Sunday, April 19, 2015

እግዚያብሄር አንድ ሊያደርገን ይሆን ይህን ሁሉ ሰቆቃ የሚያሳየን?


አንድ ወቅት ፕሮፌሰር መስፍን “የኢትዮጵያውያን እንባ ከመብዛቱ ሰማይን እራሱ አደፍርሶታል (አጨቅይቶታል )” ብለው ነበር ::

ዛሬም ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ከአንረ ዘር ከመጡ ጎጠኞች የሚደርስባቸው ስቃይ እና መከራ እንግልት ግድያ አልፎ መሄጃ አጥቶ ለግዜውም መጠግያ ይሆነኛል ለግዜውም ሆነ ለዘለቄታው ብሎ በስደት ከከተመበት አፍሬካ ሀገራት እስከ ቃረብ ሀገራት ዛሬም እንደ ትናቱ በኢትዮጵያውያን እንባ እና ደም እንደተሞላ ነው::South Africa

ከጥቂት ግዚያት ጀምሮ ደግሞ ዘግኛኝ ነው ስለ ኢትዮጵያውያን የሚሰማው የሚታየው የሚነገረው ኬንያ በህገወጥ ገቡብኝ ያለቻቸውን እኢትዬጵያውያን አሰረች ….አንጎላ ….ዝምባቡዬ ፍርዳቸውን ሲጨርሱ ወደ ሀገራቸው እመልሳለው አለች ከዛ የከፋው ደግሞ የኢትዮጵያውያን ኦርጋን በየመን ዘላኖች እየተቀደደ ይሸጣል የደፈራል ብሎ አልጀዚራ በድምጽ እና በምስል አስደግፎ አሳይቶናል እንደወሻም ታስረው ቀጣይ እጣቸውን የሚጠብቁ እትዮጵያውያንን አስይቶናል :: ይሄ አይተንአይናችን ደፍርሶ እስከ መቼ እንደዚ ብለን ሳንቸርስ ሰብሳቢ የለሌ ህዝብ እና ደራሽ የለው ምስኪን በሳውዲ መንገዶች እየታረደ ደሙ ሲፈስ እህቶቻችችን እየደፈሩ ተቃጥለው በየ ቆሻሻው ገንዳው ሲጣሉ እስር ቤቱ ሲታጎሩሩ በታሰሩበት እስር ቤት ሲደፈሩ ድረሱልን ብለው ኡ ኡ ኡ ብለው ድምጻቸውን ሲያሰሙ ድማቸውን የሚሰማ እንባቸውን የሚያብስ ሳይሆን በስልክ እርዳታ የምትፈልጉ ደወሉልን እያሉ የሚያላግጡ ዘረኞች ኢትዮጵያን እየመራን ነው ብለው ሲናገሩ የከረፉኛ ::

ሰብሳቢ እና መሬ የሌው ህዝብ ዛሬም በየመን እንግልት እና መከራ እየደረሰበት ከዛሬ ነገ ምን ይገጥመኝ ይሆን እያለ በሰቆቃ እያሳለፈ ነው እንደ መንግስት ምንም የተደረገለት ነገር የሌው ኢትዮጵያዊ እነ ሱዳን እነ ኤርትራ ኬንያ ሱማልያ ያደረጉትን 0000000.1% እነኩዋን ለማረግ ፍላጎትም ሞራልም የለው ኢትዮጵያን እየመሩ ኢትዮጵያን የሚጠሉ የበዘር ስካር በሽተኞች ናቸው እና በስደት ያለ ኢትዮጵያዊ ግን ወገን ለወገን ደራሽ ነው እና የተቻለውን በሚችለው መንገድ ጥረቱን እያድረገ ነው ከሰልፍ እስከ ኢኮነሚ እርዳታ እና ጥበቃ ከለላ የሚያገኝኡበትን አካባቢ ወይም ሀገር ፍለጋ እላይ እታች እያለ ባለበት ወቅት ሌላ መካራ ሌላ ስቃይ ሌላ የድረሱልን ጥሬ………..

