለህግ የበላይነት መርሆዎች መከበር በጽናት ቆመዋል፡፡ ከህወሀት የወሮበላ ስብስብ ቡድን በተቃራኒው ቆመዋል፡፡ እነዚህ የነጻነት ቀንዲሎች 90 ሚሊዮን ለሚሆኑት ኢትዮጵያውያን/ት ወገኖቻቸው ተስፋን የሚያለመልም ሂደትን በመተግበር በጽናት ቆመዋል፡፡

አሮጌውን ዓመት 2014ን ደወል በመደወል ስንሸኝ እና አዲሱን ዓመት 2015ን እየተቀበልን ባለንበት በአሁኑ ወቅት ሁሉም አንባቢዎቼ እስክንድር ነጋን፣ ርዕዮት ዓለሙን፣ ወብሸት ታዬን፣ አንዷለም አራጌን፣ በቀለ ገርባን፣ አቡባከር አህመድን፣ የዞን 9 ጦማሪያንን ማለትም አጥናፍ ብርሀኔን፣ ዘላለም ክብረትን፣ በፈቃዱ ኃይሉን፣ አቤል ዋቤላን፣ ማህሌት ፋንታሁንን፣ ናትናኤል ፈለቀን፣ አስማማው ኃይለጊዮርጊስን፣ ተስፋለም ወልደየስን እና ኤዶም ካሳዬን ጨምሮ በማክበር እና በማመስገኑ እረገድ ለጀግንነታቸው እውቅና እንድንሰጥ እና እንድንዘክራቸው እንድትቀላቀሉኝ በትህትና እጠይቃለሁ፡፡ እነዚህ ጀግኖች እና ጀግኒቶች በአስር ሺዎች ለሚቆጠሩ ስም የለሾች፣ የማይታወቁ ትንታጎች፣ ያልተዘመረላቸው እና ያልተሰገደላቸው ጀግኖች እና ጀግኒቶች ለእኩልነት፣ ለፍትህ እና ለክብር ሲባል በዓለም ፍጹም አስቀያሚ በሆኑት በኢትዮጵያ የማጎሪያ እስር ቤቶች በመሰቃዬት ላይ ለሚገኙት ህዝቦች ጥቂት ምሳሌዎች ብቻ ናቸው፡፡ በአስከፊነቱ በሚታወቀው እና ቃሊቲ በመባል በሚጠራው እና በሌሎች በመለስ ዜናዊ የእስረኞች የማጎሪያ ቅርንጫፍ እስር ቤቶች በመላ ኢትዮጵያ በመማቀቅ ላይ ለሚገኙ ጀግኖች እና ጀግኒቶች በሙሉ ታላቅ ክብር እሰጣቸዋለሁ፡፡ ክብር እና ሞገስ ለእነርሱ ይሁኑ!

2ኛ) ርዕዮት ዓለሙ፡ አሁን በህይወት በሌሉት በመለስ ዜናዊ የሸፍጥ ወንጀል ፍብረካ የ14 ዓመታት እስራት የተፈረደባት እና የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ቀንዲል ለሆነችው የ36 ዓመቷ ወጣት ጀግኒት ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ታላቅ ክብር አለኝ፡፡ ርዕዮት “የኢትዮጵያ እውነት ተናጋሪዋ እስረኛ” በመባል በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅናን አግኝታለች፡፡ ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ተከራካሪ ኮሚቴ/Committee to Protect Journalists ባቀረበው ዘገባ መሰረት ርዕዮት የታሰረችው የህዳሴው ግድብ እየተባለ ለሚጠራው የግድብ ግንባታ ገንዘብ ለማሰባሰብ እያደረገ ባለው የተሳሳተ አካሄድ በገዥው የፖለቲካ ፓርቲ ላይ ጠንካራ ትችትን በመሰንዘሯ እና በወቅቱ የሊቢያ መሪ የነበሩት ኮሎኔል ሙአማር ጋዳፊ እና መለስ ዜናዊ አንድ ዓይነት ተመሳስሎ ያላቸው ከአንድ ባህር የተቀዱ አምባገነን መሪዎች ናቸው ብላ እውነትን አፍርጣ በመናገሯ ነበር ብሏል፡፡

