በአስራት አብርሃም
አዲስ አበባ በፊት ከየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ለሚመጣ ሰው ገነት ነበረች። አዲስ አበባ የሄደ ሰው ቤት ባይሰራ እንኳ ሆዱ ጠግቦ ይኖራል፤ መኪና ባይኖረውም ባማሩ ታክሲዎች ሽር እልም ማለት ይችላል። ወደ አዲስ አበባ የሄደ ሰው እንደሚያልፍለት ምንም ጥርጥር የለውም እየተባለ ሲነገር ልጅ ሆኘ እሰማ ነበር። እንደ ችግር ከተነሳ አዲስ አበባ የሄደ ሰው ወደ ሀገሩ አይመለስም፤ የሽዋን ውሃ ከቀመሰ ሀገሩን ይረሳል እየተባለ ይወራል። አሁን ያ ሁሉ ተረት ሆኗል። አሁን አዲስ አበባ መምጣት ብቻውን የሚፈይደው ነገር የለም፤ ወይ ደህና ዘመድ ወይም ባለስልጣን ሰው ሊኖርህ የግድ ይላል፤ ምንም ለሌለው ደሀ ሰው ዝም ብሎ እንደ ድሮ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ መምጣት በጣም አስቸጋሪ ነው። ምግብና መኝታ ማግኘት ፂማም ሴት በከተማው የመፈለግ ያህል ከባድ ሊሆንበት ይችላል፤ ጎደና እያደረ ካልለመነ በስተቀር!
እኛ በአዲስ አበባ የምንኖረው ዜጎች በብዙ ነገር ብንማረርም አሁንም ግን መሄጃ ያጡ ብዙ ሰዎች በተለያዩ ምክንያትና ለተለያዩ ዓላማ ከሁሉም ክፍላተ ሀገር ወደ አዲስ አበባ ይጎርፋሉ። ገሚሱ ጫማ ጠራጊ ሲሆን ሌላው ደግሞ መውልዊያ እየዞረ ይሸጣል። ሌላው ቆሎ ሌላው ደግሞ ሎተሪ እያዞረ በመሸጥ የዕለት ምግቡን ያገኛል። ከዚህ ውጪ ለልመናም የሚመጣ አለ፤ ምናልባትም በአዲስ አበባ ቀላሉን ነገር መለመን ሳይሆን አይቀርም፤ ምክንያቱም የአዲስ አበባ ህዝብ አባ መስጠት የሚባል ዓይነት ነው። በየትኛውም ቋንቋ፣ በየትኛውም ኃይማኖት ለምነው ይሰጣል።
የኑሮው ነገርማ እንኳን ምንም ለሌለው አዲስ መጤ ይቅርና እዚሁ የአራዳ ውሀ እየጠጣ ላደገም አስቸጋሪ ሆኗል። በአሁኑ ሰዓት የእግር መኪና ወይም የመስራያቤት ሰርቪስ የሌለን የአዲስ አበባ ነዎሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ፣ አንዳንዴም ከዚያ በላይ እንሰለፋለን። ሰልፍ ያማራት እርጉዝ ብትኖር አሁን ብዙም የሚያስቸግር አይደለም፤ ወደ አንዱ የታክሲ ሰልፍ ወስዶ እዚያ እንድትቆም ማድረግ ይቻላል።
Wednesday, April 30, 2014
Tuesday, April 29, 2014
ሦስት ባርያ ነጻ የሚወጣው መቼ ነው? እሱ ሲፈቅድ ነው? ወይስ ጌታው ሲፈቀድለት?
ፕ/ር መሰፍን ወ/ማርያም
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት የፖሊቲካ ድርጅቶች ገዢ የሚባለውንም ጨምሮ ስያሜአቸው እንደሚያመለክተው ከነጻነት ውጭ ናቸው፤ ሌላው ቀርቶ ለነጻነት የተዘጋጁ አይደሉም፤ ራሳቸው በባርነት ውስጥ በጀርባቸው ተንጋልለው ሌሎችን ከባርነት ለማውጣት ማሰባቸው አለማሰባቸውን እንጂ ሌላ አያመለክትም፤ ወያኔ ራሱ ገና ነጻ ያልወጣ የባሪያዎች አለቃ ነው፤ ወያኔ ለባርነት ደረጃ አበጅቶ ጠርናፊና ተጠርናፊ እያለ ከፍሎታል፤ ከወያኔ ጋር በደባልነት አገር ለመግዛት የተመለመሉት ከባርነት ሳይወጡ ካባ ለብሰው በአገልጋይነት የወያኔን ጉድለት ለማሟላት የሚሞከርባቸው መሣሪያዎች ናቸው፤ መሣሪያነታቸው የተሰማቸው ከብዙ ዓመታት ጀምረው በመኮብለል ላይ ቢሆኑም፣ ጭራውን እየቆላ በሞተ-ከዳ እግር ለመግባት የሚተናነቀው ብዙ ነው፤ ወያኔ ለአንድ ትልቅ አገር የሚበቃ ሠራዊት፣ ለአንድ ትልቅ አገር የሚበቃ የፖሊስ ኃይል፣ ለአንድ ትልቅ አገር የሚበቃ የአስተዳደር የሰው ኃይል በቁጥርም በጥራትም የለውም፤ በይድረስ-ይድረስ በብዙ ዶላር አስተማሪዎችን ከውጭ እያስመጡም ሆነ፣ ወይም በፖስታ፣ ወይም ከታወቀው ማምረቻ በሚወጡ የለብ-ለብ ምሩቆች እየተንገዳገደ እዚህ ደረሰ።
እዚህ ደረስን ቢሉና ቢኤ፣ ኤምኤና ፒኤችዲ በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ቢያውለበልቡም የሚሠሩት ብቻ ሳይሆን የሚናገሩትም አለመማራቸውን ያሳብቅባቸዋል! ለመሆኑስ በጥይት ለጥይት የተገራ አንጎል እንዴት ብሎ በሀሳብ ይለዝባል? እንዴት ብሎስ ለሕግ ይገዛል? ስለዚህም ወያኔ ስለትምህርት መነሻውንም መድረሻውንም አያውቅም፤ ስለዚህም ለትምህርት ሚኒስትርነት የሰየማቸውን ሰዎች አንድ በአንድ ማስታወሱ ወያኔ ለትምህርት ያለውን ግምት ያሳያል፤ በትምህርታቸውና በሙያቸው እውቀት በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በየትም አንቱ የተባሉትን ሰዎች ‹በችሎታ ማነስ› እየተባለ በትእዛዝ በሚነዳ አሻንጉሊት እየተፈረመ ከዩኒቨርሲቲ ማባረሩና ዩኒቨርሲቲውን ወና ማድረጉ ሌላ ማስረጃ ነው፤ ከተባረሩት ውስጥ አንድም በኑሮው የተጎዳ የለም፤ የተጎዳው ዩኒቨርሲቲው ነው፤ የተጎዳችው ኢትዮጵያ ነች፤ የተጠቀሙት ወያኔዎች ናቸው፤ ዩኒቨርሲቲውን ሲያረክሱትና ሲያዋርዱት እነሱ ራሳቸውን ከፍ አድርገው ለማሳየት መድረኩን የከፈተላቸው መስሏቸው ነበር፤ በአቶ አዲስ ዓለማየሁ ላይ የተረተው ፋሺስት ‹ለካስ ሰው ከሌለበት፣ ቤት ቁንጫ ይፈላበታል!› ያለው እንደተፈጸመባቸው ዛሬም አልገባቸውም፤በዚህም ምክንያት ወያኔ ለተለያዩ የማኅበረሰብ አገልግሎቶች ለማሰማራት የሚያስችሉት የተማሩና የተመራመሩ ባለሙያዎች የሉትም፤ በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የተቋቋሙት እንደኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አንደመብራት ኃይል፣ እንደቴሌ፣ እንደየኢትዮጵያ ዓየር መንገድ፣ … ወዘተ. በአጥንታቸው በመሄድ ላይ ናቸው፤ ማክሸፍ እንዲህ ነው! ለአብራሪዎች ትምህርት ቤት የነበረችው ኢትዮጵያ ዛሬ አብራሪዎችን ከኢጣልያና ከሌሎች አገሮች እያስመጣች ነው፤ የሥልጣን ወንበሩን ከያዙት ጀምሮ አከርካሪት ስለመስበር ሲፎክሩ ቆይተው አሁን ኢጣልያዊ አውሮጵላን አብራሪና መሀንዲሶችም ከያለበት እያስመጡልን ነው፤ የማን አከርካሪት ተሰበረ!

Monday, April 28, 2014
የጋዜጠኞቹና የአክቲቪስቶቹ እስር አሳሳቢ ነው፡፡
ከኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋመ) የተሰጠ መግለጫ
------------------------------------------------------------------------
የጋዜጠኞቹና የአክቲቪስቶቹ እስር አሳሳቢ ነው፡፡
------------------------------------------------------------------------
ትላንት ሚያዝያ 17 2006 አመሻሽ ላይ ዞን 9 በተሰኘ ድረ ገጽ (ብሎግ) ላይ በሳል ፖለቲካዊና ማህበራዊ ትችቶችን በማቅረብ ከሚታወቁት ፀኀፍት መሀከል 6ቱ ማለትም ማህሌት ፋንታሁን፣ በፍቃዱ ሀይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ዘላለም ክብረት፣ አጥናፍ ብርሀን፣ አቤል ዋበላ እንዲሁም ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ፣ ጋዜጠኛ አስማመው ኃ/ጊዎርጊስ እና ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል፡፡
ግለሰቦቹ በተለያየ ቦታ በየስራ ገበታቸው ላይ እያሉ ሁሉም በተመሳሳይ ሰዓት በፀጥታ ሀይሎች ተይዘው በማዕከላዊ ምርመራ ማዕከል ታስረው የሚገኙ ሲሆን፤ የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት እስሩ በደንብ የታሰበበት ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ታሳሪዎቹ ታሰሩ ከተባለበት ሰዓትና ደቂቃ ጀምሮ የሚገኙበትን አጠቃላይ ሁኔታ ለማጣራት አየሰራ ሲሆን ፤ እስካሁን በሰበሰበው መረጃ መሰረት ልጆቹን ለእስር የሚያበቃ ምን አይነት ማስረጃ እንደተገኘባቸው ለማወቅ አልቻለም፡፡
ሆኖም ግን ለእስር ከመዳረጋቸው በፊት ከመንግስት ሲርስባቸው በነበረው ህገወጥ ድርጊቶች ምክንያት ለረጅም ጊዜ ስራቸዉን ካቋረጡ በኋላ በቅርቡ ወደ ስራ መመለሳቸዉን ይፋ አድርገው እንደ ነበር ከድረ-ገጻቸው ላይ ለመረዳት ችለናል፡፡ ይህ ጉዳይ እስሩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎብናል፡፡

Saturday, April 26, 2014
የዘረኞች ነውር በድሬዳዋ
ድሬዳዋ የኢትዮጵያዊያን ከተማ ነበረች። ኢትዮጵያዊያን የጎሳቸውን አጥር አፍርሰው በኢትዮጵያዊነታቸው ብቻ ለረዥም ዘመን አብረው በድሬዳዋ ኑረዋል። በዚህ ሁኔታ የሚኖረው ህዝብ አብሮ ስቆ ፤አብሮ ተደስቶ፤ ያለው ለሌለው አካፍሎና ተቻችሎ መኖርን የሚያውቅ ነበር። ዛሬ ግን ያች ቀድሞ የምናውቃት ድሬዳዋ ተረት ሁናለች። ሁሉ ስቆና ተደስቶ የሚኖርባት ከተማ ሳትሆን በየወቅቱ በእሳት እንድትጋይ ሁና ብዙዎች እንባቸውን በመዳፋቸው የሚያፍሱባት ከተማ ሁናለች። ብዙዎች የንግድ ሥፍራቸው ተቀነባብሮ በተነሳ እሳት በመጋየቱ ባዶ እጃቸውን ቀርተዋል። ልጆቻቸውም ድሃ አደግ እንዲሆኑ ሁኗል። ይባስ ብሎ ንብረቶቻቸውን ከእሳት ቃጠሎ ለመከላከል እሳቱን ለማጥፋት የተነሱ ዜጎች በአሸባሪነት ተከሰው ህወሃቶች “ ፍርድ ቤት” ብለው ወደ ሚጠሩት ሥፍራ እንዲቀርቡ ሁኗል።
ገ/መድህን ገ/መስቀል፤ ቢኒያም ጌታቸው፤ መቻል አብራር፤ ምትኩ ውብየ፤ ኢዮብ ገብሬ፤ ሃቢብ ሸምሱ፤ ለዒላ ዓሊ ፍትህን በማያውቀው በህወሃት ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ከእነዚህ ውስጥ ከገ/መድህን ገ/መስቀል በቀር ሌሎቹ የዋስ መብት ተነፍጓቸው ወሂኒ እንዲቆዩ ተደርጓል። ገ/መድህን ገ/መስቀል በምን ሁኔታ ከሌሎቹ ተለይቶ “ነፃ ሰው” ሊባል እንደቻለ የሚያውቅ የለም። ብዙ ሰዎች ግን በትግራይ ተወላጅነቱ አፍቃሬ ህወሃት ” ተደርጎ እንዲታይ ለማድረግ ነው ይላሉ። ህወሃት በልዩ አፈና የራሱ ዋሻ ያደረገውን የትግራይ ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ለማቆራረጥ እንዲህ አይነት ያፈጠጠና ያገጠጠ የዘር መድልዎ ሲያደርግ የመጀመሪያው አይደለም። ድህረ ምርጫ 97 ከአዲስ አበባ ከተማ ተግዘው ወደተለያየ ማጎሪያ ከተላኩት በርካታ ሺዎች ውስጥ የትግራይ ተወላጆችን መርጦ “እናንተ ነፃ ናችሁና ወደ ቤታችሁ ሂዱ” ብሎ እንዳሰናበተ የማያውቅ የለም። የዘረኞቹ ቁንጮ መለስ ዜናዊ በህይወት በነበረበት ወቅት ሲደረግ የነበረውና ከህልፈቱም ቦኋላ ቀጥሎ ያለው የህወሃት የዘረኝነት መገለጫ አንዱ መንገድ ይሄው ነው። በትግራይ ወጣቶች የህወት መስዋዕትነት ለስልጣን በቅተው እራሳቸውን ያነገሱ የህወሃት መሪዎች ትግሬን ነፃ ማውጣት ማለት ከሌላው ወገኑ ጋር ውሎ አድሮ ደም የሚያቃባ አድልአዊነት እንዲህ በአደባባይ መፈጸም ነው ብለው ያምናሉ። እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል እንዳለቺው እንስሳ ለህወሃቶች እንዲህ አይነት ዘረኝነት ወደፊት ሊፈጥር የሚችለው አደጋ አይታያቸውም ወይም ስለርሱ ማሰብ አይፈልጉም። ።ከአማራና ከአፋር የሚዋሰኑትን ለም ቦታዎችንና በበከርሰ ምድር ማዕድን የከበሩ ሥፍራዎችን ቀምተው ወደ ክልላቸው ሲጠቀልሉና ነዋሪውን በማፈናቀል የቀድሞ ታጋዮቻቸውን ሲያሰፍሩባቸው አልሰቀጠጣቸውም። ወያኔ የራሱ ዋሻ አድርጎ በሚቆጥረው የትግራይ ክልል ውስጥ እያደረሰ ያለው ስቃይና መከራ የክልሉን ግንብ ጥሶ በመላው አለም በመሰማት ላይ ባለበት በአሁኑ ወቅት በተለያየ የአገሪቱ ክፍል ተበትኖ የሚኖረውን ጥቂት የትግራይ ተወላጅ ተጠቃሚ በማድረግ የትግሬ ነጻ አውጪ ለመምሰል የሚደረገው ጥረት በትግራይ ህዝብ ዘንድ ሳይቀር እየተወገዘ ነው። ዘረኞቹን የህወሃት መሪዎች እረፍት የነሳውና እንዲቅበዘበዙ እያደረገ ያለውም የዚህ ዘረኛ አላማቸው የራሴ ነው በሚሉት የቀድሞ ምሽጋቸው ሳይቀር እየታወቀ መምጣቱ ነው።