አቀንቃኙ አረ አይነጋም ወይ ኢትዮጵያዬ ያለው ያለፈው እና መጪው መከራ ታይቶት የሆን? ትንቢት ነጋሬ የሆነልን ? አዎ ይፈጠራል በለን በአይናችን ይሄን አይነት ለዛውም በጥቁር አፍሬካውያን ወንድሞቻችን የዚ አይነት ግፍ ይፈጸማል ብሎ የሚያስብ አፍሬካዊ አልነበረም እኔ ጨምሮ ይሄን አይነት ስሜት የፈጠረልኝ ከመሬት ተነስቼ አይደለም ትናት በቀኝ ግዛት ያንን አይነት መከራ ሲቀበል እና ሲገደል የነበረ እህቱና እናቱ ልጁ በዘረኛ ነጮች አይኑ እያየ በሀገሩ ስትደፈር እንደ ፌልም እያየ ምንም ማረግ ባለ መቻሉ ደም ያለቀሰ ጥቁር ደቡብ አፍሬካዊ በቤልጀም ብራስልስ እና በሌሎች አውሮፓ ከተሞች እንደ እንስሳ የብረት ሳጥን ተሰርቶለት ከተማ መሀል እጁ ታስሮ ለህዝብ እንዲጎበኝ ሲደረግ የነበረ ህዝብ ያሲደረግበት ይቃወምለት የነበረን ኢትዮጵያዊ በዘረኞች ሲገደል ለም እያለ ከማንን ቀድሞ ይጮህለት የነበረን ኢትዮጵያዊ ዛሬ በዚ ዘመን ታየቶ በማይታወቅ ጭካኔ ሲገድል ሲያሰቃይ ሳይ አነባወ ….. ለዛሬ ነጻነቱ ያበቁትን መሬወቹን በማስተማረ በመርዳት ከዛም አልፎ ኢትዮጵዊ ፓስፓርት በመስጠት ለዛሬ ማንነታቸው ትልቃ አሻራ ያደረገውን ኩሩ እና ጀግኛ ኢትዮጵያዊ ዛሬ ቀን ጥሎት በሀገሩ የመኖር ህልውናው ሲጠፋ ቀን እስኪያልፍ ብሎ ትናት ባለው ነገር የረዳቸው ዛሬ እንደሀገር ከፍ ማለታቸው ሚስጢር ላይ ትልቅ አሻራ ያለውን ኢትዮጵያዊ ሰማ ሰባሬ የሚያካክል ድንጋይ ሲጭኑበት ሳይ ጎማ ውስጥ አስረው ከነ ሂወቱ ሲያቃጥሉት ስመለከት እንደ ስጋቤት ስጋ በቆንጨራ እየበለቱ ሲሰነጥቁት የሚመለከት የሰው ልጅ ምን እንደሚል እኔጃ እንደ ኢትዮጵያዊ ግን እኔ ያንን መከራ እና ግፍ ሲፈጸም ሳይ ቃላትም አቃተኝ አስመረረኝም ::


የዚ ሁላ መከራ እና ግፍ ግን ግልጽ ነው ትናት ሀገር ሳይኖራቸው ሀገር እንዲኖራቸው ያረግናቸው ሀገሮች ዛሬ ከኛ የተሻለ መሬ አላቸው ትናት ነጻ እንዲወጡ ያደረግናቸው የተገላቢጦች እኛ ዛሬ ነጻነት የለንም ሀገር የለንም መሬ የሚሰበስበን የለም እነሱ በባእዳን ቀኝ ግዛት ሲያዙ እኛ የተገላቢጦሽ ከመሬትዋ በበቀሉ ዘረኞች ቀኝ ግዛት ተይዘን እንገደላለን እንታሰራለን እንሰደዳለን ከዛ የከፍው ደግሞ የዘር ማጥፋት ይካሄድብናል ለዚ ምሳሌ ወልቃይት ጠገዴ ህዝብ እና የኡጋዴን ህዝብ ነው:: ይሄን ያዬ ዛሬ ቀን ያነሳቸው ችግር አጋጥሞን የተጠጋናቸው ሀገሮች ሰብሳቢ እንደሌን በማወቃቸው ጭካንያቸው በአራቱም አለም ሀገራት እየደረሰብን ነው ::

ኢትዮጵያዊ በየትኛውም ዘመን እንደ አሁኑ ግዜ የተዋረደበት እና እንደ እንስሳ የታረደበት እንባው የፈሰሰበት የተሰቃየበት የጮሕበት ከሀገር አልፎ እስከ ተሰደደበት ዘመን አለ? ካለ ታሬክ አዋቂወች ብታስተምሩኝ ብትነግሩኝ ዝግጁ ነኝ ::