3ኛ) ውብሸት ታዬ፡ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይን አጠቃላይ በሙስና መዘፈቅ አስመልክቶ በሚያዘጋጀው ጋዜጣ ትችት በማቅረቡ እና የጋዜጠኝነት የተመልካችነት ሙያውን በመስራቱ ብቻ በአምባገነኑ የወሮበላ ስብስብ ገዥ አካል የፍብረካ ወንጀል ክስ ተመስርቶበት የ14 ዓመታት እስራት ተፈርዶበት በማጎሪያው እስር ቤት እየተሰቃዬ ያለውን ጀግና ጋዜጠኛ እና አርታኢ ውብሸት ታዬን ከልብ አከብረዋለሁ፡፡ የውብሸት ታዬ የ5 ዓመት ልጅ የፍትህ እንዲህ የሚሉት ጨዋነት የተሞላባቸው ቃላት በአዕምሮዬ ላይ ሁልጊዜ ያቃጭላሉ፣ “በማድግበት ጊዜ እንደ አባቴ ሁሉ እኔም ወደ እስር ቤት ነው የምሄደው ማለት ነው?“

4ኛ) አንዷለም አራጌ፡ ወደ ማሪያው እስር ቤት ከመጋዙ በፊት የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ኮከብ የአመራር አባል የነበረውን አንዷለም አራጌን አከብረዋለሁ፡፡ አንዷለም አራጌ ከአዲሱ የኢትዮጵያ የፖለቲካ መሪዎች፣ ጋዜጠኞች እና የሲቪል ማህበረሰብ ወጣት ዝርያ መካከል የሚመደብ ሲሆን በህዝቡ ዘንድ በስፋት የሚከበር እና ተቀባይነት ያለው የጽናት ተምሳሌት ወጣት የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባል ነው፡፡ እ.ኤ.አ እስከ ሜይ 2010 መለስ ዜናዊ 99.6 በመቶ የህዝብ ድምጽ በማግኘት ምርጫውን በድል አድራጊነት አሸንፊያለሁ በማለት ባዶ ዲስኩር እስካሰሙበት የይስሙላ ሀገር አቀፍ ምርጫ ድረስ አንዷለም አራጌ ለዴሞክራሲ መገንባት እና ለህግ የበላይነት መከበር በጽናት በመቆም ሲታገል የቆየ ትንታግ ወጣት ነው፡፡ ግልጽ በሆነ ሀሳብ በመሞላት፣ ፍጹም የሆነ ምሁራዊ አንደበትን በመላበስ፣ ሊታመን ቀርቶ ሊታሰብ በማይችል ድፍረት የተሞላበት አካሄድ፣ በአስደማሚ አንደበተ ርትዑ ንግግር፣ እንደጦር በሚወጋ አመክኗዊ አቀራረቡ፣ ጉብዝና የተመላበት አቀራረብ፣ እውነታዎችን ፈልፍሎ በማውጣት እና ለእውነት በጽናት በመቆም የመለስ ዜናዊን የቴሌቪዥን የቅድመ ምርጫ ክርክር ተሰላፊ አሽከሮች በሚያቀርባቸው በእውነት ላይ የተመሰረቱ አመክኗዊ የክርክር ጭብጦች ባዶ መሆናቸውን ያጋለጠ እና መቅኖ ያሳጣ ጀግና የፖለቲካ ሰው መሆኑን በተግባር ያረጋገጠ ወጣት ነው፡፡ በእርግጠኝነት ይኸ ዓይነት ጽናትን የተላበሰ የትግል መስመር በቀጣይነትም ሊያዝ የሚገባው ጉዳይ ነው!