Ethiopia: Multiple arrests in major crackdown on government critics (Press releases by Amnesty)
The Ethiopian government is tightening its suffocating grip on freedom of expression in a major crackdown which has seen the arrest of numerous independent, critical and opposition voices over the last two days, said Amnesty International.
Six members of an independent blogger and activist group and a freelance journalist were arrested yesterday 25 April. Another journalist was arrested this morning. Meanwhile 20 members of the political opposition Semayawi (Blue) party have been arrested since Thursday.
"These arrests appear to be yet another alarming round up of opposition or independent voices" said Claire Beston, Ethiopia researcher at Amnesty International. "This is part of a long trend of arrests and harassment of human rights defenders, activists, journalists and political opponents in Ethiopia."
Six members of the independent blogger and activist group ‘Zone 9’ were arrested on 25 April in Addis Ababa. Group members Befeqadu Hailu, Atnaf Berahane, Mahlet Fantahun, Zelalem Kiberet, Natnael Feleke and Abel Wabela were arrested from their offices or in the street on Friday afternoon. All six were first taken to their homes, which were searched, and then taken to the infamous Federal Police Crime Investigation Sector ‘Maikelawi’, where political prisoners are held in pre-trial, and sometimes arbitrary, detention.
ከሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለሚዲያ ማህበረሰቡ የተላለፈ ጥሪ
ውድ የሚዲያ ማህበረሰብ አባላት፡- ባለፉት 23 ዓመታት ህወሓት/ኢህአዴግ በህገ መንግስቱ የሚዲያ ነጻነት እንደሚፈቀድ ቢደነግግም በተግባር ግን የራሱን ፕሮፖጋንዳ ከሚነዛባቸው ሚዲያዎች ውጭ ሌሎቹን ሲዘጋና ሲያሸማቅቅ ኖሯል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ህዝባችን ከገዥው ፓርቲ ፕሮፖጋንዳ ውጭ አማራጭ መረጃ ማግኘት አልቻለም፡፡ ጋዜጠኞች እየታሰሩ፣ እየተሰደዱ፣ ሚዲያዎች እየተዘጉም ቢሆን የተቻላችሁን ያህል ለህዝብ መረጃ ለማድረስ የሚዲያው ማህበረሰብ አባላት ለምታደርጉት ሁሉ ከፍ ያለ ክብር አለን፡፡ የታፈነውን የህዝብ ድምጽ ለማሰማት የምታደርጉትን ጥረትም እናበረታታለን፡፡ ሆኖም አሁንም ቢሆን በገዥው ፓርቲ አፋኝነት ምክንያት ህዝባችን የሚገባውን መረጃ እያገኘ አይደለም፡፡ እናንተም በሰበብ አስባቡ ጫና እየደረሰባችሁ እንደሆነ ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡
ገዥው ፓርቲ ላይ የሰላ ትችት የሚያደርሱ ጋዜጠኞች ‹‹አሸባሪ›› ተብለው ታስረዋል፡፡ ጋዜጦችና መጽሄቶች በስርዓቱ ተዘግተዋል፡፡ በርካታ ጋዜጠኞች አገራቸውን ጥለው ተሰደዋል፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ድብደባ፣ ማስፈራሪያና ዛቻ ደርሶባቸዋል፡፡ እየደረሰባቸውም ነው፡፡ ገዥው ፓርቲ በሚያደርስባቸው ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ ጫና ከገበያ ወጥተዋል፡፡ በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት ለህዝባችን አማራጭ መረጃ የሚያደርሱ ሚዲያዎችና የሚዲያው ማህበረሰብ መብቶቻቸውን ተነጥቀው አደጋ ላይ ወድቀዋል፡፡
አማራጭ መረጃ ለዴሞክራሲና ለልማት ቀዳሚውን ሚና እንደሚጫወት የሚያምነው ፓርቲያችን ይህን የመብት ረገጣና አፈና ሲቃወምና ሲታገል ቆይቷል፡፡ አሁንም በጠነከረ መልኩ ይቃወማል፡፡
ፓርቲያችን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽን ጨምሮ የተነጠቁትን መብቶቻችን ለማስመለስ በመጣሩ አመራሮቹና አባላቱ በህገ ወጥ መንገደ እስር ቤት በሚገኙበት ተመሳሳይ ወቅት የዞን ዘጠኝ ወጣቶች በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህም ከመቸውም ጊዜ በላይ ጭቆናው እንደመረረ እና ሁሉን ማህበረሰብ ያቀፈ ትግል እንደሚያስፈልግ ዋነኛ ማሳያ ነው፡፡ ከዚህ የመረረ ጭቆና ህዝባችንን ነጻ ማውጣት የምንችለው እኛ ህዝቡን ማደራጀትና ማንቀሳቀስ የሚዲያ ማህበረሰቡም መደረጃውን ለህዝባችን ማድረስ ሲችል ብቻ ነው፡፡
ከሰማያዊ ፓርቲ የሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ በሃይማትታችሁ ጣልቃ ለተገባባችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የተደረገ ጥሪ!
ውድ ሃይማኖታችሁ ላይ ጣልቃ እየተገባባችሁ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፡- ሰማያዊ ፓርቲ ኢትዮጵያውያን በነጻነት የፈለጉትን ሃይማኖት እንዲከተሉ፣ የፈለጉትን እምነት እንዲይዙ ባለው የጸና አቋም ገዥው ፓርቲ በሙስሊሙና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ እያደረገ ያለውን ጣልቃ ገብነት ሲቃወም ቆይቷል፡፡ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ገዥው ፓርቲ በሐይማኖቱ ጣልቃ መግባቱን ተቃውሞ የሚያደርገውን ፍጹም ሰላማዊ እንቅስቃሴ በማድነቅ ገዥው ፓርቲ ከህገ ወጥ ተግባሩ እጁን እንዲሰበስብ ምክር ከመለገስ አልፎ በሰላማዊ ሰልፍም ድምጹን አሰምቷል፡፡ በተጨማሪም የሙስሊሙን መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የተወሰደው ህገ ወጥ እርምጃ እና በእስር ላይ እየደረሰባቸው ያለውን ስቃይም በጽኑ ሲቃወም ቆይቷል፡፡ ወደፊትም በዚሁ አቋሙ እንደሚቀጥል ይገልጻል፡፡
በተመሳሳይ በክርስቲያኖች በተለይም በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ያለውን ጣልቃ ገብነትም በተመሳሳይ ሲቃወም ቆይቷል፡፡ ለአብነት ያህል በዋልድባ ገዳም ላይ የተወሰደውን ህገ ወጥ ተግባር በግልጽ ተቃውሟል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በተለይም በማህበረ ቅዱሳን ላይ ጫና እየተደረገ እንደሚገኝ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በማህበሩ ላይ ሊደረግ የታሰበው ሴራ እየተከታተለ ይገኛል፡፡ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንም ሆነ በማህበሩ ላይ እየተደረገ ያለውን ጫናም በጽኑ ይቃወማል፡፡
ውድ የሁለቱም እምነት ተከታዮች፡- ሰማያዊ ፓርቲ ህወሓት/ኢህአዴግ የሚያደርገውን ጫና እና ጣልቃ ገብነት በጽኑ እየተቃወመ፣ ማንኛውም በሐይማኖታችሁ ላይ የሚደረግን ጫና በግልጽ እንድትቃወሙ ጥሪ ያቀርባል፡፡ የሁለቱም የእምነት መጽሃፍቶች በአንዳችን ላይ የሚደርሰው ግፍ በሌላኛው ላይም እንዳይሆን መፈለግ እንዳለብን እንደሚገልጹት የእናንተ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ላይ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነትና ጫናም በመቃወም ለመርህ እንድትቆሙ ማሳሰብ ይፈልጋል፡፡
Friday, April 25, 2014
አለም አቀፍ ሰብአዊ መብት መሳሪያዎችና ኢትዮጵያ
በሶልያና ሽመልስ
በኢህአዴግ መንግስት የመሪነት ሰልጣኑን ከያዘ ከዛሬ 22 አመት ግድም ጀምሮ ቃል ገብቶ ተግባራዊ ባለማድረግ ከሚወቀስባቸው ጉዳየች አንዱ የአገሪትዋ የሰብአዊ መብት አያያዝ ነው፡፡ ሁሉንም አለም አቀፉን የመብቶችን አለማቀፋዊነት የሚያረጋግጡ ጠንካራ እና ግልጽ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን የያዘ ህገ መንግስት በመጀመሪያዎቹ የስልጣን አመታት መጽደቁም ይታወቃል፡፡
በመጀመሪያዎቹ አስር አመታት የነበረው የሰብአዊ መብት አያያዝ በጣም በአስጊ ሁኔታ ከፍተኛ ቅሬታ የቀረበበት ቢሆንም የቀጣዩ አስር አመታት አፈጻጸምም ከትችት አላመለጠም፡፡ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሰብአዊ መብት ሪፓርቶችን የሚያወጡ አገር በቀል የማህበረሰብ ድርጅቶች በበጎ አድራጎትና ማህበራት አዋጅ የተነሳ ሽባ በመሆናቸው የሰብአዊ መብት ሁኔታውን ለመገምገም አስቸጋሪ ስለሆነ የአገሪትዋ ሰብአዊ መብት ሁኔታ ” የውጪ ሃይሎች” ድምጽ ብቻ የሚሰማበት ምድረ በዳ ሆኗል፡፡ በአገሪትዋ የተለያዬ ክፍሎች የሚከናወኑ የመብት ጥሰቶችን ለእርምት የሚያቀርብ የአገር ውስጥ ተቋም በሌለበት ሁኔታ በቀጣዩ የፈረንጆች ወር መጀመሪያ የኢትዮጰያ የሰብአዊ መብት ግምገማ (universal periodic review ) ለሁለተኛ ጊዜ በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ይካሄዳል፡፡
አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ግምገማ (United Nations Human Rights Council Universal Periodic Review)
አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ግምገማ ሁሉም የተባበሩት መንግስታት አገራት በየ4 አመት ተኩል የሚያደርጉት የሰብአዊ መብት ግምገማ ሂደት ነው፡፡ይህ የግምገማ ሂደት አገሮች ያላቸውን የሰብአዊ መብት ችግሮች ለመፍታት እና ችግሮቻቸውን በማስታወስ እነዲያሻሽሉ እንደያግዝ የታሰበ ስርአት ሲሆን እኤአ ከ20006 ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል፡፡ በዚህ ግምገማ የተገምጋሚው አገር መንግስት የሰብአዊ መብት ስራውን አስመልክቶ ሪፓርት ያቀርባል፡፡ መንግሰታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የሰብአዊ መብት ተቋማትም በተመሳሳይ ተገምጋሚው አገር የሰብአዊ መብት ሁኔታ ላይ ሪፓርታቸውን ለተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ያስገባሉ፡፡ እነዚህ የመንግሰትም መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሪፓርቶችም ተሰብስበው ለአባል አገራት አንዲደርሱ የማድረግ ሃላፌነቱን የተባበሩት መንግስታት ይወስዳል ፡፡ ይህ የግምገማ ሂደት በአጠቃላይ ለ3 ሰአት ከሰላሳ የሚቆይ ሲሆን ተገምጋሚው አገር የራሱን የሰብአዊ መብት ሁኔታ የሚገልጽ ሪፓርት ካቀረበ በሁዋላ የተለያዩ አገራት ጥያቄ ለማቅረብና የማሻሻያ ነጥባቸውን ( recommandations) ለመናገር ቦታ ይይዛሉ ፡፡ በዚህ የግምገማ ሂደት ተገምጋሚ አገር አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው የሚቀበለውን የማሻሻያ ነጥብ ተቀብያለው ሲል የማይቀበላቸውን ነጥቦች አልቀበልም በማለት እዚያው መልስ መስጠት ይችላል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን አጠቃሎ የተቀበላቸውንና ያልተቀበላቸውን ማሻሻያ ሃሳቦች በሶስት ወራት ገደማ ውስጥ በይፋ ያሳውቃል፡፡ ይህ ሂደት ከተጠናቀቀ በሁዋላ እነዚህን የማሻሻያ ሃሳቦች መተግበር የተገምጋሚው አገር ሃላፊነት ነው፡፡ይህ ሂደት የመጀመሪያው ከሆነ የሰብአዊ መብት ሪፓርትና ጥያቄዎችን የመመለስ ሂደት ሲሆን ለሁለተኛ ዙር ከሆነ ግን ተገምጋሚው አገር በመጀመሪያው ግምገማና በሁለተኛው ግምገማ መካከል ያለውን አፈጻጸምና መሻሻል የማሻሻያ ነጥቦቹ ላይ ያደረገውን ተግባራዊ ለውጥ አብሮ ያቀርባል፡፡ በዚህ መሰረት የኢትየጵያ መጀመሪያው ግምገማ እኤአ በ2009 የተካሄደ ሲሆን ከተለያዩ አገራት 160 የማሻሻያ ነጥቦች አቅርበው ነበር፡፡
የአብዮቱ የልደት ቀን
በፋሲል የኔያለም
ክፍል አንድ
በማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ውስጥ መተንበይ ከባድ ፈተና ነው፣ ቢሆንም ምሁራን መረጃዎችን አሰባስበው ከመተንበይ ወደ ሁዋላ አይሉም። ቶማስ ፍሬድማን ከ100 ዓመታት በሁዋላ በዓለማችን ስለሚፈጠረው የፖለቲካ ሁኔታ መጽሃፍ አሳትሟል። ሳሙኤል ሃንቲንግተንም ስለመጪው ጊዜ ግጭቶች ያሳተመው Clash of Civilizations በአንድ ወቅት ሰፊ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። የአሜሪካ መንግስት የ25 ዓመታት ትንበያ በየጊዜው ያወጣል። አንዳንዱ ትንበያ ይሳካል ሌላው ደግሞ ተኖ ይቀራል። የሶቭየትን መፈራረስ የተነበዩ ብዙ ምሁራን ነበሩ ፣ የአሜሪካን መፈራረስም የተነበዩ ቁጥራቸው ቀላል አልነበረም። በሶቭየት ላይ "ያሟረቱ ሲሳካላቸው"፣ በአሜሪካ ላይ "ያሟረቱት ግን ሳይሳካለቸው ቀረ"። በቻይናም ላይ ብዙ ትንቢቶችን እያነበብን ነው። አንድሪው ፍራንክ ReOrient በሚለው መጽሃፉ ቻይና የነገዋ ልዕለ ሃያል ናት ይለናል፣ ፍሬድማን ደግሞ የለም የቻይ እድሜ የጤዛ ያክል ነው፣ ከጥቂት አመታት በሁዋላ ትበታተናለች ይለናል። በአጭሩ ትንበያ ማካሄድ ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሲቀል ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ግን እጅግ ከባድ ነው።
አንድ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪ "በኢትዮጵያ ውስጥ አብዮት ይከሰታል አይከሰትም" ብሎ ለመተንበይ ከመሞከሩ በፊት የሚመጣውን አደጋ ለመቀበል ዝግጁ መሆን አለበት። ትንቢቱ ሳይሳካ ከቀረ "ስነልቦናን" የሚጎዳ ትችት ሊያስተናግድ ይችላል። ይህን መቋቋም እንደሚችል ካመነ ነጻነቱን እንዳወጀ ይቁጥረው። አንዳንዱ ትንቢት ጻሃፊ ትችትን በመሸሽ ትንቢቱ የሚፈጸምበትን ጊዜ ወይም የጊዜ ገደብ ለመጥቀስ አይፈልግም፤ "እንዲህ ይሆናል" ብሎ ይናገራል እንጅ " በዚህ ጊዜ እንዲህ ይሆናል" ብሎ ለመናገር አይደፍርም። ይሄ ደግሞ ትንቢት አይባልም። "በኢትዮጵያ ውስጥ አብዮት ይነሳል" ብሎ በደፈናው መተንበይና "በ2010 ዓም በኢትዮጵያ ውስጥ አብዮት ይነሳል" ብሎ መተንበይ ሰፊ የሆነ ልዩነት አላቸው። አንድ ጊዜ አንዲት ተማሪ ዴንማርክን ካርታ ላይ እንድታመለክት ተጠየቀች፣ ተነሳችና መላውን አውሮፓ አመለከተች። ተማሪዎችም ሳቁ። ተማሪዋ አውሮፓን መጠቆሟ ትክክል ቢሆንም፣ ከአውሮፓ ውስጥ ዴንማርክን ነጥላ ባለማሳየቷ ግን ተሳሳተች። የጊዜ ገደብ ያልተቀመጠለት ትንበያም ዴንማርክን ጠቁም ሲባል አውሮፓን እንደመጠቆም ይቆጠራል ። በጽሁፌ ማጠቃለያ ላይ የለውጡን ( አብዮቱን) ጊዜ በድፍረት አስቀምጣለሁ። (ካልተሳካልኝ ትችቱን ለማስተናገድ ዝግጁ ነኝ፣ ድንገት ከተሳካለኝ ግን አደራ ኮከባችንን ቁጠርልን እያላችሁ እንዳታስቸግሩኝ)

