Friday, September 4, 2015

ማስታወሻ፤ የእናት ሐገር ጥሪ!!

ቅዱስ ዮሃንስ

የነገ ቅዳሜና እሁድ አገርን የማዳንና የደጀንነት የድጋፍ ጥሪ ዝግጅቶች

የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ በመላው ዓለም ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በነፃነት ትግሉ ዙሪያ እየመከረና ድጋፎችን እያሰባሰበ ቀጥሏል። እስካሁን በተደረጉት ሕዝባዊ ስብሰባዎች ንቅናቄው ከነፃነት ናፋቂ ኢትዮጵያውያን ጋር ስኬታማ ውይይቶችን በማድረግ፤ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የደረሰውን አገርን የማዳን ትግል ከዳር ለማድረስ ከኢትዮጵያውያኑ የገንዘብና የሞራል ድጋፎችን ማሰባሰብ ችሏል። በየ ሕዝባዊ ስብሰባዎቹ ኢትዮጵያውያን በነቂስ በመውጣት የታደሙባቸው እንደነበርና ከንቅናቄ ጋር እስከ ትግሉ ፍፃሜ አብረው ለመጓዝ ቃል በመግባት ደጀንነታቸውን ያረጋገጡባቸው እንደነበር መዘገቡ አይዘነጋም።

ሕዝባዊ ስብሰባዎቹ ነገ ቅዳሜ እና እሁድ ቀጥለው የሚውሉ ሲሆን ፕሮግራሞችን ለማስታወስ ያህል፤

ነገ ቅዳሜ Sept 5፡


  • በካልጋሪ ካናዳ ሰዓት ከ 3 PM ጀምሮ =====>> ቦታ፡ Whitehorn Community Hall
  • በስዊዘርላንድ ዙሪክ ሰዓት ከ 13 ሰዓት ጀምሮ 
  • በኖርዌይ ስታቫንገር ሰዓት ከ 16 ሰዓት ጀምሮ


እሁድ Sept 6፡


  • በኦክላንድ ሳንጆሴ ካሊፎርኒያ ሰዓት ክ 2 PM ጀምሮ ===>> ቦታ፡ Washington Inn
  • በቶሮንቶ ካናዳ ሰዓት ከ 4 PM ጀምሮ ====>> ቦታ፡ Estonian House

ስለዚህ በካልጋሪ ካናዳ፤ በስዊዘርላንድ ዙሪክ፤ በኖርዌይ ስታቫንገር፤ በኦክላንድ ሳንጆሴ ካሊፎርኒያ፤ በቶሮንቶ ካናዳ አገራት እንዲሁም አጎራባች ከተሞች የምትኖሩ ነፃነት ናፋቂ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በሕዝባዊ ስብሰባዎቹ ላይ በመገኘት ለተጀመረው የነፃነት ትግል ደጀንነታችሁንና ድጋፋችሁን በተግባር ታረጋግጡ ዘንድ በክብር ተጠርታችኋል።

ኑ በበረሀ ለአገራችንና ለሕባችንን ነፃነት እየተዋደቁ ላሉት አርበኞቻችን ድጋፍና አጋርነታችንን እናረጋግጥላቸው!!

በእርስዎ ድጋፍ የአገር አድኑ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል!

የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ

No comments:

Post a Comment