5ኛ) አብርሃ ደስታ፡ ወጣቱን፣ ፍርኃት የለሹን እና ልዩ ተሰጥኦ ያለውን ኢትዮጵያዊ ጦማሪ አብርሀም ደስታን ከልብ አከብራለሁ፡፡ አሁን በቅርቡ እ.ኤ.አ ጁላይ 7/2014 ወደ ማጎሪያው እስር ቤት ከመጋዙ በፊት በእራሱ ማህበራዊ ድረገጽ በለቀቀው ጽሁፍ አብርሃ ህወሀት እራሱ ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት እንዲኖረው ጠንካራ የሆነ የክርክር ጭብጥ ሲያካሂድ ነበር፡፡ “የህወሀትን ካድሬዎች ጠላት ያለማድረግ ወይም ደግሞ በእኔ ድረገጽ እንዳይጠቀሙ ክልከላ የማላደርግበት ምክንያት የህወሀትን ምሁራዊ ክልከላ እና ኪሳራ ማወቅ ጠቃሚ እንደደሆነ ስለማምንበት ነው“ ብሎ ነበር፡፡ ሰዎች ምን ማለት እንደፈለጉ በማዳመጥ የአንድን ሰው የማሰብ እና ምክንያታዊነት ችሎታ መገምገም እንችላለን፡፡ የሚጽፉትን በማንበብ ማወቅ ይቻላል፡፡ ስለሆነም ካድሬዎቹ እንዲጽፉ እንፍቀድ፡፡ እራሳቸው ማን እና ምን እንደሆኑ እራሳቸውን እንዲገልጹ እንፍቀድ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ምን ለማለት እደፈለጉ የሚጽፉትን እናንብብላቸው፡፡ እነርሱንም በሚገባ እንወቃቸው፡፡ እነርሱን ድል ለማድረግ በመጀመሪያ እነርሱን ደህና አድርገን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ የእራስህን ጠላት ማወቅ ጠቃሚነቱ የጎላ ነው፡፡ ለዚህም ነው ይህንን ድርጊት ማድረግ ያለብን!”

6ኛ) የዞን 9 ጦማሪያን፡ የዞን 9 ወጣት ጀግኖች እና ጀግኒቶች ጦማሪያንን አከብራቸዋለሁ፣ አወድሳቸዋለሁ፡፡ እነዚህ ወጣት ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያት በኮምፒውተር የመክፈቻ ቁልፎች በመጠቀም እና ለነጻነት ያላቸውን ቀናኢነት በግልጽ በማንጸባረቃቸው እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ በሚጠራው የአሸባሪ የጨለማ ቡድን ስብስብ ልብ ውስጥ ሽብር ለቀቁበት፡፡ ይህንን ጉዳይ በማስመልከት ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ወጣት ጦማሪያኑ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳ ከእስር እንዲለቀቁ በማሳሰብ እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቷል፣ “ስራቸውን በአግባቡ የሚሰሩትን ጦማሪያን እና ጋዜጠኞችን ለማጥቃት በሚል እኩይ ምግባር የጸረ ሽብር ህግ የሚባል የማደናገሪያ ህግ አዋጅ አድርጎ በማውጣት እና እራሳቸውን በዚያ ውስጥ በመወሸቅ በንጹሀን ዜጎች ላይ እያደረሱት ባለው ጥቃት በህገ መንግስቱ እና ሀሳብን በነጻ የመግለጽ ዓለም አቀፋዊ መብት ላይ የተደረገ ዘለፋ ነው፡፡ “አጥናፍ ብርሀኔን፣ ዘላለም ክብረትን፣ በፈቃዱ ኃይሉን፣ አቤል ዋቤላን፣ ማህሌት ፋንታሁንን፣ ናትናኤል ፈለቀን፣ አስማማው ኃይለጊዮርጊስን፣ ተስፋዓለም ወልደየስን እና ኤዶም ካሳዬን ምርጥ የኢትዮጵያ ወጣት የነጻነት ታጋይ ቀንዲሎች በመሆናቸው አከብራቸዋለሁ፣ አወድሳቸዋለሁ፡፡