Tuesday, April 22, 2014
በደል በቃ! ጭቆና በቃ! ብለህ ተነስ! አምጽ!!!
በቅዱስ ዮሃንስ
አመጽ የህዝብ መብት ነው። የተበደለና የተጨቆነ ህዝብ ማመፅ መብቱ ብቻ ሳይሆን ግዴታውም ጭምር ነው። በአገራችን ኢትዮጵያ የየካቲት 66 ቱን አመፅ ብንመለከት መንስኤው ጭቆና ነበር። የቤኒዚል ዋጋ መጨመሩን የተቃወሙ ታክሲ ነጅዎችና በትምህርት ፖሊሲው ላይ ሊተገበር የታቀደውን ሴክቶሪያል ሪቪው የተቃወሙ አስተማሪዎችና ተማሪዎች ህዝባዊ እንቅስቃሴውን ለኩሰው እንዳቀጣጠሉትና ህዝባዊ አመፅ ወልዶና ተፋፍሞ የአፄውን አገዛዝ ወደ ከርሰ መቃብሩ እንደሸኘው ይታወሳል። ይህም ህዝባዊ አመጽ ከአንባገነንና ጨቋኝ ስርአት በላይ ሃይል እንዳለው ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
ካለፉት ጥቂት አመታት ወዲህ አለማችንም በአዲስ አይነት ሕዝባዊ አመፅና የለውጥ ማዕበል እየተናጠች ትገኛለች፡፡ በ2002/3 ዓ.ም በቱኒዚያ የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ አመፅ ፕሬዝዳንት ቤን አሊን ካሰናበተ በኋላ ወደ ግብፅ በማምራት ለ30 ዓመታት ተደላድለው ይመሩ የነበሩትን ሙባረክንም ከስልጣናቸው አሽቀንጥሯቸዋል፡፡ ቀጥሎም በየመን፣ በባህሬን፣ በሶሪያ፣ በአልጀሪያ፣ በሊቢያ፣ በኳታር፣ በዮርዳኖስ፣ በኩዌትና በሌሎችም አረብ አገራት ሕዝባዊ አመፅ መቀስቀሱ ይታወሳል፡፡ ከነዚህ ህዝባዊ አመጾች ጀርባ ደግሞ የመንግስታት ገደቡን ያለፈ በደል፤ ጭቆና፤ አምባገነንነት፤ ቅጥ ያጣ ዘረፋ እና ሙስና ይገኛል። በኢትዮጵያስ፤ በእውነት ግን ገደቡን ያለፈ በደል የለምን? ጭቆናስ? ኧረ ቅጥ ያጣ ዘረፋና ሙስናስ? ይህ ሁሉ እየሆነ ታዲያ ስለምን ህዝብ በቃ ብሎ መነሳትና ማመጽ ተሳነው?
በአረብ ስፕሪጉ አብዮት በተለይም በቱኒዚያ፤ አልጀሪያና በሌሎቹም አገሮች እንደተመለከትነው ህዝቡ የኑሮ ውድነትንና ስራ አጥነትን በመቃወም ከአገዛዞቹ ፍቃድ ውጭ በተቀናጀ ሁኔታ ባካሄዱአችው የተቃውሞ አመፆች በርካቶች ቢሰውም እንቅስቃሴው ድልን ወልዶ አገዛዞቹን ቀብሮ ማለፉ አይዘነጋም። ድሉ የተገኘውም ህዝቡ አሻፈረኝ ብሎ ስለተነሳና ስለታገለ ብቻ ነው። አምባገነኑ የቱኒዚያ አገዛዝ፤ ፕሬዜዳንቱና መላ ቤተሰቦቹ እንደ ባንዳዎቹ የጉጅሌው ወያኔ ቁንጮዎችና ቱባ ካድሬዎች በሙስና የተጨማለቁ ሲሆን ተቃዋሚዎችን ቦዘኔዎች ሲሉ ቢከሱና በርካታ ንጹሃን ዜጎችን ቢገድሉም በህዝባዊ አመጽ ከመገርሰስ ግን ፈፅሞ ሊያመልጡ
አልቻሉም፤ ላይመለስ አገዛዙ ተቀብሯልና። ቀደም ብሎ በሌሎች አገሮችም እንደታየው የኑሮ ውድነትን በመቃወም ህዝብ ሞት አይፈሬ ሆኖ በጀግንነት በመሰለፉና፤ በርካቶች ቢሰውም ትግሉ ግን ተፋፍሞ በመቀጠሉ አዎንታዊ ድልን አስመዝግቦ መጠናቀቁ ይታወቃል። ከዚህም የምንማረው አሁን በአገራችን በጉጅሌው ወያኔ የተዛባ ፖሊሲ ምክንያት የተንሰራፋውን የኑሮ ውድነትና ስራ አጥነትን እንዲሁም ሙስና፤ የሰብአዊ መብት ረገጣ፤ ስልጣን የህዝብ እንዲሆን፤ ግለሰቦች በፖለቲካ አመለካከታቸው፤ በእምነታቸውና ሃሳባቸውን በነፃነት በመግለፃቸው የማይታሰሩባት ሃገር ለመፍጠር፤ ፍትህን ለማስፈን ጭቆናንና በደልን በዝምታ በመመልከት ሳይሆን መፍትሄው እምቢኝ አሻፈረኝ ብሎ በመነሳት የተቀናጀ ህዝባዊ አመጽ ማድረግና የችግሮቹን ሁሉ ምንጭ የሆነውን የጉጅሌ አገዛዝ መቅበር እንዳለብን ነው።
Monday, April 21, 2014
ሁለት : ባርያ ነጻ የሚወጣው መቼ ነው? እሱ ሲፈቅድ ነው? ወይስ ጌታው ሲፈቀድለት?
በፕሮፍ. መስፍን ወልደ ማርያም
መጋቢት 2006
አንድ በሀርቫርድ የኒቨርሲቲ ያጋጠመኝን ነገር መግቢያ ላድርገውና ልቀጥል፤ በአንድ ሴሚናር (የጥናት ውይይት) ላይ አንድ ጥቁር አሜሪካን ፕሮፌሰር ወደአሜሪካ በባርነት በመጡት አፍሪካውያን ላይ የተፈጸመውን ግፍ በመዘርዘር አስረድቶ አሁን ለእነሱ ልጆችና የልጅ ልጆች ካሣ መከፈል አለበት የሚል ክርክር አነሣ፤ ካሣውን የመክፈል ግዴታ የሚጣለው ማን ላይ ነው? ካሣውንስ የመቀበል መብት የሚሰጠው ለማን ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን ሳናነሣ ብዙ ሌሎች ጥያቄዎች ይኖራሉ፤ — እነዚያ ከአፍሪካ በባርነት ተይዘውና ተሸጠው የመጡት ሰዎች ዛሬ የሉም፤ እነሱ በባርነት ሞተዋል፤ ዛሬ በሕይወት የሚገኙት ጥቁር አሜሪካውያን ነጻነታቸውን አግኝተው ባለሙሉ መብት ዜጎች ሆነዋል፤ በአንጻሩ ደግሞ ለባሪያዎች ነጻነት የተጋደሉ ነጮች አሉ የእነዚህ ልጆች ከባሪያዎቹ ወይንስ ከጌቶቹ ወገን ይመደባሉ? ዛሬ ለልጆቻቸው ካሣ ይከፈል ማለት ልጆቹ የራሳቸውን ነጻነት ችላ ብለው ከአባቶቻቸው ባርነት ጋር እንዲቆራኙ ማድረግ አይሆንም ወይ? የባርነት ምልክቶችን ሁሉ ደምስሰው ነጻ ሰዎች ለመሆን የመጀመሪያው ግዴታ ራስን ችሎ በሁለት እግሮች መቆም ነው፤ ካሣ ክፈሉን ማለት አንደኛ ዋጋ ለማይሰጠው ነጻነት ዋጋን በማውጣት ማርከስ ነው፤ ከሰውነት ወደቤት እንስሳነት መውረድ ነው፤ ሁለተኛ በጌታና በባርያ መሀከል ያለው ግንኙነት መልኩን ለውጦ እንዲቀጥል መድረግ ነው፤ የውይይቱ ባለቤት እኔ ያቀረብሁትን ሀተታ እንዳላሰበበት ቢናገርም የእኔ ጥያቄ የተወደደ አልመሰለኝም፤ ካሣ ተቀባዮች ባርነታቸውን ካሣ ከፋዮች የባሪያዎች ባለቤትነታቸውን ጠብቀው እንደተቆራኙ መቀጠላቸው ባርነትን አያጠፋም፤ ለእኔ ጤናማ አልመሰለኝም።
ባሪያና ኃላፊነት አይተዋወቁም፤ ባሪያ ለገዛ ራሱ ኑሮም ቢሆን ኃላፊነት የለውም፤ ለምግቡም ሆነ ለልብሱ፣ ለመጠለያውም ሆነ ለቀብሩ ኃላፊነት የለበትም፤ ለሁሉም ነገር ኃላፊነቱ የጌታው ነው፤ ከባርነት መውጣት ማለት፣ ከባርነት መላቀቅ ማለት ነው፤ ለገዛ ራስ ሕይወት፣ ለገዛ ራስ ኑሮ ሙሉ ኃላፊነትን መሸከም ነው፤ ስለዚህም ከባርነት ወደነጻነት መሻገር ከግድዴለሽነት ወደኃላፊነት መሻገር ነው፤ ስለዚህም ከግዴለሽነት ወደኃላፊነት ሳይሻገሩ ከባርነት ወደነጻነት መሻገር አይቻልም! ኤልሪድጅ ክሊቨር የሚባል ጥቁር አሜሪካዊ በእስር ቤት ሆኖ የጻፈው (Soul on Ice) የሚል መጽሐፍ በዚህ ጉዳይ ላይ አፍአዊ ምልክቶችን ዘልቆ የሚገባ የነጻነትንና የባርነትን ባሕርያት ያሳያል፤ በአንድ በኩል በሴት ባርያና በወንድ ጌታ መሀከል ያለውን፣ በሌላ በኩል ደግሞ በወንድ ባርያና በሴት እመቤት በኩል ያለውን ግንኙነት በግላጭ ያወጣዋል፤ ባርነትን የባሕርዩ ያደረገ መገለጫው ለምንም ነገር ኃላፊነት የማይሰማው መሆኑ ነው፤ ለምንም ነገር ሳያስብ፣ በትእዛዝ ብቻ መመራት የተመቸው ባርያ ነው።

Saturday, April 19, 2014
ግድብ እያፈረሱ ጎርፍ መከላከል አይቻልም !!!
ዘረኛዉ የወያኔ ዘገዛዝ በ2002 ዓም “አኬልዳማ” የዛሬ ሁለት አመት ደግሞ “ጂሀዳዊ ሀረካት” የሚባሉ ሁለት አስጸያፊ ድራማዎችን ሰርቶ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማታለል የሞከረዉ ወያኔ በያዝነዉ ሳምንት መግቢያ ላይ ደግሞ ሌላ “የቀለም አብዮት” የሚባል ቂላቅል ድራማ ሰርቶ ለለዉጥ የተዘጋጀዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ቀለብ ለመስለብ ጉድ ጉድ ማለት ጀምሯል። ይህ በኪነጥበብ የፈጠራ ስራዉ ሳይሆን እንደማሞ ቂሎ በተፈጥሮዉ አስቂኝ የሆነ የዉሸት ድራማ የሚያሳየን ወያኔ በስልጣን ላይ ለመቆየት የማያደርገዉ ምንም ነገር አለመኖሩን ብቻ ነዉ። ይህንን ድራማ ከአኬል ዳማና ከጅሀዳዊ ሀረካት የሚለየዉ አንድ ነገር ቢኖር በዚህ ድራማ ዉስጥ ዋና ዋናዎቹ ተዋናንያን የተለመዱት የኢቲቪ ካድሬዎች ሳይሆኑ ሳይማሩ ምሁር የሚል ስያሜ የተሰጣቸዉ ሁለት ወጣት ካድሬዎችና የዉሸት እመቤት በመባል የምትታወቀዉ አዛዉንቷ እሟሆይ ሚሚ ስብሀቱ መሆናቸዉ ብቻ ነዉ።
ወያኔ በአኬልዳማ ድራማ ጥላሸት ለመቀባት የሞከረዉ ግንቦት ሰባትን የመሳሰሉ ለኢትዮጵያ የግዛት አንድነትና ለህዝቦቿ መብት መከበር በህይወታቸዉ የቆረጡትን የህዝብ ወገኖች ሲሆን፤ ጅሀዳዊ ሀረካት ደግሞ የአገርና የህዝብ ጠላት አድርጎ የሚያቀርበዉ የማምለክ መብታችን ይከበር ብለዉ በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ ያቀረቡትን የኢትዮጵያ እስልምና እምነት ተከታዮችን ነዉ። እንደተለመደዉ በዉሸት ታጅቦ ከሰሞኑ ብቅ ያለዉ ሦስተኛዉ የወያኔ ድራማ ደግሞ ከ85 በመቶ በላይ የሚያወራዉ ስለኢትዮጵያ ሳይሆን ዩክሬይን፤ ጆርጂያ፤ ሰርቢያና ኪርግስታን ዉስጥ ስለተካሄዱት ህዝባዊ የለዉጥ እንቅስቃሴዎችና ስለቀድሞዉ የቬኑዝዌላ መሪ ስለ ሁጎ ሻቬዝ ነዉ። የድራማዉ አቢይ መልዕክት ደግሞ የቀለም አብዮት ልማትን የሚጻረርና አገርን የሚጎዳ ስለሆነ ኢትዮጵያ ዉስጥ መሞከር የለበትም የሚል ነዉ። በዚህ የሞኞች ድራማ ዉስጥ ምሁርና ተንታኝ ሆነዉ የቀረቡትን የጂማ ዩኒቨርሲቲዉን መርከብ ነጋሽንና የኢትዮጵያ አለም አቀፍ የሰላምና የልማት ኢንስቲትዩት ባልደረባ የሆነዉን አቤል አባተን አደብ ገዝቶ የተከታተለ ሰዉ እነዚህ ወያኔዎች ሌላ ቢቀር የተማረ ሰዉ አጠገባቸዉ የለም እንዴ የሚያሰኙ ብዙ ነገሮችን መታዘብ ይችላል። በእርግጥም መርከብና ነጋሽና አቤል አባተ ኢትዮጵያ ዉስጥ ጭነት የተሸከመዉን አህያ እየመራ ወደ ገበያ የሚወስደዉ ገበሬዉ ሳይሆን በተቃራኒዉ ገበሬዉን እየመራ ወደ ገበያ የሚወስደዉ አህያዉ መሆኑን በማያወላዳ መልኩ አሳይተዉናል። እነዚህ ሁለት በጥንቃቄ ተመርጠዉ የመጡ የወያኔ ካድሬዎች እንዲህ ነበር ያሉት ።

