Sunday, September 20, 2015

አቶ ነአምን ዘለቀ በሚኒሶታው የአርበኞች ግንቦት 7 ገቢ ማሰባሰቢያ ይገኛሉ!

አስመራ የገቡት አቶ ነአምን ዘለቀ በሚኒሶታው የአርበኞች ግንቦት 7 ገቢ ማሰባሰቢያ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ!

ለአርበኞች ግንቦት 7 የሚደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጠሉበት በዚህ ወቅት በሚኒሶታም የፊታችን ኦክቶበር 17, 2015 ዓ.ም እንደሚካሄድ አስተባባሪዎቹ ገለጹ:: በሚኒሶታ የአርበኞች ግንቦት 7 የገቢ አሰባሳቢ አስተባባሪ ኮሚቴ በመግለጫው እንዳስታወቀው አቶ ነአምን ዘለቀ ከአስመራ መልስ በሚኒሶታው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ይገኛሉ:: ኦክቶበር 17 ቅዳሜ ከቀኑ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በሚደረገው በዚህ የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት ላይ ከአቶ ነአምን በተጨማሪም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች እንደሚኖሩ አስተባባሪው አስታውቋል:: አቶ ነአምን ዘለቀ የአስመራ ቆይታቸውን በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ እንደሚያካፍሉ በርካታ ሕዝብ ተስፋ እንዳለው ይጠበቃል:: ስብሰባው የሚደረግበት አድራሻን እና ቦታን ለማወቅ ለዝግጅቱ የተሰራውን ፖስተር ይመልከቱ:: 

No comments:

Post a Comment