7ኛ) በቀለ ገርባ፣ አቡባከር አህመድ እና ሌሎች የነጻነት ታጋዮች፡ ስለእምነት ነጻነት፣ በሰላማዊ መንገድ ስለመሰብሰብ መደራጀት እንዲሁም ሀሳብን በነጻ ስለመግለጽ መብት በመናገራቸው እና በመጠየቃቸው ብቻ ወንጀል እንደሰሩ ተደርጎ እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ በሚጠራው አምባገነን የወሮበላ ስብስብ የጭቃ ጅራፍ እየተገረፉ እና እየተለበለቡ በመሰቃዬት ላይ የሚገኙትን በቀለ ገርባ፣ አቡባከር አህመድን እና ሌሎችንም ለነጻነት የሚታገሉ ትንታግ ኢትዮጵያውያን/ት ጀግኖች እና ጀግኒቶች ሁሉ ከልብ አከብራቸዋለሁ፣ አወድሳቸዋለሁ፡፡

በቀለ ገርባ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲ ንቅናቄ/Oromo Federalist Democratic Movement እየተባለ የሚጠራው የፖለቲካ ድርጅት ምክትል ሊቀመንበር እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህር የነበረ ነው፡፡ ለአሸባሪ ድርጅት ጽሁፍ አቅርቧል በሚል በቁጥጥር ስር እንዲውል ከተደረገ በኋላ የሸፍጥ ክስ ተመስርቶበት በዝንጀሮው የይስሙላ ፍርድ ቤት የ8 ዓመታት እስራት ተፈርዶበት በአሁኑ ጊዜ በማጎሪያው እስር ቤት በመማቀቅ ላይ የሚገኝ የነጻነት ታጋይ ነው፡፡ በቀለ ወያኔን ወደኋላ የሚንሸራተት እና ለማስተዳደርም አቅም ሳይኖረው በኃይል ለመግዛት ብቻ የተቀመጠ አስከፊ ድርጅት ነው የሚል ትችት ማቅረቡ የሚታወስ ነው፡፡ በህወሀት የጭቆና አገዛዝ አራት ዓይነት የዜግነት መደቦች አሉ በሚል የክርክር ጭብጡን እንዲህ አቅርቧል፣ “የመጀመሪያው የዜግነት መደብ በስልጣን ላይ ያሉትን እና መሬትን እንደ ጉልት ሽንኩርት በመቸብቸብ ላይ የሚገኙትን ያጠቃልላል፡፡ የሁለተኛው የዜግነት ምድብ ደግሞ መሬት የሚወስዱትን እና የሚቀበሉትን ያካትታል፡፡ ሶስተኛው የዜጎች ምድብ ደግሞ እነዚህ ህገወጥ ድርጊቶች ሲፈጸሙ በመታዘብ የተመልካችንትን ሚና የሚጫወተው የህብረተሰብ ክፍል ነው ይላል፡፡ የመጨረሻው እና አራተኛው የዜግነት ምድብ ደግሞ ዜጎች በዜግነታቸው ይዘውት የነበረውን አንጡራ ይዞታቸው የሆነውን መሬታቸውን እና ቤቶቻቸውን ኃይልን በመጠቀም የሚወሰዱባቸው ፍትህ ያጡ እና የነጡ ዜጎችን ያካተተ ነው፡፡“ በቀለ ገርባ በቁጥጥር ስር ውሎ ወደማጎሪያው እስር ቤት ከመጋዙ አንድ ቀን በፊት ህወሀት የሸፍጥ የአሸባሪነት ክስ በመመስረት እርሱን ለማጥቃት የጥቃት ዱለታ እያደረገ እንደሆነ ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል ተወካይ ግልጽ አድርጎ ነበር፡፡

አቡባከር አህመድ ጠንካራ የሆነ የእምነት ነጻነት መከበር ተሟጋች ታጋይ ነው፡፡ አቡባከር ጥያቄዎቹን በተቀነባበረ መልክ አዘጋጅቶ የህግ የበላይነት አክባሪ እና አቀንቀቃኛ መሆኑን እንዲህ በማለት ገልጾ ነበር፣ “ማንኛውንም አመራር አልተቃወምንም፡፡ እኛ ጥያቄ አድርገን ያቀረብነው ህገመንግስቱ ይከበር የሚል ብቻ ነው፡፡ ሁላችንም በአንድ ድምጽ እያልን ያለነው ህገመንግስቱን ማክበር አለባቸው የሚሉን አካሎች እራሳቸው በእርግጠኝነት ህገመንግስቱን ማክበር አለባቸው የሚል ነው፡፡“