Thursday, April 17, 2014
ሕወሓት እና መስእዋትነት
የሕዝብ ልጆችን መስእዋትነት በክህደት የተካ መንግስት
የታጋዩ እናት ..ልጅሽ በረሃ የገባው ተርቦ ነው እንጂ፤ ለኛ ብሎ አልወጣም.. እየተባለች እያለቀሰች ትገኛለች ፡፡ እነኛ ፈንጅ እርገጥ ካንተ መስዋእትነት በስተጀርባ ድል አለ፤ ብልጽግና አለ ይሉት የነበሩ መሪዎች አሁን በስልጣን ኮርቻቸው ላይ ተፈናጠው ፍጹም ጸረ-ዴሞክራሲና ሙሰኞች ሆነው ይገኛሉ፡፡ ተወዳዳሪ የማይገኝላቸው ጉበኞች ፣ የመሬት ሻጮች ፣ አገር ሻጮች ሆነው አርፈውታል፡፡
በትጥቅ ትግል ጊዜ አንድ አንድ ሰዎች የህወሓትን ስብስብ "የሰዎች ስብስብ" ነው ወይስ "ሰዎች መስለው መላእክት ናቸው የተሰባሰቡበት.. "የሚል ጥርጣሬ ውስጥ ሁሉ እስከመግባት ደርሰው እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ እንደ ዛሬ አያድርገውና በጊዜው የህዝብን ችግር ለመፍታት ህወሓት መስዋእትነት ለመክፈል ተወዳዳሪ አልነበረውም፡፡ የህወሓት መሪዎች ታጋዩ ለመስዋእትነት እንደተፈጠረና የሱ መስዋእትነት ሰላም፣ ብልጽግና፣ ለሁሉም ዜጋ እኩል የስራ እድል፣ ትምህርት እንደሚያገኝ፣ በህግ ፊት ሁሉም ዜጋ እኩል እንደሚሆን በማስተማርና በማሳመን ፈንጅ እንዲረግጥ አድርገውታል፡፡ የዚያ ዘመን ትውልድ የመስዋእት ትውልድ እንደሆነ ተቀብሎና አምኖ ታሪክ ሰርቶ አልፎዋል፡፡
አንድ ግዳጅ አለና ቅድሚያ መስዋእት ለመክፈል ዝግጁ የሆነ ማን ነው ተብሎ በሚጠየቅበት ጊዜ ልክ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ጥያቄ ሲቀርብላቸው ለመመለስ እኔ እኔ እያሉ እንደሚሽቀዳደሙ ሁሉ ታጋዩ ለአንዴና ለመጨረሻ ህይወቱን ለመክፈል ይሽቀዳደም ነበር፡፡ አሁን ያለው ሁኔታ ይመጣል ብሎ አልገመተማ፡፡ በዚሁ ጊዜ አድልዎ ተፈጸመ ሊባል የሚችለው ለመስዋእትነት ቅድሚያ አልሰጠም በማለት ታጋዩ ለበላይ አለቃው (ጠርናፊው) ሂስ ማቅረብ ነበር፡፡ እንደ ዛሬ የህዝብና የመንግስት ሃብት መውረር የሚባለ ነገር አልነበረም፡፡
ይድረስ ለብዙሃኑ የሠራዊቱ አባል ወገናችን!!
የመከላከያ ሚኒስትር በተሰኘው የውሸት ሥልጣን ላይ የተቀመጠው አድርባይ ሲራጅ ፈርጌሳ ለይስሙላው ምክር ቤት ባቀረበው ሪፓርት፣ “የመከላከያ ሚኒስትር የብሔር ተዋጽዖ የተመጣጠነ” እንደሆነ ገለፀ። እንደ ሰውየው ሪፓርት ከሆነ የመከላከያ ሠራዊቱ 29.46 በመቶ አማራ፣ 25.05 በመቶው ከደቡብ ብሔሮች የተውጣጣ፣ 24.45 በመቶ ኦሮሞ፣ 17.47 በመቶው ትግራይ እና የተቀሩት ክልሎች ድርሻ 4.17 በመቶ ነው። መረጃው የተቀናበረው በክልል ቢሆንም የቀረበው ግን በዘር ነው። “ተመጣጠነ” የተባለውም የክልሎች ተዋጽዖ ሳይሆን የዘር ተዋጽዖ ነው። ሠራዊቱን እንዲህ በዘር ሸንሽንኖ የስታትስቲክስ ጨዋታ መጫወት አሳዛኝም አሳሳቢም ነገር ነው። የሆነ ሆኖ ይህ መረጃ፣ መረጃ ነው ተብሎ ለሕዝብ ቀርቧል።
ይህንን መረጃ የሰማ ማሰብ የሚችል አዕምሮ ያለው ሰው የሚጠይቀው የመጀመሪያ ጥያቄ “የሠራዊቱ ስብጥር በተገለፀበት ዓይነት የመኮንኖቹም ስብጥር ለምን አልተገለፀም?” የሚል ነው። ይህ ጥያቄ በአስተዋይ ሰው አዕምሮ ውስጥ በተነሳነበት ፍጥነት ምላሽ ያገኛል፤ ምክንያቱም ምላሹ እዚያው እቁጥሮቹ ውስጥ አለ። የመኮንኖቹ ስብጥር ያልተነገረበት ምክንያት አብዛኞቹ መኮንኖች በ17.47 በመቶው በመሆናቸው ነው። ወደዚህ መምደሚያ የሚደርሰው አሳቢው ስለፈለገው ሳይሆን የመረጃው አቀራረብ አመክኖ (ሎጂክ) ወደዚያ ስለሚገፋ ነው። በዚህም ምክንያት በሲራጅ ፈርጌሳ አንባቢነት የቀረበው የህወሓት ሪፓርት በገዛ ራሱ ላይ ነው የተኮሰውም።
እኛ እንደ ሲራጅ ፈርጌሳ የዘር ስታትስቲክስ ውስጥ አንገባም፤ መልዕክታችን ለተገፋውና እየተበደለ ላለው ለመላው የሠራዊቱ አባል ነው።

Wednesday, April 16, 2014
ነገረ-ኢትዮጵያ ቅፅ 1 ቁጥር 8 (PDF)
ነገረ ኢትዮጵያ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮችን ይዛ ቀርባለች፡፡ በተለያየ ምክንያትጋዜጣዋን ኮፒ በዕለቱ ያላገኛችሁ ይኸው መረጃ ይደርሳችሁ ዘንድ በፒዲኤፍ (PDF) ለቀናታል፡፡
- ፕሮፈሰር አለማየሁ፣ ታምራት ታረቀኝ፣ ግርማ ሞገስና ታዲዮስ ታንቱ ጥልቅ ትንታኔዎችን ሰጥተውባታል፡፡
- የተማሪዎች የሰላማዊ ሰልፍ ማቆም አድማ፣ የአርሶ አደሮች ሰቆቃና ሌሎችም አዲስ ወሬዎች ተካተውባታል፡፡
- በላይ ማናዬ የብሄርፌደራሊዝሙን ቅዝምዝሞሽ ይተነትንልናል፡፡
- ዮናታን ተስፋየ ለምን ፈራን ይለናል፡፡
- እያስፔድ ተስፋዬ የስርዓቱን ሰለባዎች (ከማሞ መዘምር እስከበቀለ ገርባ ዳስሷል፼፡፡ -
- ጌታቸው ሺፈራው ኢህአዴግ ምንም እንደማያሟላ ይሞግታል፡፡
- ብርሃኑ ተክለ ያሬድ የእስር ቤት ትዝታውን አቅርቦባታል፡፡ ወጣቱ አቃቤ ህግ የፍትህ ስርዓቱ ፍትህ ያስፈልገዋል ብሏል፡፡
- የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ስራ አስኪሃጅ በደሎች ተዘርዝረውበታል፡፡

Tuesday, April 15, 2014
ዶሮዋን አታታሏት፤ በመጫኛም አትጣሏት!!
በማስረሻ ማሞ (ሆላንድ)
በአንድ አገር ላይ አብዮት የሚከሰተው ምን ሲኾን ነው? አብዮቶችስ ወደ ዐመጽ የሚቀየሩት ምን ዐይነት ተግዳሮት ሲገጥማቸው ነው? አብዮት በአንድ አገር ላይ ሥር ነቀል ለውጥ ለማምጣት ያለው አበርክቶትስ ምንድን ነው?
የየትኛውም አብዮት መነሻ ምክንያቱ ጭቆና ነው። የኢ-ፍትሃዊነት ሥር መስደድ ነው። የመልካም አስተዳደር እጦት መስፋፋት ነው። የአንድ አገር ማኅበረሰብ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ በጥቂት ጉልበተኞች ቁጥጥር ሥር መግባት ውጤት የሚፈጥረው እልህ ነው። በተቀመጠው ሕገ-መንግሥታዊ መስፈርት መሠረት መንግሥት ዜጎችን በእኩልነት መምራት ሲሳነው የሚፈጠር የታመቀ ጭቆና የሚፈነዳበት ክስተት ነው።
በዚህ ሰዓት ስለ “ቀለም አብዮት ሰላባዎች” ዶክመንታሪ ፊልም አሰርቶ የሚያሳየን ኢሕአዴግ ባንድ ወቅት አብዮተኛ ነበር። ዛሬ አብዮት ምን ያህል አስከፊ ነገር ሊያመጣ እንደሚችል በእነ ዩክሬን በኩል እያሳየ ሊያስረዳን ይሞክራል። የዚህ አብዮት አራማጆች ደግሞ ምዕራባውያን (የኒዮ ሊበራል አጀንዳ አራማጆች) ናቸው ይለናል። በዩክሬን እና በመሰል አብዮቶች ውስጥ ምዕራባዋያን እጃቸውን አይጠልቁም ማለት አይቻልም። ምዕራባውያን ብቻ ሳይኾኑ፤ የእነሱው ተቃራኒ ርዕዮተ ዓለም የሚያራምዱት እነ ሩስያም ባመቻቸው መንገድ እጃቸውን ይነክራሉ። ይኼ በዓለም ፊት የበላይነትን ለማስረገጥ የሚደረግ የሥልጣን ጫዎታ ነው። ዶሮዋን አታታሏት፤ በመጫኛም አትጣሏት!!
በዚሁ የኢቲቪ የቀለም አብዮት ሰለባዎች ዶክመንታሪ ላይ ሁለት አዳዲስ ፊቶች ዐየን። መርከብ ነጋሽን እና አቤል አባተን። ርግጥ ነው ፌስቡክ ላይ ይታወቁ ነበር። የሚሰጡትን ትንታኔ ልብ ብዬ አደመጥሁት። ሐሳባቸው እንደተቆረጠባቸውም ገመትሁ። ከፊት ለፊታቸው የተደቀነው የኢቲቪ ካሜራ እንደልባቸው የሚያስቡትን ሁሉ እንዲያፈሱ የሚያደርግ እንዳልኾነም እሙን ነው። ራሳቸውን በደንብ አድርገው በሴንሰርሺፕ ያጠሩትም መሰለኝ። ጥሩ ጎኑ እንዲህም መናገር የሚችሉ ወጣት ልጆች መኖራቸው ነው። ትንታኔያቸው “የቀለም አብዮት ማሰብም ኾነ እንዲደረግ መመኘት ኢትዮጵያን እንደ ዩክሬን ያደርጋታል” ለሚለው የፊልሙ ጭብጥና የመንግሥት አጀንዳ ሰለባ ከመኾኑ በቀር።

