በእምነት ቦታ ይገባኛል ነዋሪዎች ባሰሙት ጥያቄ ኢህአዴግ የጥይት መልስ ሰጠ፡፡ ድርጊቱን በምስል በማያያዝ በተለያዩ ማኅበራዊ ገጾች ያሰራጩት ክፍሎች አዛውንትና መነኮሳት ሳይቀሩ መደብደባቸውንና መቁሰላቸውን በምስል አስደግፈው አመልክተዋል፡፡
አኻዙ በትክክለኛው ባይታወቅም አምስት የሚደርሱ ሰዎች ሕይወታቸው እንዳለፈ በማኅበራዊ ገጾች የተበተኑት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ አንዳንድ የድረገጽ ዜናዎችም በአኻዝ ከመለያየት በስተቀር የግድያውንና የድብደባውን መጠን በመግለጽ ዜናቸውን አስፍረዋል፡፡
ድርጊቱን የፈጸመው ኢህአዴግ ስለሞቱትና ስለተደበደቡት መነኮሳትና አዛውንት እንዲሁም ሌሎች ወገኖች ይህንን መረጃ እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ ይፋዊ ማስተባበያ አልሰጠም፡፡ ይልቁንም ከሁለት ሳምንት በፊት ኢህአዴግ የፌዴራል ምክት ሚ/ሩን በፖሊስ ፕሮግራም በማቅረብ የፌስቡክ ዜናዎችን አትመኑ በማለት ማሳሰቢያ ሲሰጥ ነበር፡፡
“ነገረ ኢትዮጵያ” የተሰኘው የፌስቡክ ገጽ ቀበሌ፣ ወሰንና የምክርቤት ስም ጠቅሶ የተፈጠረውን ሁኔታ ከዚህ እንደሚከተለው አስፍሮታል፡፡


ይህ በእንዲህ እንዳለ “በቁጥጥር ሥር ውሏል” የተባለው የሙስሊሙ ተቃውሞ በድንገት መካሄዱ ታውቋል፡፡ በአዲስ አበባ ኑር መስጊድ የተካሄደውን ተቃውሞ አስመልክቶ የተለያዩ የማኅበራዊ ገጾች በተለይም የሙስሊሙን ጉዳይ በመከታተል ይፋ የሚያደርጉ መገናኛዎች እንዳስታወቁት ተቃውሞው የተካሄደው ኢህአዴግ ከሚጠብቀውና ከሚገምተው ውጪ ነበር፡፡ እንደወትሮውም የጥሪ ማስታወቂያና ቅስቀሳ አስቀድሞ አልተካሄደም በማለት ዘግበዋል፡፡ ተቃውሞው ውጤታማ፣ ግቡን የመታና የተጠናከረ ቅንብር እንደነበረው የታዘቡ ይናገራሉ፡፡
ኢህአዴግ በእሁድ የፖሊስ ፕሮግራሙ የሚሰጠው “ልማት ተኮር” የፖሊስ ማስተባበያ “ምርመራ ውጤት በተስፋ” ይጠበቃል፡፡ ከተለያዩ የማህበራዊ ገጾች ያገኘናችው ምስሎች ከዚህ በታች ሰፍረዋል::
ምንጭ፡ ጎልጉል የድህረ ገጽ ጋዜጣ
No comments:
Post a Comment