ከሁሉም በላይ ስም ለሌላቸው፣ እውቅናን ላላገኙት፣ በግልጽ ላልታወቁት እና ላልተዘመረላቸው በአስር ሺዎች ለሚቆጠሩት በኢትዮጵያ ለነጻነት ልዕልና፣ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እና ለሰብአዊ መብቶች መከበር በጽናት በመቆም ለሚታገሉት ጀግኖች እና ጀግኒቶች ኢትዮጵያውያን/ት የፖለቲካ እስረኞች ታላቅ ክብር እሰጣለሁ፣ አወድሳቸዋለሁ፡፡ ለተቀደሰው ዓላማቸው በጽናት በመቆም ጋሬጣውን ሁሉ ችለው በድል አድራጊነት ነጻነትን ያቀዳጃሉ!

እስክንድር ነጋ ድፍረትን በተቀላቀለበት ሁኔታ “በጽናት እቆማለሁ” በማለት አውጇል፣

እ.ኤ.አ ሜይ 2013 ወንድሜ እና የተከበረው ጓደኛዬ እስክንድር ነጋ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጽፎ ነበር፣ “በጽናት እቆማለሁ!“ ያ ደብዳቤ በአስከፊነቱ ከሚታወቀው ከመለስ ዜናዊ የቃሊቲ የማጎሪያ እስር ቤት በድብቅ ወጥቶ ነበር፡፡

“በጽናት እቆማለሁ!“ የሚለው ደብዳቤ 7 ቀላል አንቀጾችን/paragraphs አካትቶ የያዘ ብቻ ነበር፡፡ ሆኖም ግን በውስጡ ይዞት የነበረው መልዕክት ለሰባት እንዲያውም ለሰባት ሰባ ዓመታት የሚያቆይ መልዕክትን አጠቃሎ የያዘ ነበር፡፡ “በጽናት እቆማለሁ!“ የሚለው ደብዳቤ ለፍትህ አልባው አገዛዝ አልታዘዝም፣ አላጎበድድም፣ አልሰግድም፣ ጸጥ ብዬ አልገዛም የሚል ደፋርነትን የተላበሰ ደብዳቤ ነበር፡፡ ይህ ደብዳቤ በተስፋ የተሞላ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ ስሜትን የሚኮረኩር እና የነጻነት ትግሉን ሆ ብለን እንድንቀላቀል የሚገፋፋ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ ነብያዊ መንፈስን የተላበሰ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ ከልብ ውስጥ እጅግ በጣም ዘልቆ የተጻፈ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ በስሜታዊነት ሳይሆን ጥልቀት ባለው ሁኔታ የስነ ልቦናዊ የአስተሳሰብ ሂደቶችን ባካተተ እና ምክንያታዊነትን አጉልቶ በማሳየት የተዘጋጀ የምሁራዊ አንደበት መግለጫ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ ለቤተሰቡ፣ ለባለቤቱ እና ለልጁ በቀጥታ እንዲደርስ ሆኖ የተዘጋጀ ደብዳቤ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ እንዲደርስ ተብሎ የተጻፋ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ ዲያስፖራ ሁሉ እንዲደርስ ተብሎ የተጻፈ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ ለመጭዎቹ የኢትዮጵያ ትውልዶች በታሪክ የሚቀመጥ ተብሎ የተጻፈ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ ለነጻነት እና ለሰው ልጆች ክብር ሲባል የተጻፈ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ የአንድን ሰው የነጻነት ጥያቄ ጩኸት፣ አንድ ሰው የወለደውን ልጅ ማሳደግ እንዲችል ነጻ የመሆን መብት እንዲኖረው እንዲሁም አንድ ሰው ከባለቤቱ እና ከቤተሰቡ ጋር ነጻ ሆኖ የመኖር መብት እንዳለው ለማሳወቅ የተጻፈ ነው፡፡ ይህ ድብዳቤ ስለእያንዳንዱ ዜጋ መብት እና እያንዳንዱም ዜጋ በመረጠው ሙያ ሀገሩን የማገልገል መብት እንዳለው ለማሳወቅ የተጻፈ ነው፡፡ በመጨረሻም “በጽናት እቆማለሁ!“ አንድ ነገርን በውል ያመላክታል፡ እውነትን፡፡ በጽናት መቆም ማለት ስለእውነት እና ስለእውነት ብቻ በመቆም አንድን ሰው ነጻ ያወጣል ማለት ነው፡፡