"አዲስ አበባ የኦሮምያ ናት" የሚለውን ቀልድ ተውትና ለእውነተኛ የነጻነት ትግል ተነሱ!
በፋሲል የኔያለም
ይደረስ ለጥቂት የኦሮሞ ሊህቃን
የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ትግል በሁለት አቅጠጫዎች የሚካሄድ ነው ። አንደኛው ከህወሃትና አጋሮቹ ጋር የሚካሄደው የሽቅብ (vertical) ትግል ሲሆን ሌላው ደግሞ ተቃዋሚዎች እርስ በርስ የሚያካሂዱት የአግድሞሽ (horizontal) ትግል ነው። የአግድሞሹ ትግል ሲዳከም የሽቅብ ትግል ይጠነክራል፣ የአግድሞሹ ትግል ሲጠናከር ደግሞ የሽቅብ ትግል ይዳከማል። ለ23 ዓመታት የተካሄደው የነጻነት ትግል ፍሬ ሊያፈራ ያልቻለው በከፊል የአግድሞሹ ትግል ሙሉ በሙሉ ሊጠፋ ወይም ሊዳፈን ባለመቻሉ ነው። ለወደፊቱም ቢሆን የአግድሞሹ ትግል እየተዳከመ ካልሄደ ሽቅብ የሚካሄደው ትግል ሊጠናከር አይችልም። ህወሃትና አጋሮቹ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተዳክመው የሚገኙበት ጊዜ ላይ እንገኛለን። ይህን የተዳከመ ሃይል በካልቾ መትቶ ለማባረር የአግድሞሹን ትግል በማዳከም የሽቅብ ትግሉን ማጠናከር ያስፈልጋል፤ የአግድሞሹ ትግል ሊዳከም የሚችለው ደግሞ ዋነኞቹ ተቃዋሚዎች ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ፈርመው የያዙትን ጥይት ወደ ሽቅብ ለመተኮስ መስማማት ሲችሉ ብቻ ነው።
ወደ ሽቅብ የሚደረገውን ትግል ከሚያዳክሙ ሃይሎች መካከል በተቃውሞ ጎራ ተሰልፈናል የሚሉ የተወሰኑ የኦሮሞ "ሊህቃን" በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። እነዚህ ሊህቃን ምን እንደሚፈልጉ አይታወቅም። አቋማቸው በየጊዜው እንደ እስስት የሚለዋወጥ በመሆኑም እንዲህ ናቸው ብሎ አፍን ሞልቶ ለመናገር አይቻልም። እነሱን አምኖ አብሮ ለመታገልም በጣም አስቸጋሪ ነው፤ መቼና የት ቦታ ላይ እንደሚለወጡ አይታወቅም፤ ከእነሱ ጋር አብረው ለመስራት የሞከሩ ድርጅቶች ሁሉ እስከዛሬ አልተሳካላቸውም። እነዚህ ጥቂት ሊህቃን የኦሮሞን ህዝብ ፍላጎት የሚያውቁ አይመስለኝም። መሽቶ በነጋ ቁጥር አቋማቸውን በብርሃን ፍጥነት ሲለዋዉጡ የምናየውም ለዚህ ይመስለኛል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እነዚህ ጥቂት ሊህቃን የመገንጠል አጀንዳቸውን በመተው ለነጻይቷ አገር መወለድ እንደሚሰሩ ሲነግሩን ተስፋ አድርገን ነበር፤ ነገር ግን ሰሞኑን የሚጽፉትና የሚናገሩት አሁንም ካረጁበት የመገንጠል አላማ ፈቅ አለማለታቸውን የሚያሳይ ነው። በተለይ የአዲስ አበባ ከተማን አዲስ ካርታ ለመቃወም የሚያነሱት መከራከሪያ ልብን ዝቅ የሚያደርግና የሰዎቹን እውነተኛ ፍላጎት ገሃድ የሚያወጣ ነው።
Monday, April 14, 2014
አንድ ባርያ ነጻ የሚወጣው መቼ ነው? ሲፈቅድ ነው? ወይስ ሲፈቀድለት? (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)
በአለፈው ሳምንት (ፋክት ቁጥር 36) ወይዘሮ መስከረም የተለያዩ መጻሕፍትን በመጥቀስ በሴቶች ላይ ያለውን መጥፎ ጫና በደንብ ያስመሰከረች ይመስለኛል፤ ግን እኮ በሴቶች ላይ ያለው ጫና የቆየ፣ ክፉና ጎጂ መሆኑን ማንም ያውቀዋል፤ ቁም-ነገሩ ያለው ከዚያ የባህል ጭነት በራስ ጥረት ወጥቶ፣ ነቀፌታንም ሆነ እርማትን ለመቀበል ሳይፈሩና ሳያፍሩ እንደመስከረም በአደባባይ ሀሳብን በመግለጽ በአገርና በወገን ጉዳይ መሳተፍና ሌሎችም እንዲሳተፉ የተቻለን ሁሉ ማድረጉ ላይ ነው፤ ለዚህ ነው ይህንን መልስ የምጽፈው፤ ወይዘሮ መስከረም በአጋጠሟትና በምታያቸው እንቅፋቶች ላይ ማተኮርዋ እንደርስዋ መንፈሳዊ ወኔው የሌላቸውን ያስፈራራቸዋል እንጂ አያበረታታቸውም፤ የማንንም አፍአዊ ጫና ተቋቁመው በራሳቸው የውስጥ ኃይል እንዲመሩ እናድርግ።
አንድ መጽሐፍን በመጥቀስ ወይዘሮ መስከረም የሚከተለውን ጽፋለች፡–
ፈጣሪ የሠራውን ውጫዊ ገጽታን ማሽሞንሞን በቂ እንደሆነ ሲነገራት የኖረች ሴት፣ በምን ተነሳሺነት አእምሮዋን የሚመግብ እውቀት ልትሻ ትችላለች? … በልጅነት እውቀትን ወደመሻት ያልተገፋ ማንነት በጉብዝና ወራት አላዋቂ በመሆን ቢወቀስ ትርጉም አይኖረውም፤ …››
ወይዘሮ መስከረም ሔዋን ሲነገራት የማትሰማ የመጀመሪያዋ ሰው (ልብ በሉ ሴት አላልሁም፤) መሆንዋን እንዴት እስከዛሬ ሳታውቅ ቀረች? ባለመጽሐፉም ይሁን መስከረም የሔዋንን ታሪክ ሳያነሡ መቅረታቸው መሠረታዊ ስሕተት ነው፤ በተጠቀሱት ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ውስጥ አንድም እውነትን የሚመስል ነገር የለም፤ መስከረም ‹‹የሔዋን ዘር›› ከማለት በፊት የሔዋንን ሥራ ቆም ብላ ብታስታውስ የጠቀሰችውን መጽሐፍ እኔ እንደምነቅፈው ትነቅፈው ነበር፤ የሔዋን ታሪክ የሚነግረን የሚከተለውን ነው፡ ‹‹ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፣ ለጥበብም መልካም እንደሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው፤ እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ፤ የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ፤›› ዘፍ. 3

የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ እና የዲያስፖራውን ሚና በተመለከተ በኖርዌይ ኦስሎ ሕዝባዊ ውይይት ተካሄደ
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ
በዲምክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አዘጋጅነት አፕሪል ቅዳሜ 12/2014 በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ እና የዲያስፖራውን ተሳትፎ በተመለከተ ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ ተካሄደ:: በሕዝባዊ ስብሰባው ላይ ቁጥራቸው ወደ ሁለት መቶ የሚጠጉ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች ከኦስሎ እና ከተለያየ ከተማ በመምጣት በስብሰባው ላይ የተገኙ ሲሆን የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነት እና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አመራር አባል አቶ ቡዙነህ ፅጌ የስብሰባው ተጋባዥ እንግዳ በመሆን ሰፋ ያለ ንግግር አድርገዋል::
ሕዝባዊ ስብሠባው በኖሬጅያውያን የሰአተ አቆጣጠር ከቀኑ 15:00 እስከ ምሽቱ 21:00 ሰዓት የተካሄደ ሲሆን የዲሞክራሲያዊ ለለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አቢ አማረ በኢትዮጵያ ውስጥ በወያኔ አረመናዊ ስርአት በጭካኔ በግፍ ለተገደሉ እና በተለያዩ አስር ቤቶች በፖለቲካ ኣስተሳስባችው ምክንያት ያለወንጀላች የሚስቃዩ ውድ ኢትዮጵያዊን ወገኖቻችን በማስብ በዚሁ ዘረኛ ቡድን አስቃቂ የኣካል ጉዳት ለተፈጸባቸው ኢትዮጵያዊን የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማስደረግ ስብሰባውን አስጀምረውታል::
በመቀጠለም አቶ ዮሀንስ አለሙ የዴምክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሊቀመንበር የመግቢያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸው ስለ ዲምክራሲያዌ ለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አመሰራረት እና ስለ ድጋፍ ድርጅቱ አላማ በማብራራት የድጋፍ ድርጅቱ በአሁኑ ሰአት በሀገር ቤት በሰላማዊ ትግል የወያኔን መንግስት ለመጣል እየታገሉ ያሉትን የፖለቲካ ድርጅቶችን እየረዳ እንደሚገኝ እና ከሀገር ውጭ ደግሞ የወያኔን መንግስት በሁለገብ ትግል ለማስወገድ እየሰራ ያለውን የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነት እና የዲሞክራሴ ንቅናቄ የፖለቲካ ድርጅትን በግንባር ቀደምነት እየረዳ እንዳለ በመግለጽ የወያኔን ዘረኛ ስርአት ለመጣል ሁሉም ሰው አስተዋጿ ማድረግ እንደሚጠበቅበት እና ማንኛውም ኢትዮጵያዌ ዜጋ በሀገራችን የጋራ ጉዳይ ስለሆነው የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ሀሳብ በመለዋወጥ ፣በመካከላችን ያሉትን ማንኛውንም የሃሳብ ልዩነቶች ወደ ኋላ በመጣል ፣ በመቻቻል፣ ሀገር እያፈረሰ እና ሕዝብ እያዋረደ ያለውን የዘረኛውን የወያኔን መንግስት ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሁለገብ ትግል ለማስወገድ መረባረብ እንዳለበት አጽኖት ሰጥተው ንግግር አድርገዋል::

Sunday, April 13, 2014
የኢቲቪ "የቀለም አብዮት" ስጋት ሲፈተሽ!
ኢቲቪ "የቀለም አብዮት" ዝግጅት (ስጋት) አቀረበልን። ግን የኢህአዴጉ ኢቲቪ ለምን የቀለም አብዮት ጉዳይ አጀንዳ አደረገው? የቀለም አብዮት ጉዳይ ለምን ዝግጅት አስፈለገው? አዎ! "የቀለም አብዮት" ጉዳይ አጀንዳ የሆነው የቀለም አብዮት (በትክክለኛው አጠራሩ ህዝባዊ ዓመፅ) ስጋት ስላለ ነው። የህዝብ ዓመፅ (የቀለም አብዮት) ለምን ስጋት ሆነ? ኢህአዴግ ለምን ህዝባዊ ዓመፅን ሰጋ? ተግባሩ ስለሚያውቅ ነው።
የኢህአዴግ መንግስት ዓፋኝ መሆኑ አውቀዋል፣ ተገንዝበዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ዓፈና እንደማያስፈልገው መገንዘቡም የኢህአዴግ መንግስት የተገነዘበ ይመስለኛል። ህዝብ ስለ ዓፈና ግንዛቤ ካለው ነፃነት መፈለጉ አይቀርም። ነፃነት የፈለገ ህዝብ በማፈን መግዛት እንደማይቻል ኢህአዴጎችም የተገነዘቡት ይመስላል።
አሁን ኢህአዴግ የህዝብ ድጋፍ እንደሌለው እየተረዳ ነው። የኢህአዴግ ዓላማ ስልጣን እስከሆነ ድረስ በህዝብ ባይመረጥም የህዝብን ድምፅ አጭበርብሮ የተመረጠ አስመስሎ በስልጣን ለመቆየት ጥረት ማድረጉ አይቀርም። ነፃነት የፈለገ ጭቁን ህዝብ ድምፁን ለማስከበር ጥረት ሲያደርግ የህዝብ የነፃነት ትግል ከኢህአዴግ የስልጣን ፍላጎት ጋር ይጋጫል። ግጭቱ ህዝባዊ ዓመፅ ሊወልድ ይችላል የሚል ስጋት አድሮበታል። ለዚህም ነው የቀለም አብዮት (ህዝባዊ ዓምፅን) አጀንዳ አድርጎ ዝግጅቱ (ይቅርታ ስጋቱ) ያቀረበልን።
በኢቲቪ ከቀረበልን ዝግጅት በመነሳት ኢትዮጵያ የቀለም አብዮት (ህዝባዊ ዓመፅ) ያሰጋታል። ምክንያቱም የኢህአዴግ መንግስት ህዝባዊ ዓምፅን ባያሰጋው (ባይፈራ) ኑሮ በምስራቅ አውሮፓና ላቲን አሜሪካ ስለተከናወኑ የቀለም አብዮቶች ባላሳሰበው ነበር። ኢቲቪዎች "ምዕራባውያን የራሳቸው ጥቅም ለማሳካት ሲሉ በሌሎች ሀገሮች ህዝባዊ ዓመፅ እንዲቀሰቀስ ያደርጋሉ" አሉን። በዓለም አቀፍ ግኑኝነት ማንኛውም ሀገር የራሱ ብሄራዊ ጥቅም ለማስከበር ይሰራል። ምዕራባውያን ይሁኑ ምስራቃውያን የየራሳቸው ጥቅም ለማስከበር ነው የሚሰሩት። ይህ ግልፅ ነው።
Saturday, April 12, 2014
አወዛጋቢዉ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት አዋጅ ሥራ ላይ ዋለ
ባለፈው ዓመት መጨረሻ በአዲስ መልክ በአዋጅ የተቋቋመውና ዜጎች መረጃ እንዲሰጡ የሚያስገደድደው ብሔራዊ የመረጃ ደህንነት አገልግሎት አዲሱን አዋጅ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን ምንጮች ገልጸዋል።
በ1987 ዓ.ም የደህንነት የኢሚግሬሽንና ስደተኞች ጉዳይ ባለስልጣን በሚል ስያሜ ተቋቁሞ በስራ ላይ የነበረው ይህው ተቋም የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ ለመወጣት እንዲችል በሚል ባለፈው ዓመት አዲስ የማሻሻያ ረቂቅ ለፓርላማው ቀርቦ መጽደቁ ይታወሳል።
አዲሱ አዋጅ ካስፈለገባቸው ምክንያቶች መካከል በዓለም አቀፍ ደረጃ በመረጃና ደህንነት ዙሪያ የስጋቶች ምንጭ እና የመከላከያ ስርዓትና አሰራር እየተለዋወጠ በመምጣቱ፣በአገር ውስጥ የጸረ ሽብርተኝነት እና የበረራ ደህንነት የማስጠበቅ የመረጃና ደህንነት ተጨማሪ ሃላፊነቶች በአገልግሎቱ ስልጣንና ሃላፊነት ውስጥ እንዲካተቱ እንደተደረገ ያገኘነው መረጃ ይጠቅሳል።
በዚህ አዋጅ መሠረት በፌዴራልም ሆነ በክልሎች ደረጃ ሌላ የመረጃና ደህንነነት መ/ቤት ማቋቋም የተከለከለ ሲሆን የመ/ቤቱ ገቢና ወጪ ሂሳብ ይፋዊ በሆነ መንገድ በኦዲተር እንዳይመረመርና ሂሳብ ነክ ጉዳዮች ለጠ/ሚኒስትሩ ብቻ ሪፖርት እንደሚያደርግ ደንግጓል። ለመ/ቤቱ ከውጪ ተገዝተው የሚገቡና በተለያየ ምክንያት ለስራ ተብለው የሚወጡ ዕቃዎች ጉምሩክ ሳያያቸው እንዲወጡና እንዲገቡ የተደነገገ ሲሆን የደህንነት ሠራተኞች ሃብት ምዝገባ በጸረ ሙስና ኮምሽን ሳይሆን በተቋሙ እንደሚከናወን ይገልጻል።

ዲያስፖራዉ ለወገኖቹ የሚልከዉ ገንዘብ የኢትዮጵያ ቀዳሚ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ መሆኑ ታወቀ
ኢትዮጵያ በ2005 በጀት ዓመት ምረቶቿን ለዉጭ ገበያ ልካ ካገኘችዉ ገቢ ይበልጥ በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለወገኖቻቸዉ ከሚልኩት ገንዘብ ያገኘችው ገቢ እንደሚበልጥ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተገኘ የጹሑፍ መረጃ አመልክቷል። ይህ አክራሪ ወይን አገሩን የከዳ ዳያስፖራ እየተባለ በወያኔና በደጋፊዎቹ የሚጠላዉ ዳያስፖራ በብዙ ቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዝብ ወደ አገሩ በመላክ የዳያስፖራዉ ችግር የወያኔ ዘረኝነት ነዉ እንጂ አገሩና ወገኑ አለመሆኑን በተግባር አሳይቷል ሲሉ አንድ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪ ተናግረዋል።
ከወያኔ ባለስልጣኖች የተገኘዉ መረጃ እንደሚያሳየው በ2005 በጀት ዓመት አገሪቱ ከኤክስፖርት 3.1 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ያገኘች ሲሆን ኢትዮጵያውያን ከውጭ ከሚልኩት ገንዘብ ደግሞ 3 ቢሊዮን 9 መቶ ሚሊዮን ዶላር አግኝታለች። በ2004 በጀት ዓመትም ከሐዋላ እና ከኤክስፖርት ያገኘቸው ገቢ ተመሳሳይ ማለትም እያንዳንዳቸው 3.2 ቢሊየን ዶላር መሆኑን መረጃው ያሳያል።መረጃው የሐዋላ ገንዘብ በፍጥነት እያደገ ሲመጣ በአንጻሩ አገሪቱ እንደቡና ፣የቅባት እህሎችና ጥራጥሬና የመሣሠሉትን በመላክ የምታገኘው ዓመታዊ ገቢ እያሽቆለቆለ መምጣቱን ያሳያል።