ከስቃያችን የከፋው ስቃይ ደግሞ ኢትዮጵያን በመምራት ላይ ካሉት መካከል የውጭ ጉዳይ ሚንስተር ነኝ የሚለው ግለሰብ ነው በኢትዮጵያን ስቃይ ለሱ ማፌዣ መሆኑ ነው እኔ የቴሌፎን ሚንስተር ብየዋለው ኢትዮጵያውያን ባልተደላደለ እና በጭንቀት እና በመከራ ውስጥ ሆነው ካሁን አሁን ምን ያጋጥመናል ምን ይደርስብን ይሆን ብለው ህጻናት ልጆቻቸውን ይዘው አምላክን እያለቀሱ በሚማጸኑበት ወቅት የተሰማላቸው አጋጣሚውን ያገኙ የድረሱልን ጩኽታቸውን በሚያሰሙበት ወቅት የቴሌፎኑ ሚንስተር “ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡ ስልክ ቁጥር ደውሉሉን ” እያለ የሚያላግጠው ነገር ይገርመኛል እነዚ ወገኖች እኮ ለሆሊዴይ ኤርፓርት ሲደርሱ ፓስፓርት ጠፍቶባች አይደለም እኮ በመት እና በመኖር ውስጥ ሆነው የተባሉት ምቾት ነገሮች በሌለብት ውስጥ ይሄን ሲል ምን ያህል ለኢትዮጵያዊነት ላይ ያላቸውን ጥላቻ እና ዘረኝነት ነው የሚያሳየው ሱማሌ እንክዋን ከኛ ትሻል?? ለነገሩ እኛ መንግስት የለንም!! ባንዳ ወንበዴ እንጂ :: እንደ መግስት ለህዝባቸው መግለጫ አልፈው ጥበቃ እየሰጡ እንዲሁም የደቡብ አፍሬካ መንግስት ማብርያራ በአስቸኩዋይ ይሰጠን ብለው የጠየቁ ሀገሮች ስናይ የኛወቹ ግን ምንም የስልኩን ሚንስተር እንኩዋን ቦከሀራም ቀደመ ::

በመጨረሻም ይሄ ሁሉ ስቃይ እና መከራ እንዴት ነው እትዮጵያዊ ማቆም የሚችለው በስቃይ ላሉ ወገኖች መከታ የሚኮነው ? ለዚ ምላሹ አጭር እና ቀላል ነው እንደ ኢትዮጵያዊ እና እንድ ህዝብ በ24 አመት ውስጥ ዘረኞች እየከፋፈሉ የገዙበትን እየገዙበት ያለውን ስራት በጋራ እና በአንድነት መታገል በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ ያለውን ዘረኛ ስራት እኔ የእንትና ´ነኝ እኔ የሱ ነኝ ማለታችንን አቁመን በአንድነት መታገል መከፋፈላችን ካገር አልፎ ስደት አለም በተናጠል እንድንገደል እንድንሰቃይ እያደረገን ነው የጠነከረ ነገር አንድ የሆነ የተባበረ ሀይል ስለሌለን ስለዚህም ቅድሚያ በአንድነት በሀገራችን የሚድርስብንን ስቃይ እና መካራ ታግለን ማጥፋት ከዛም ኢትዮጵያ እንደ ኢትዮጵያዊ በሀገራቸው የሚከበሩባትን ሀገር ማቆም ስለ ህዝቡ ስቃይ የሚናደድ ስለ ህዝቡ መከራ የሚቆጣ መከታ የሚሆን መሬ መፍጠር ይሄን ስናደርግ ዛሬ የናቁን ያከብሩናል ይሄን ያደረሱብን ያደረሱብንን ጉዳት እና መከራ ይክሱናል !! አሁን በምዳክርበት መንገድ ከሄድን ግን የዘር አገዛዙም ይቀጥላል በስደትም መናቁ እና ስቃዬ ይቀጥላል ታድያ ኢይትዮጵያዊ የቱን ይመርጣል !!

እግዚያቢሄር ስቃይ እና መከራችንን አይቶ ይሀን ስቃይ በአንድነት ሆነን የምንታገልበትን መንገድ እና ግዜ ሰአት ፈጥሮልናል እና ዛሬውኑ በአንድነት ሆነን እንታገል በአንድነት ሆነን በሀገራችን ላይ ያለውን ዘረኛ ስራት ለማሰወገድ እና በሀገራችን ኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ስርአቱን መንገድ ለመዘርጋት የግፍን እና የሰቆቃን ቀንበር ለማጥፋት የሚታገሉትን እንርዳ እናበረታታ ምንም ካላረግንም መንገዳቸው ላይ ቆመን ቃሬጣ አንሁንባቸው !!

በዚ ወቅት በሳውድ አረቢያ በየመን አሁን ደግሞ በሳውዝ አፍሬካ በመከራ እና በችግር ውስጥ ላላቹህ ኢትዮጵያውያን ወገኖች እግዚያቢሄር ከመከራቹህ እና ከስቃያቹህ ይታደጋቹ ዘንድ ጸሎቴ ነው !! ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለለም ተከብራ ትኑር !!

No comments:

Post a Comment