ለጥቂት ጊዜ ፍቀዱልኝ እና የሚሰማኝን የእራሴን እምነት ልግለጽ፡፡ “በጽናት እቆማለሁ!“ የሚለውን ደብዳቤ ደጋግሜ ብዙ ጊዜ አንብቤዋለሁ፡፡ በአዕምሮዬ ላይ ያጫረውን ጥርጣሬ ለማስወገድ እንዲቻል በማለት ይህንን ደብዳቤ አንብቤዋለሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ጥርጣሬዎቼ ሁሉ ሙጥጥ ጥርግ ብለው ጠፉ፡፡ ከዚያም በጽናት ቆምኩ፡፡ ወደ ነጻነት የሚወስደው መንገድ ረዥም፣ ብዙ ውጣ ውረድ ያለበት እና እጅግ በጣም አድካሚ እንደሆነ በተሰበረ ልብ ባለሁበት ወቅት ነበር ደብዳቤውን ያነበብኩት፡፡ በእኔ ፍጹም የሆነ እምነት የቱንም ያህል ለነጻነት የሚደረግ ጉዞ ረዥም አይደለም፡፡ ለሰኞ ትችቴ “ርዕስ የሚሆን ቃላትን ባጣሁበት ወቅት“ ነበር የእስክንድርን ደብዳቤ ያነበብኩት

ምንም የምለው ነገር የለም፡፡ ወዲያውኑ ሲኒየ እስከሚሞላ ድረስ በአዲስ ሀሳብ ተጥለቀለቅሁ፡፡ በየጊዜው ስለሁኔታው ባሰብኩ ቁጥር የእስክንድርን ደብዳቤ አነባለሁ እናም ስለሁኔታው አስባለሁ፡፡ የእስክንድር ድምጽ ጆሮ እያላቸው ለመስማት ለማይፈልጉት ወገኖች የጸጥታ ድምጽ ሊሆን ይችላል፡፡ ለእኔ የእርሱ ጸጥታ የሰፈነበት “በጽናት እቆማለሁ!“ የሚለው ድምጽ በየዕለቱ “በጽናት እቆማለሁ!“ “በጽናት እቆማለሁ!“ እያለ ደጋግሞ በህሊናዬ ያቃጭልብኛል፡፡

ለመሆኑ እስክንድር “በጽናት እቆማለሁ!“ ሲል ምን ማለቱ ነው? በቀላል አነጋገር በመለስ ዜናዊ የቃሊቲ የማጎሪያ እስር ቤት ቀን በቀን በእስር ላይ ሆኘ እገኛለሁ ለማለት ፈልጎ ነውን? እንደ እስክንድር፣ ርዕዮት እና ሌሎችም የነጻነት ታጋዮች የመሳሰሉ ሰዎች “በጽናት እቆማለሁ!“ ሲሉ በእርግጠኝነት ምን ለማለት ፈልገው ነው?