ወ/ሮ አስቴር ማሞን ሹመት አገኙ
ወያኔ መልምሎ ያቀረበለትን የደካማ ግለሰቦች ሹመት ፓርላማ እየወሰደ አጽድቁልኝ ከማለት ሌላ ይህ ነዉ ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ስልጣን የሌላዉ ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ በያዝነዉ ሳምንት ማብቂያ አካባቢ የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበርና የጽ/ቤት ኃላፊ የነበረችዉን ወ/ሮ አስቴር ማሞን በምክትል ጠ/ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር እንድትሆን ያቀረበዉን ሹመት ፓርላማው ተቀብሎ አጽድቋል።
የኦህዴድ ሊቀመንበርና የክልሉ ፕሬዚደንት ከነበሩት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ሞት በኃላ ኦህዴድ ባደረገው የሥልጣን ሽግሽግ አቶ ሙክታር ከድር ከምክትል ጠ/ሚኒስትርነት ተነስቶ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት ሆኖ መሾሙ የሚታወስ ሲሆን ወ/ሮ አስቴር ማሞ ደግሞ በአቶ ሙክታር እግር ተተክታለች።
ወ/ሮ አስቴር ማሞ በጰጉሜ ወር 2002 ዓ.ም በተካሄደው የኦህዴድ ጉባዔ ከድርጅቱ ሥራ አስፈጻ ኮምቴ አባልነት አሰናብቷት የነበረ ሲሆን በመጋቢት ወር 2005 ዓ.ም የተካሄደው የኦህዴድ ጉባዔ አባዱላ ገመዳን፣ ኩማ ደመቅሳንና፣ግርማ ብሩን ከፓርቲው ሥራ አስፈጻሚነት ሲያሰናብት የወያኔ ታማኝ ሎሌ መሆኗ የሚነገርላት ወ/ሮ አስቴር እንደገና መመረጧ የሚዘነጋ አይደለም። የአቶ አለማየሁ አቶምሳን ሞት ተከትሎ በቅርቡ ፓርቲው ባደረገው ሽግሽግ አስቴር ማሞ ከኦህዴድ ጽ/ቤት ኃላፊነቷ በተጨማሪ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚደንት ሆና ተሹማለች።

የወያኔ ፖሊሶች ከ20 በላይ የቦዲ ብሄረሰብ ተወላጆችን መግደላቸዉ ተሰማ
ነብሰ ገዳዮቹ የወያኔ ጸጥታ ኃይሎች በቅርቡ በቦዲና በኮንሶ ብሄረሰቦች መካከል የተከሰተዉን ግጭት እናበርዳለን በሚል ሰበብ በወሰዱት የማጥቃት እርምጃ ከሃያ በላይ የቦዲ ብሄረሰብ ተወላጆችን ሳይገድሉ እንደልቀረ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኝ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ አስታወቀ። የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት ምክትል ሊቀመንበርና የዞኑ ሰብሳቢ አቶ አለማየሁ መኮንን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ በቦዴዎችና በኮንሶች መካከል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የፌደራል ልዩ ሃይል በወሰደው እርምጃ ወደ 29 የሚጠጉ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለድርጅታቸው ሪፖርት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
የሟቾችን ስም ዝርዝር በማጠናቀር ላይ ሲሆኑ ሰሞኑን ይፋ እንደሚያደርጉም ምክትል ሊቀመንበሩ ተናግረዋል ሆስፒታል ሄደው የቆሰሉትን ሰዎች መጎብኘታቸውና ማነጋገራቸውን የሚናገሩት አቶ አለማየሁ ፣ ከሁለቱ በስተቀር ሌሎች ወደ 6 የሚጠጉ ሰዎች በፌደራል ፖሊስ ጥይት መቁሰላቸውን እንደገለጹላቸው ተናግረዋል።

ፋሽስቱ ወያኔ በንጹሃን ዜጎች ላይየሚያደርሰውን በደል በተጠናከረ ሁኒታ መቀጠሉ ተሰማ
በወልድያከተማከ50 በላይየሚሆኑግለሰቦች የሚኖሩበትቤትበኢንቨስትመንትስምለአገዛዙ ቅርበት አለው ለተባለ ባለሀብትመሰጠቱን ተከትሎበ 24 ሰዓትውስጥቤታችሁን ለቃችሁ ውጡ መባላቸውን በመቃወማቸው የወያኔ ቅጥረኛ የፌደራል ፖሊሶች ግለሰቦችን ማሰራቸው ተሰማ። የከተማውከንቲባፀሐዩመንገሻ፣የዞንብአዴንሀላፊአበባውሲሳይእናሌሎችጉዳዩየሚመለከታቸውየአገዛዙ አገልጋይ ካድሬዎች ሲጠየቁይህጉዳይከአቅማችንበላይስለሆንአይመለከተንምማለታቸውህብረተሰቡንማስቆጣቱ ተዘግቧል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሶማሌ ክልል ረር ባሬ ዉስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት 16 ሰዎች መታሰራቸውን የአገር ውስጥ ምንጮቻችን በላኩልን ዜና ገለጹ። ከአስተዳደርጋርበተያያዘያነሱዋቸውንጥያቄዎችተከትሎከፋሽስቱ የወያኔ አገዛዙ ጋር ከፍተኛ ግጭት ውስጥ የሆኑት የሶማሌ ክልል የየረርጎሳአባላትውስጥ16 ሰዎች መታሰራቸው ታውቋል።
ሲራጅ ፈርጌሳ በአንድ ዘር ቁጥጥር ስር የሚገኘዉን ሰራዊት የብሔር ተዋጽኦ አደነቀ
የጉጅሌው ወያኔ አገዛዝ ያረቀቀው የይስሙላ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 87 የአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የብሔሮች፣ የብሔረሰቦችና የሕዝቦችን ሚዛናዊ ተዋጽኦ ያካተተ መሆን እንዳለበት የሚደነግግ ሲሆን አገዛዙ ላለፉት 19 ዓመታት ራሱ ህዝብን በማጭበርበር ረጅም እድሜ ለመግዛት ይረዳው ዘንድ ያረቀቀውን የህገ መንግስቱን አንቀጽ በመጣስ በተለይም በመከላከያው አመራር ላይ የአንድ ብሄር የበላይነት በማስፈን ስልጣኑን ለማስጠበቅ እየሰራ መሆኑ የሚታወቅ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የጉጅሌው ወያኔ የመከላከያ ሚኒስተር ተብየ ሲራጅ ፈጌሳ ለወያኔው አሻንጉሊቱ ፓርላማ የ2006ን ሪፖርት ዋቢ በማድረግ የሠራዊቱ የብሔር ተዋጽኦ እየተመጣጠነ መምጣቱን በመደስኮር ለማስረጃነትም ከአጠቃላይ የመከላከያ ሠራዊቱ አባላት የአማራ ብሔር ተዋጽኦ 29.46 በመቶ በመሆን በቀዳሚነት እየመራ ይገኛል ሲል የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ተዋጽኦ 25.05 በመቶ በመሆን በሁለተኛ ደረጃ፤ የኦሮሞ ብሔር 24.45 በመቶ የሦስተኛ ደረጃን ይዟል፤ የትግራይ ብሔር ተዋጽኦ ወደ 17.47 በመቶ በመውረድ በአራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ሲል ዳግም ህዝብን ለማደናገርና ለአገዛዙ እንዲመች ተደርጎ በውሸት የተቀሸረ የቅጥፈት ሪፖርቱን አሰምቷል።
የጉጅሌው ወያኔ አገዛዝ በመከላከያ ሰራዊቱ የአመራሩ ክፍል የብሄር ተዋጽኦ እስካልተመጣጠነ ድረስ ታች ባለው የሰራዊት አባል የቁጥር ጋጋታ ብቻ ‹‹ተዋጽኦውን አሟልተናል›› ብሎ መደስኮር ዳግም አገዛዙ ለህዝብ ያለውን ንቀት ከማሳየቱ ውጭ ሌላ ምንም ትርጉም አይሰጥም። የመከላከያ ሰራዊቱ አመራር በአንድ ብሄር የተሞላና የብሄር ተዋጽኦን በማማከል የተገነባ አለመሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው።

ኢትዮጵያ ዉስጥ የሰብአዊ መብት አያያዝ በከፍተኛ ሁኔታ እየዘቀጠ ነዉ
ለኢትዮጵያው ፋሽስታዊ አገዛዝ እጅግ ከፍተኛውን የእውቀት፣ የአይነትና የገንዘብ እገዛ በማድረግ የሚታወቀው የአውሮፓ ሕብረት ፓርላማ አገዛዙ በሀገሪቱ እጅግ የገዘፈ የሰብአዊ መብት ረገጣ ያሰፈነ መሆኑን ምስክሮችን አስቀርቦ በማዳመጥና የአባላቱን የግል ትዝብት በመጨመር ከፍተኛ ትችት መሰንዘሩ ተሰማ።
በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙትን የማእከላዊና ቃሊቲ ወህኒ ቤቶችን ጨምሮ በኦጋዴንና በሌሎችም የሀገሪቱ ክፍሎች አገዛዙ እያደረሰው ያለውን አፈና፣ ግርፋት፣ ያለምክንያት ማሰር፣ ግድያና አስገድዶ መድፈር ምስክርነት በዝርዝር ያደመጠው የአውሮፓ ሕብረት ፓርላማ በገፍ እያፈሰስን ያለነው አመታዊ የገንዘብ እገዛም በትክክለኛው መንገድ እየዋለ ካለመሆኑም በተጨማሪ ለሙስና የተጋለጠ ነው በማለት አስረግጦ ተወያይቷል።
ኢትዮጵያ ከፍተኛውን የሰብአዊና የልማት ርዳታ ከሚወስዱት ሀገራት ቀዳሚዋ መሆኗን በአንክሮ የገለጸው ይህ የአወሮፓ ሕብረት ፓርላማ ውይይት፤ ይህ ሁሉ እገዛ ያላግባብ በዘፈቀደ ሲውል፣ ለሙስና ሲጋለጥና ከዚያም በላይ ከታለመለት ዓላማ ውጭ ለአገዛዙ የፖለቲካ ፍጆታ ለፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ማሰባሰቢያነት እንዲሁም ተቃዋሚዎችን ለማጥቂያነት ሲውል በአዲስ አበባ የሚገኙ የምራባዊያ ሀገሮች ዓለማቀፍ ተቋማትም ሆኑ ኤምባሲዎቻቸው ምንም አለማለታቸውና ነገሩን እንደቀላል መተዋቸው በጣም አሳፋሪ ነው ይህ ደግሞ ከአውሮፓ ሕብረት ህግና መመሪያ ተቃራኒ ነው ሲል አማሯል።

ደሴዎች ሆይ ! ቁጭታችሁ ቁጭታችን፤ ብሶታችሁ ብሶታችን ነው።
በደሴ ሚሊየኖች የመሬት ባለቤት እንሁን ሲሉ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ጩኽዋል።መሬት ክብር ነው። መሬት ሃብት ነው። መሬት ማንነትም ነው። ይህ ክብር፤ ይህ ሃብት፤ ይህ ማንነት ከህዝቡ ላይ ተወስዷል። በኢትዮጵያ ውስጥ የመሬቱ ባለቤት ህወሃት-ኢሕአዴግ ነው። ይሄ ቡድን መሬቱን ብቻ ሳይሆን ህዝቡንም “የእኔ ንብረት ነው” የሚል አስተሳሰብ አሳድሯል። በዚህ አስተሳሰቡም የወደደውን ሲተክል፤ የጠላውን ሲነቅል ብዙ ዓመት ኑሯል። ከዝያም “ህዝቡ ተኛ ብንለው ይተኛል፤ ተነስ ስንለውም ይነሳል” እያለም ይሳለቃል። እውነት ነው መሬት አልባ የሆነ ዜጋ ተኛ ሲባል ከመተኛት፤ ተነስ ሲባልም ከመነሳት ሌላ ምን የተሻለ አማራጭ አለው? ለዚህ አማራጭ ላጣ ህዝብ አማራጭ ይኖረው ዘንድ የምትተጉ ወገኖችን ከልብ እናደንቃለን።
የደሴውን ሰልፍ ያዘጋጃችሁ ዜጎች ተስፋ አለመቁረጣችሁ ይደነቃል። ከፍ አድርጋችሁ የጮኻችሁት ጩኽት በኢትዮጵያ ውስጥ ከዳር አሰክ ዳር ተስተጋብቷል። ይሄን ድምፅ ያልሰማው ህወሃት-ኢሕአዴግ ብቻ ነው። ይሄ ቡድን “ማን አባቱ ይጠይቀኛል” የሚል ከንቱ እብሪት ዓይኖቹ እንዳያዩ፤ ጆሮዎቹም እንዳይሰሙ ስላገዱት የሰልፉን ድምፅ አላየሁምም አልሰማሁምም ብሏል። ህወሃት ማስተዋል የሚችል ቢሆን ኑሮ ይሄን ድምፅ አድምጦ መልስ ቢሰጥ እንደሚበጀው ያውቅ ነበር። ግን ምን ያደርጋል “እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይበቀል” የምትለዋን እንስሳ መምሰልን የመረጠ ቡድን በመሆኑ ይሄን መሰሉን ድምፅ ሲሰማ “እኔ የኢያሪኮ ግንብ አይደለሁም በጩኸት የምናደው ” እያለ ይሳለቃል።እንዲያውም “የእኔን ፖሊስ ማስቀየር የሚቻለው በመቃብሬ ላይ ነው” እያለ እንደሚፎክርም መታወቅ አለበት።