“በጽናት እቆማለሁ!“ በማለት እስክንድር ሲጽፍ ምን ለማለት እንደፈለገ ከእርሱ ጋር ለመነጋገር ወይም ጠይቆ ለመገንዘብ አስፈላጊ ነው ብዬ አላምንም፡፡ የእርሱ ቃላት ለእኔ ከምንም በላይ ጎላ ብለው የተጻፉ እና ግልጽ መልዕክት ማስተላለፍ የሚችሉ ናቸው፡፡ እስክንድር ማለት የፈለገው ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ በአንድ ወቅት “ጽናት” በሚል ርዕስ እንደጻፉት ለማለት ፈልጎ ነው፡፡ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ሰዎች ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግን ለምን ያህል ጊዜ ነው በጽናት የምንቆመው? ነጻነታችንን ለመቀዳጀት ምን ያህል ጊዜ መቆየት አለብን?” በማለት ይጠይቁ ነበር፡፡ (በእርግጥ ህዝቦች ከዚያ የበለጠ እንዲህ የሚል ትርጉም ያለው ጥያቄ መጠየቅ ይችሉ ነበር፣ “እንደዚህ ዓይነቱን ዋጋቢስ የሆነ ስርዓት የምንታገሰው እስከ ምን ያህል ጊዜ ነው?”) ዶ/ር ማርቲን ሉተር “ሩቅ አይሆንም” በማለት ነግረዋቸው ነበር፡፡ ለሌሎችም ጥያቄዎች አጭር እና ተገቢውን መልስ እንዲህ በማለት ሲሰጡ ነበር፡

በአሁኑ ጊዜ “ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?” የሚል ጥያቄ እንደምትጠይቁ በሚገባ እገነዘባለሁ…

በዛሬው ዕለት ከሰዓት በኋላ ልላችሁ እችላለሁ አጋጣሚው ምን ያህል አስቸጋሪ ቢሆንም፣ ሰዓቱ ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም ጊዜው በጣም ረዥም አይሆንም ምክንያቱም እውነት መሬት ከነካች በኋላ እንደገና ትነሳለችና፡፡

ምን ያህል ጊዜ? ረዥም ጊዜ አይሆንም ምክንያቱም የቱንም ዓይነት ውሸት እና ቅጥፈት ለዘላለም ሊኖር አይችልምና፡፡

እኮ ለምን ያህል ጊዜ? ረዥም ጊዜ አይሆንም ምክንያቱም የዘራኸውን ታጭዳለህና…

እኮ ለምን ያህል ጊዜ እኮ ነው የምንለው? ረዥም ጊዜ አይሆንም ምክንያቱም የሞራል ስብዕና ጠርዙ ረዥም ነውና፣ ሆኖም ግን ወደ ፍትህ ዘንበል ይላል፡፡

እስክንድር፣ ርዕዮት እና ሌሎች የነጻነት ታጋዮች ለምን ያህል ጊዜ ነው በጽናት የሚቆሙት? ኢትዮጵያ ለምን ያህል ጊዜ በጽናት መቆም አለባት? ረዥም ጊዜ አይሆንም፣ ሆኖም ግን ተስፋየለሽ ሰዓት ቢሆንም ቅሉ ረዥም አይሆንም ምክንያቱም ህወሀት የዘራውን ያጭዳልና፡፡ ድልአድራጊነት ጽናቱ ላላቸው ሰዎች ሁሉ የተረጋገጠ ነው፡፡

እስክንድር በደብዳቤው እንዲህ በማለት ጽፎ ነበር፣ “ግለሰቦች ሊቀጡ ይችላሉ፣ ሊሰቃዩ ይችላሉ (ኦ ልጀን እንዴት እዳጣሁት እና እንደናፈቀኝ) ከዚህም በላይ ሊገደሉ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን ዴሞክራሲ ሊወገድ የማይችል የሰብአዊነት ዕጣፈንታ ነው፡፡ ዴሞክራሲን ማዘግየት ይቻል ይሆናል ሆኖም ግን ማሸነፍ አይቻልም፡፡“

ፍትህን ማዘግዬት ይቻላል፣ ሆኖም ግን በፍጹም ማሸነፍ አይቻልም፡፡ በሰብአዊ መብት ላይ ወንጀልን የፈጸሙ ወንጀለኞች በእመቤት በፍህ ላይ ያላግጣሉ፣ አፍንጫቸውን ይነፋሉ፣ አመልካች ጣታቸውንም ይቀስራሉ፣ ሆኖም ግን እመቤት ፍትህ በእጇ ላይ ምን እንዳለ እንጅ ምን ይዛ እንዳለች ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ የሰው ልጅ ታሪክ የመጨረሻ መቆሚያ ጠርዙ የሰው ልጆች የሰብአዊ መብት ዕድል የሚከበርበት፣ የነጻነት እና ዴሞክራሲ መኖር፣ ከጭቆና ነጻ የመሆን፣ ከደናቁርት ወሮበላ ዘራፊ አምባገነኖች መላቀቅ፣ አንድ ሰው ከአምላኩ የተሰጡትን ተፈጥሯዊ የማሰብ፣ የመፍጠር እና ነጻ የሆኖ ሰብአዊ መብቶች ማከበር ነው፡፡