Friday, April 11, 2014
ነገረ-ኢትዮጵያ፣ ቅጽ 1 ቁጥር 7 ወቅታዊ ጉዳዮችን ይዛ ወጥታለች
- የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻና ፍትሃዊ ምርጫ፣
- የ2007 ምርጫ ከወዲሁ ትኩረት ይሻል!
- የማዕድኑ ሙስና በኢትዮጵያ፣ የመምህራን ፍዳ፣
- ከሙስሊሞች እንቅስቃሴ በስተጀርባ፣
- የሂውማን ራይትስ ዎች የቴሌኮም እና ኢንተርኔት ቁጥጥር በኢትዮጵያ ሪፖርት፣
የኢትዮጵያ መንግስት በረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ላይ ክስ መሰረተ
በተመስገን ደሳለኝ
-ከ253, 336 ከ42 ሳንቲም ዩሮ በላይ ኪሳራ ደርሷል ተብሏል
-የአእምሮ ችግር እንዳሌለበትም ተረጋግጧል
ፍትሕ ሚኒስቴር በረዳት አብራሪ ኃይለመድን አበራ ላይ የካቲት 9 ቀን 2006 ዓ.ም ሌሊት የበረራ ቁጥር ET 702 የሆንን ቦይንግ አውሮፕላንን ከእነ 202 ተሳፋሪዎቹ ወደ ሮም በሚበርበት ወቅት ጠልፎ ሲውዘርላንድ አሳርፏል በማለት በከፍተኛው ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ክስ መመስረቱን የፍትሕ ሚኒስቴር ምንጮቼ አረጋግጠውልኛል፡፡
በኃይለመድን ላይ የቀረበው ክስ ሁለት ሲሆን፤ የመጀመሪያው በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 507/1/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፡-
‹‹…በዋና አብራሪ ፓትዮዝ ባርቤሪ አማካኝነት ከአዲስ አበባ በሱዳን በኩል ወደ ጣሊያን ሀገር ሮም ከተማ መንገደኞችን ለማድረስ በማጓጓዝ ላይ እንዳለ ዋናው አብራሪው የበረራ መቆጣጠሪያውን ክፍል ከውስጥ በመቆለፍ፣ ያለፍቃድ እና በሕገ-ወጥ መንገድ አውሮፕላኑን በቁጥጥር ሥር በማድረግ የአውሮፕላኑ የበረራ ቡድን አባላት በሩን እንዲከፍት ሲጠይቁት አርፋችሁ የማትቀመጡ ከሆነ በአውሮፕላኑ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ብሎ በማስፈራራት፤ እንዲሁም የአውሮፕላኑን የመዳረሻ አቅጣጫ ያለአግባብ በማስቀየር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ፈቃድ ውጭ ወደ ስዊዘርላንድ አየር ክልል ውስጥ በመግባት ተሳፋሪዎች እና የአውሮፕላኑ ሠራተኞች ሕይወት እና ደህንነት አደጋ ላይ እንዲወድቅ አድርጎ በመጨረሻ በጄነቭ ከተማ ውስጥ ያለመዳረሻው እንዲያርፍ በማድረጉ እና ተሳፋሪዎችን ለአደጋ በማጋለጡ በፈፀመው በሕገ-ወጥ መንገድ በጉዞ ላይ ያለን አውሮፕላን መያዝ ወይም ማገት›› የተከሰሰ መሆኑን ያትታል፡፡
Thursday, April 10, 2014
ከአገር መውጣት የማይችሉ ባለሥልጣናት በጭንቀት ውስጥ ናቸው
"አሁን ያለው ኢህአዴግ ላዩ በቀለም ቀቢ የተዋበ ይመስላል"
ኢህአዴግ በሙስና ስም የ”ማጥራት ዘመቻ” ማካሄዱን ተከትሎ የተከሰተው አለመተማመንና እርስ በርስ በጥርጥር የመተያየት ችግር ካድሬውን ማስጨነቁ ተጠቆመ። ኢህአዴግን ለመሰናበት የሚፈልጉ በርካታ ካድሬዎች “ለምን” በሚል የሚቀርብላቸውን ጥያቄ በመፍራት የግድ ፓርቲውን መስለው እንደሚኖሩ ተገለጸ።
የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ቀደም ሲል ኢህአዴግን ተሰናብተው የወጡና በተለያዩ የውጪ ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው በማገልገል ላይ ካሉ ያገኘውን መረጃ በመጥቀስ እንደዘገበው፣ የቀድሞ የትግል ጓደኞቻቸው “በደህና ጊዜ ተገላገልክ” በሚል በፓርቲው ውስጥ ችግር ስለመኖሩ እየነገሯቸው ነው። አብዛኞቹ ኢህአዴግን ተለይተው በሰላም ስለመኖር እንደሚያስቡ ነው የተሰማው።
የቤተሰቦቻቸው የወደፊት እድልና የነሱ በፍርሃትና በጭንቀት መኖር አሳዛኝ እንደሆነ የነገሩት የቀድሞ የኢህአዴግ ሰዎች “አሁን ያለው ኢህአዴግ በቀለም ቀቢ የተዋበ ይመስላል” በማለት አንድ በሚኒስትር ዲኤታ ማዕረግ እያገለገለ ያለ የቀድሞ ጓደኛቸው እንደነገራቸው ገልጸዋል።
ለስራ እንኳን ካገር መውጣት የማይችሉ ባለስልጣኖች እንዳሉ ዘጋቢያችን አመልክቷል። በተቀመጡበት ሃላፊነት ወደ ውጪ የሚያስኬድ አጋጣሚ ሲኖር የሚከለከሉ እንዳሉም ያገኛቸውን መረጃዎች ጠቅሶ ዘግቧል። ለሃላፊዎቹ ደህንነት ሲባል የሚሰሩበትን ተቋምና ስም መናገር እንደማይችሉ በመጥቀስ መረጃውን የሰጡት ክፍሎች “ባለስልጣኖቹ በመካከላቸው እርስ በርስ መተማማን ስለማይችሉ ችግራቸውን መወያየት እንኳን አይችሉም” ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የመብቶች ትግሎች ሁሉ ህወሓትን ከሥልጣን ወደ ማስወገድ አቅጣጫ ያመራሉ!!!
የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎች የክስ ሂደት በበርካታ አሳዛኝ ጉዳዮች የታጀቡ ቢሆኑም የሚሰጡት ትምህርት ግን ከፍተኛ ነው። እነዚህ ወገኖቻችን “ችሎት” በተሰኘው የአገዛዙ የድራማ መድረግ በመገኘት ፍትህን ለመግደል ካባ ለብሰው “ዳኞች” ተብለው ለተኮፈሱ የአገዛዙ ተላላኪ ካድሬዎች እና ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ያደረጓቸው ጠንከር ያሉ ንግግሮች ካድሬ “ዳኞችን” አሳፍረዋል፤ ኢትዮጵያዊያንን ግን አኩርተዋል። እኚህ ወገኖቻችን ከወያኔ ችሎት ፍትህ ይገኛል የሚል ብዥታ ባይኖራቸውም መድረኩን መልዕክት ለማስተላለፊያነት ተጠቅመውበታል። በዚሁ መድረክ በአገዛዙ እጅ ከወደቁበት ጊዜ ጀምሮ እየደረባቸው ስላለው ሰቆቃ ሲናገሩ አድማጮች ሊቆጣጥሩት የማይችሉት ሐዘንና እልህ ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል።
ወያኔ እንዲህ ዓይነቱ ጭካኔ የሚፈጽመው በሙስሊም መሪዎች ላይ ብቻ አይደለም። የህግ እውቅና የተሰጣቸው መብቶቻቸው እንዲከበርላቸው በጠየቁ ወገኖቻችን ሁሉ ተመሳሳይ ሰቆቃ ሲፈጸም ኖሯል፤ አሁን እየተፈጸመ ነው። “ኑሮ ከበደን” ያሉ ወጣቶች ተደብድበዋል። “የእርሻ መሬት አጣን” ያሉ ገበሬዎች ከያዙት ቁራሽ መሬት ተፈናቅለዋል፣ ተግዘዋል፣ ከነልጆቻቸው ለጎዳና ኑሮ ተዳርገዋል። በሀረር እና በአዲስ አበባ ከተሞች እንደታየው “ነግደን እንኑር” ባሉ ነጋዴዎች ላይ ከአቅም በላይ ከሆነ ግብር ጀምሮ በንብረታቸው ላይ እሳት እስከመልቀቅ የደረሰ አረመኔዓዊ ድርጊት ተፈጽሟል።

Tuesday, April 8, 2014
የሃይማኖት ነፃነት ከወዴት አለ?
በቅዱስ ዮሃንስ
በሀገራችን ኢትዮጵያ ጥንታዊው ሃይማኖቶች ማለትም ኦርቶዶክስ ክርስትናና እስልምና ለረጅም ዘመናት ሳይነጣጠሉ ተቆራኝተው በአንድነት የኖሩ መሆናቸውን የታሪክ ማኅደር በሰፊው ይመሰክራል፡፡ በሀገራችን አንድነት፤ በሕዝባችንም ነፃነት እንዲሁም በቤተ እምነቶቻችንን ጽናትና ጥንካሬ ላይ በተለያዩ ጊዜያት ልዩ ልዩ ፈተናዎች ቢገጥሙም፤ በቆራጥ የሃይማኖት አባቶቻችን ጽኑ አመራር፣ ተጋድሎና መስዋዕትነት የተጋረጡባቸውን መከራ እያለፉ ሃይማኖቶቻችንን ጠብቀው፤ የሀገራችንና የሕዝባችንም አንድነትና ነፃነት ሳያስደፍሩ አቆይተውልናል፡፡ ፀረ-ኢትዮጵያዊና ፋሽስቱ ወያኔ ከሽፍትነት ወደ ገዥ ቡድንነት ተሸጋግሮ ሥልጣን ላይ ከወጣበት 23 ዓመታት ጀመሮ የጥፋት እጁን ዘርግቶ የሀገራችንን ሕልውና አደጋ ላይ ለመጣል እየተፍጨረጨረ ከሚገኝባቸው በርካታ አጀንዳዎች መካከል ከፍተኛውን እጅ የያዘው እነዚህን ታላላቅ እምነቶች ማጥፋት እንደሆነ ይታወቃል። ፋሽስቱ ወያኔ የሃይማኖትን ነፃነትን እየተጋፋና በገሃድ ጣልቃ እየገባ ይሄን የሃይማኖት መስመር ነው መከተል ያለባችሁ፤ ሃይማኖቱንም የሚመሩት ልሂቃን እኔ ካልኩት ውጭ አይሆኑም በማለት የሃይማኖት መሪዎችን እየቀባና እየሾመ፤ የሃይማኖት አመለካከትን /Doctrine/ በጉጅሌው ፓርላማ ሳይቀር እየተነተነ የቱ ልክ እንደሆነ የትኛው የተሳሳተ መስመር ውስጥ እንዳለ እየሰበከ ይገኛል።
ምኒልክን ብትወቅሱ ማንነታችሁን ትረሱ
ዶ/ር ኃይለማርያም ላሬቦ
በቅርቡ የአፄ ምኒልክን ስም የማጒደፍ ዘመቻ ያተኰረው ንጉሠ-ነገሥቱ በአሩሲ ውስጥ አኖሌ በተባለ ቦታ ፈጸሙ በተባለ ግፍ ላይ ነው። እንግዴህ “ሞኝና ውሃ እንደወሰዱት ይሄዳል” እንደሚባለው ቅሌታም ብቻ ነው ልበ-ወለድን እንደእውነት፣ ምናብን እንደድርጊት አድርጎ የሚወስደው። ከዚያም አልፎ ደራሲው የታሪክ ባለሙያ መሆን ይቅርና የዐሥራ-ሁለተኛ ክፍል ትምህርት እንኳን ማጠናቀቅ ያልቻለ ግለስብ ነው።
በዚህ በፈጠራ ጽሑፍ ተመሥርቶ ሐውልት የሚያሠራው ግለ-ሰብም ሆነ ባለሥልጣን በግድየሌሽነት የሕዝቡን ገንዘብ ማባከን ብቻ ሳይሆን፣ ሕዝቡን ራሱን ምን ያህል ወደኋላ የቀረ በማሰኘት በዓለምና በታሪክ ፊት እያስገመተ ነው። ርግጠኛ ነኝ የአኖሌ ሕዝብ የሚጠጣ ንጹህ ዉሃ፣ የሚመላለስበት ዘመናዊ መንገድና መጓጓዣ፣ በሽተኛውን የሚያስታምምበት የተደራጀ ሕክምና ቤት፣ ልጆቹን የሚያስተምርበት ማለፍያ ትምህርት-ቤትና፣ ትምህርቱንም ከጨረሰ ወዲያ የሚሰማራበት አስተማማኝ የሥራ ዘርፍ የለውም ይሆናል። የሐውልቱ ገንዘብ በተረት ላይ በተመሠረተ ድርጊት ከሚውል፣ በእነዚህ አገልግሎቶች ላይ ቢጠፋ፣ ሕዝቡን ምንኛ በጠቀመው፤ አሠሪውንስ ምንኛ ባስመሰገነው። ድርጊቱ እውነት ቢሆንስ ሐውልት ለምን አስፈለገ። ኢጣልያኖች ሰንቱን አሩሲ፣ ስንቱን ኦሮሞ ጨርሰው የለ፤ ለምን ለዚሁ መታሰቢያ አልተሠራም። እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፣ በኢትዮጵያ ምድር ለተሠራው ግፍ ሁሉ ሐውልት እንሥራ ከተባለ ደግሞ፣ ከብዛቱ የተነሣ እንኳን ለሰው መኖርያ፣ ለእግሩ ማሳረፍያ የሚሆን መሬት አይገኝም ይሆናል።
አሩሲ ራሱ ቋንቋው ኦሮሞኛ ነው ይባል እንጂ፣ ሕዝቡ ግን ከመቶ ሰባው በትውልዱ የከምባታ፣ የሐዲያና የጒራጌ ነው። እንግዴህ በዚህ መሬት በሌላው የተፈጸመው ሳይቈጠር፣ በኦሮሞች እጅ ብቻ ያለቀውን የነዚህን ሕዝብ ቊጥር የያንዳንዱ ቤት ያውቀዋል። እንግዴህ ለነሱም ሐውልት ያስፈልጋቸዋላ።
የትምህርት ጥራት መውደቅ እስከ በነርሶች የሚማሩ “ዶክተሮች” …..The case of Adigrat University:
በሴቭ አድና
በሀገራችን ስላለው አሳሳቢና ትውልድ አምካኝ የሾቀ የትምህርት ጥራት ባወራን ቁጥር አንዳንድ ሰዎች አይ መጀመርያ ብዛት ይምጣና ከዚያ ቀስ ብሎ ጥራት ይመጣል የሚል መከራከርያ ሲያቀርቡ ስሰማ ይገርመኛል፡፡
አንድ ሰው ከታች ከመሰረቱ በቂ ነገር ሳይዝ ከመጣ እንዴት ነው እላይ የስተካከላል ተብሎ የሚጠበቀው በመጀመርያ ዲግሪ ትምህርቱ እውቀቱ ዜሮ፣ የማወቅ ፍላጎቱ የተገደለበት ሚስኪን፣ በራሱ የማይተማመን፣ የእውቀትንና የትምህርትን ዋጋም የማይገነዘብ፣ እንደማያውቅ እራሱ የማያውቅ ሁኖ የወደፊቱ ህልሙና አላማው ገደል ገብቶበትና “መማር ማለት ያለእውቀት ወረቀት ነው” ወደሚል ድምዳሜ የደረሰ የመከነ የነበረውን passion ሁሉ እንድያጣ የተደረገ ባለዲግሪ፤
ይኸው እውቀትም የሌለው፣ የማወቅ ተነሳሽነቱም የተቀማ ባለዲግሪ እሱም በተራው ሌላ የዲግሪ ተማሪዎችን በሚያስተምርበት ሁኔታ ሌሎች በርካታ አእምሮዎችን ከሱም በባሰ መልኩ በሚያቀጭጭበት ሁኔታ፤ ሀይስኩልም ቢያስተምር እንዲሁ መደደብና እውቀትን መጥላት የሚባሉ በሽታዎችን ለታዳጊዎች በሚያስተላልፍበት ሁኔታ……ሂደቱ እንዲህ እየቀጠለ እንዴት ነው በሂደት ጥራት የሚገኘው?
ይህ ሰው የማስተርስ ፕሮግራም ተብሎ ትምህርት ቢላክም በሶስት፣ አራት፣ አምስት ዐመት የትምህርት ሂደት ቀጭጮ የነበረውን እውቀቱና የማወቅ ሞራሉ በ 1 ዐመት የማስተርስ ፕሮግራም ይቃናል ብሎ እንዴት ይጠበቃል(ተጨማሪ 6 ወሯ ያው የ”ሪሰርች” ጊዜ ናት)? በየዩኒቨርሲቲው በራፍ የተኮለኮሉት የ”Research proposal and Thesis ስራዎችን እናማክራለን” የሚሉት ድርጅቶችስ ይሀንን የማስተርስና የፒኤችዲ ጥናት ወረቀቶች በ3ና 5 ሺህ እየቸበቸቡ አይደለም? እናስ መቸ ነው ይኸ ከታች መክኖ የወጣውን ሰው የሚቃናው?

Monday, April 7, 2014
ኖርዌይ ኢህአዴግ ያሰረባትን ዜጋዋን ጉዳይ እየተከታተለች ነው
ማዕከላዊ እስርቤት ከፍተኛ ስቃይ ይደርስባቸዋል በሚል ተሰግቷል
የኢህአዴግን ካዝና የምትሞላዋ ኖርዌይ በማዕከላዊ እስር ቤት የሚገኙትን ዜጋዋን አስመልክቶ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እየሰራች መሆንዋ ታወቀ። በማዕከላዊ እስር ቤት የታሰሩት ዜጋዋ ድብደባና ቶርቸር እንዳይካሄድባቸው በቅርብ ክትትል እያደረገች መሆንዋን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች ለጎልጉል አስታውቀዋል።

ኢህአዴግን ከልጅነቱ ጀምራ ስትደጉም የኖረቸውና አሁን ደግሞ “በልማታዊ መንግሥትነት” መድባ ድጋፏን የምትዘረጋለት ኖርዌይ ዜጋዋን አስመልክቶ አስፈላጊውን ሁሉ የማድረግ ግዴታ እንዳለባት ይታወቃል። በዚሁ መሰረት የኖርዌይ ትልቁ ጋዜጣ ቀደም ሲል ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ ይፋ ያደረገውን ዜና የሚያረጋግጥ ዜና አሰራጭቷል።
ደቡብ ሱዳን የጸጥታ ሃይሎች አሳልፈው ለኢህአዴግ የሰጧቸው የቀድሞ የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦኬሎ አኳይ የኖርዌይ ዜግነት እንዳለቸው በማረጋገጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን በቅርበት እንደሚከታተለው፣ አዲስ አበባ የሚገኘው የኖርዌይ ኤምባሲም ስራውን እየሰራ እንደሆነ አፍተን ፖስት አመልክቷል።
አፍተን ፖስት “የሰብአዊ መብት ተከራካሪ” ሲል በዜናው መክፈቻ የጠቀሳቸውን አቶ ኦኬሎ አኳይን አስመልክቶ የውጪጉዳይ ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን አማካሪ ስቫይን ሚኬልሰንን ጠቅሶ “አቶ ኦኬሎ የደቡብ ሱዳን የደህንነት ሃይሎች በደቡብ ሱዳንና በዩጋንዳ ድንበር መካከል ይዘዋቸዋል። አንደተያዙም ወደ ጁባ ሳይወሰዱ ተላልፈው ተሰጥተዋል” በማለት የጉዳዩን አካሄድ አመላክቷል።
ማኅበረ ቅዱሳን በፓርቲ ፖለቲካ የማይጠረጠርባቸው ምክንያቶች ( የግል ምልከታ)
በኤፍሬም እሸቴ
ይህ ጽሑፍ የእኔን የግል ምልከታና አስተያየት ብቻ የሚመለከት እንጂ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ስሙ የተጠቀሰውን ማኅበርም ሆነ ከእርሱ ጋር የአገልግሎት ግንኙነት ያላቸውን ተቋማት የማይመለከት መሆኑን አበክሬ በመግለጽ ልጀምር።
አንድ ብሒል አለ። ውሸትን ደጋግመው ቢናገሩት እንደ እውነት የሚቀበለው ሰው መፍጠር ይቻላል። ስለዚህም ሐሰተኞች ሐሰታቸውን ሳያሰልሱ በተናገሩት መጠን፦ አንደኛ ራሳቸውንም በሐሰታቸው እውነትነት ያሳምናሉ፤ ብሎም ሌሎችን ማሳመን ይችላሉ። ደጋግሞ የመናገር ጥቅሙ ይኼው ነው።
አንዳንድ እውነት የያዙ ሰዎች ደግሞ “እውነት እስከያዝን ድረስ ደጋግሞ መናገር ለምን ይገባል?” ብለው ያቀርባሉ። እውነት አላቸው። ፀሐይ ሲወጣ ጨለማ መሸሹ፣ ሻማ ሲለኮስ ብርሃን መፈንጠቁ ላይቀር “ጨለማን ማውገዝ ምን ጥቅም አለው?” ይላሉ። ይህም እውነት ነው። “ጨለማን ደጋግሞ ከማውገዝ አንድ ሻማ ማብራት” እንደተባለው። ነገር ግን ሐሰት ተደጋግማ በመነገሯ ተከታይ መፍጠር እስከቻለች ድረስ እውነትን ደጋግሞ በመናገር የሚመጣ ምን ችግር አለ? ሻማውንም እየለኮሱ እውነቱንም ደጋግሞ መናገሩስ? ስለዚህ በእውነት ተደጋግሞ መነገር፣ በሻማ መለኮስም አምናለኹ። ደጊመ ቃል እንዲሉ የኢትዮጵያ ሊቃውንት።
እንኳን አገር ቤት ያለው አንባቢ ይቅርና እኛ ከአገራችን በብዙ ሺህ ማይሎች ርቀን የምንገኘው ሳንቀር በየዕለቱ የምንኮመኩመው አዲሱ ትኩስ ዜና የማኅበረ ቅዱሳን እና “የተጠመደለት ወጥመድ” ጉዳይ ነው። በማኅበራዊ ድረ ገጾች እና በጡመራ መድረኮች፣ እንዲህ በሕትመት ውጤቶች በሰፊው ሽፋን ያገኘ ጉዳይ ሆኗል። ብዙ ኢትዮጵያውያን (እምነት ሳይለይ) ይህንን ጣልቃ ገብነት በጽኑዕ እየተቃወሙት እያወገዙት ነው። “ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ የሚባል ከሆነ እኔም አክራሪነትን እወደዋለኹ” የሚሉ ሐሳቦች በብዛት ተጽፈው ተመልክቻለኹ።
ስለፍትሕ ሲባል፤ ሥርዓቱ ይፍረስ! (በተመስገን ደሳለኝ)
ባለፉት አራት አስርታት ሀገሪቱ አያሌ ተግዳሮቶችን መጋፈጧ ባይዘነጋም፤ በተለያየ ጊዜ ሚሊዮኖችን ካረገፈው አሰቃቂው ረሃብ በማይተናነስ መልኩ ሕዝቦቿን ዋጋ ያስከፈለ ጉዳይ ቢኖር የፍትሕ አለመከበር ያስከተለው ሁለንተናዊ ምስቅልቅሎሽ ነው ብሎ ለመናገር የሚያስደፍሩ በርካታ ማሳያዎች አሉ፡፡ የየካቲቱን አብዮት ጠልፎ ሥልጣኑን የተቆጣጠረው ወታደራዊው ደርግ፣ የፍርድ ቤት ደጆችን በጓጉንቸር ቆልፎ ሲያበቃ፣ የራሱ አባላት እጃቸውን እያወጡ ድምፅ በመስጠት በአፄው ባለስልጣናትንም ሆነ ግብረ-አበሮቹ በነበሩ መኮንኖች ላይ የሞት ቅጣትን ያህል የመጨረሻ ከባድ ውሳኔ የማሳለፍን አስደንጋጭ ክስተት ጨምሮ፤ ከከተማ እስከ ገጠር ያደራጃቸው የአብዮት ጠባቂዎችና የገበሬ ማሕበራትከየቤቱ አንቀው እያወጡ “ነፃ እርምጃ” እንዲወስዱ፣ ከየእስር ቤቱ እየለቃቀሙ በጅምላ እንዲረሽኑ በአዋጅ የፈቀደበት ጊዜ የፍትሕ ምኩራቡ ፈርሶ በግላጭ የተቀበረበት ዕለት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በርግጥ ይህ የማን-አለብኝነት አረመኔያዊ አገዛዝ የታቃውሞውን ጎራ በማጠናከር ታሪካዊ ውድቀቱ እንዲፋጠን ካደረጉ ምክንያቶች አንዱ እንደነበር ለመረዳት 17 ዓመታትን መውሰዱ አይዘነጋም፡፡
“ፍትሕ አልባው አምባ-ገነናዊ የደርግ ስርዓት አማርሮ በርሃ ያስወጣንና ብሶት የወለደን የለውጥ ሃዋርያት ነን፤ በመቃብሩም ላይ ፍትሕ-ርትዕ የሰፈነባት ዲሞክራሲያዊት አገር እንመሰርታለ” በማለት ከበሮ ይደስቁ የነበሩት የያኔው “ነፃ አውጪዎች”ም፣ ደርግ አፍርሶ የቀበረውን የፍትሕ ምኩራብ አመዱን አራግፈው ቢያነሱትም፤ ባነበሩት አስመሳይ ሥርዓት በኩል በዘውግ ማንነት፣ በሙስናና በሙያ አልባ ዜጎች በክለው ክብር የለሽ ሲያደርጉት በጣት የሚቆጠሩ ወራት እንኳ አልፈጀባቸውም፡፡ ‹‹አዲስ ንጉስ አንጂ ለውጥ መቼ መጣ!›› እንዲል ከያኒው፤ ካስወገዱት የደርግ መንግስት ጋር ልዩነታቸው-ደርጉ ያልቻለበትን የተቃውሞ ድምፆች በአዋጅ እንዲንቀሳቀሱ በአንድ በኩል ፈቅደው፣ በሌላ በኩል መልሶ ለመጨፍለቅ የፍርድ ቤቶችን ባረኮት የመጠቀም ባለ ሁለት ገፅ ብልጠታቸው ብቻ ነው፡፡

Saturday, April 5, 2014
ያልዘሩትን ማጨድ ከቶ አይቻልም!!
የወያኔ መንግስት የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች አጋጭቶ በመካከላቸው ጥርጣሬና መፈራራት አንግሶና የታሪክ ጠባሳዎችን እንደ አዲስ በመጓጐጥ እያደማ ከፋፍሎ ለመግዛት ካለመታከት ያደረጋቸው ሙከራዎች ገና ፍሬ ባያፈሩም ቁጥቋጦዎቹ መብቀል ጀምረዋል። እዚህም እዚያም በካድሬዎች የውስጥ ለውስጥ ተልእኮ የሚለኮሱ እሳቶች መብለጭለጭ ጀምረዋል። ሌላው ቀርቶ በአንድ ብሄረሰብ መሃል ሳይቀር በከባቢ ልዩነቶች ብቻ መናቆሮችና መጋደሎች እያስተዋልን ነው። ሰሞኑን በጉጂና በቦረና ኦሮሞዎች መካከል የወያኔ ሎሌዎች በሚያበረታቱት አተካሮ የብዙ ወገኖቻችን ህይወት ጠፍቷል። ሰዎች ከኑሮአቸው ተፈናቅለዋል። ወያኔ እንደኳስ ጨዋታ ተመልካች ዳር ሆኖ ይመለከታል፣ ያጨብጭባል።
ሰሞኑን ባህርዳር ከተማ ውስጥ በተካሄደ የስፖርት ውድድር ላይ አሳፋሪ ክስተት ነበር። ለሰሚው የሚቀፍ ብልግና የተቀላቀለበት ስድብና ቁርቋሶ አይተናል። ከበስተጀርባ ሆነው ይህንን ለፍቅር ብቻ ሊውል የሚገባ የስፖርት ዝግጅት መርዝ ረጭተውበታል። ከዚህ ላቅ ያሉ የተንኮል ድግሶችም ተደግሰው ህዝብ ውስጥ በወያኔ ከተነዙ የመርዝ ቢልቃቶች ውስጥ ስራ ላይ ሳይውሉ ቀርተዋል።
ይህ በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ዘር የሚዘራው ወያኔ ያልተከፋፈለ ህዝብ አይገዛልኝም በሚል ፍልስፍና እንደሆነ በተደጋጋሚ እያየን ነው። ሶማሌ ክልል ውስጥ በተቋቋሙ ልዩ ፖሊስ በሚል ስያሜ በሚጠሩ የመንግስት ሃይሎች ጥቃት ቁጥሩ እጅግ በርካታ የሆነ የኦሮሞ ማህበረሰብ ከኖረበት መሬት ተጠራርጎ እንዲወጣ ተደርጓል። ብዙዎቹ ተገድለዋል። ብዙ ደም መቃበት ተፈጥሯል። በየክልሉ ምስኪን የአማራ ገበሬዎችን መሬት ንብረት በመንጠቅ አከባቢውን ለቀው እንዲሄዱ አድርገዋል። መሄጃ የለንም ያሉትንም ቀጥቅጠው እንደገደሏቸው ሰሞኑን ከጅባትና ሜጫ አካባቢ ያሉ መረጃዎችን አይተናል።

Wednesday, April 2, 2014
ትንሽ ምላጭ አገር ትላጭ! መጠላለፍ ወደየትኛው ገደል እየመራን ነው?
ፕሮፍ. መስፍን ወልደ ማርያም
መጋቢት 2008
የአዲስ አበባን መኪናዎች በተለይም በጫት የሚሽከረከሩት ታክሲዎችን በማንኛውም መስቀልኛ መንገድ ላይ ለአምስት ደቂቃ ቆሞ የተመለከተ ሰው በቀላሉ እንደሚረዳው ‹እኔ ካላለፍሁ ማንም አያልፍም!› በሚል መመሪያ መኪናዎቹ ተቆላልፈው እንዲቆሙ ማድረግ ነው፤ እንደሚመስለኝ የአባቶቻችንን ዕዳ እየከፈልን ነው፤ ዱሮ በደጉ ዘመን ሁለት ኢትዮጵያውያን መስቀልኛ መንገድ ላይ ሲገናኙ አንተ-እለፍ አንተ-እለፍ እየተባባሉ የሰማዕታቱንና የቅዱሳኑን ስም እየጠሩ ይገባበዙ ነበር! ይህ ባህል በጠንካራ የሥልጣኔ ላጲስ ተደምስሶ ጠፍቶ በምትኩ እኔ ካላለፍሁ ማንም አያልፍም መንገዱን ሁሉ መቆላለፍ አዲስ የመጠላለፍ ባህል እየተተከለ ነው፤ የመጠላለፍ ባህል የሚታየው በባቡር መንገዶች ላይ ብቻ አይደለም፤ በብዙ ነገር መጠላለፍ ባህል እየሆነ ነው! የዚህ ዝንባሌ መጨረሻው አሸናፊ የሌለበት ሙሉ ጥፋት ነው።
በመንገዶች ላይ ጥቂት በጫት የሚነዱ መኪናዎች በመቶ የሚቆጠሩ መኪናዎች እንዳይንቀሳቀሱ ለማድረግ ይችላሉ፤ ሲያደርጉም በየቀኑ እየታየ ነው፤ በማኅበረሰባዊና በፖሊቲካ ግንኙነትም አንድ ሰው የሚዘራው መርዝ የጊዜው ሁኔታ በሚፈቅድለት ፍጥነት የማኅበረሰቡን አባላት ያዳርሳል፤ እንቆቅልሹ እንደሚለው ትንሽ ምላጭ አገር ትላጭ! ማለት መርዝ፣ እሳት፣ ተላላፊ በሽታ በሕዝቡ ላይ ማሰራጨት ከአምስትና ከአሥር ዓመታት በኋላ ውጤቱ ምን እንደሚሆን መገመት አያቅትም።
ድብብቆሽ አይጠቅምም፤ሁለት ነገሮችን በግልጽ ማውጣት አለብን፤አንደኛ በአሜሪካና በአውሮፓ መሽጎ ፍርሃቱንና ሽቁጥቁጥነቱን ለመሸሸግ መርዙን በኢትዮጵያውያን ላይ የሚረጨው ለምንድን ነው? አገዛዙ ይህንን የሚያደርግበት ምክንያት ግልጽ ነው፤ ከፋፍሎ የመግዛት ዘዴ ነው፤ ከአገዛዙ ጋር በሚደረግ ትግል ከታች ሆነው ከሥልጣን ውጭ የሆኑ ዜጎች በሥልጣን ላይ ከተቀመጡት ጋር እየተቆራቆዙና እየተጋጩ ናቸው፤ ይህንን እኔ የላይና-የታች ግጭት (vertical conflict) የምለው ነው፤ ከወያኔ/ኢሕአዴግ ጋር የሚደረገው ትግል ይህ ነው፤ ይህንን ለማክሸፍ ወያኔ/ኢሕአዴግ ትግሉን ከላይና-ታች አውጥቶ ወደጎን-ለጎን ግጭት (horizontal conflict) ሊለውጠው ይፈልጋል፤ ከወያኔ/ኢሕአዴግም ውጭ በጎሠኛነትና በሃይማኖት አክራሪነት የደነዘዙ ሰዎችም ትግሉን ጎን-ለጎን ሊያደርጉት እየሞከሩ ናቸው።

Subscribe to:
Posts (Atom)