እስክንድር ለልጁ ያለውን ሀሳብ እንዲህ በማለት ገልጿል፣ “ኦ ልጀን እዴት እዳጣሁት እና እንደናፈቀኝ“ በማለት የተሰማውን ስቃይ አሳውቋል፡፡ የልጁ ስም ናፍቆት የሚባል ሲሆን ትርጉሙም “አንድን ሰው በመለየት ማጣት” የሚል ነው፡፡ ምን ዓይነት የሚገርም እና ነብያዊ የስም አወጣጥ ዘዴ ነው! ናፍቆት እ.ኤ.አ በ2005 ወላጆቹ በእስር ቤት ያለምንም ወንጀል 16 ወራት ታስረው ክሳቸው እንዲቋረጥ ተደርጎ ከተፈቱበት በመለስ ዜናዊ የቃሊቲ እስር ቤት ነው የተወለደው፡፡ አረመኔው እና ጨካኙ መለስ ዜናዊ ናፍቆት ገና ያልዳበረ ህጻን በነበረበት ጊዜ የህክምና እገዛ እንዳያገኝ በራሱ ትዕዛዝ እገዳ ጥለው ነበር፡፡ የመለስን ጣልቃገብነት በተመለከተ ያለው ማስረጃ አወዛጋቢ አይደለም፡፡ መለስ እስክንድርን እና ሰርክዓለምን ለመበቀል ሲል የቀናት እድሜ ብቻ የነበረውን ህጻን ልጃቸውን ለመግደል በጽናት ወስኖ ነበር፡፡ መለስ አስክንድርን እና ሰርክዓለምን ህጻን ልጃቸው በእስር ቤት ውስጥ እንዲሞት በማድረግ በሀዘን እንዲገረፉ ለማድረግ ፈልጎ ነበር፡፡ መለስ ጠላቶቸ ናቸው የሚለዉን ሰዎች በአደባባይ በህዝብ ፊት እንዲዋረዱ ማድረግ ብቻ ደስ የሚያሰኘው ሰው ነበር። ሆኖም ግን ከህዝብ እይታ ውጭም ቢሆን ጠላቴ የሚለዉን ንጹሀን ዜጎች ሲሰቃዩ እና መከራ ሲደርስባቸው ማየት ከምንም በላይ ደስ ያሰኘው ነበር ፡፡ እሱን በቅርብ የሚያውቁት ሰዎች ለዚህ ምስክርነት ይሰጣሉ፡፡ እስክንድር እና ሰርክዓለም በመጨረሻ በጻፉት ደብዳቤ ህጻን ልጃቸው በእግዚአብሄር ታምር ከሞት እንደተረፈ ይፋ አድርገዋል፡፡

አሁን በህይወት የሌሉት መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 2010 በኒዮርክ ከተማ በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ በመገኘት ንግግር እንዲያደርጉ ፕሮግራም ተይዞላቸው በነበረበት ወቅት እስክንድር እና ባለቤቱ ሰርክዓለም (በእራሷ መብት እና በምታሳየው ደፋር የጋዜጠኝነት ባህሪ እ.ኤ.አ በ2012 ከሴቶች የግንኙነት ተቋም/Women’s Media Foundation የጋዜጠኝነት ሽልማት አሸናፊ የሆነች) ሰውዬው በዩነቨርስቲው ተገኝቶ ንግግር እንዳያደርግ የሚቃወም ደብዳቤ ለዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ጽፈው ነበር፡፡ የተቃውሟቸውን መሰረትም እንዲህ በማለት ግልጽ አድርገው ነበር፣

ህጻኑ በሚወለድበት ጊዜ ከሚጠበቀው የክብደት መጠን

No comments:

Post a Comment