በቅዱስ ዮሃንስ
አገራችን ኢትዮጵያ በጎጠኛውና በከፋፋዩ የፋሽስቱ ወያኔ አገዛዝ መዳፍ ውስጥ ከወደቀችበት ጊዜ ጀምሮ የደረሰባትንና እየደረሰባት ያለውን ውርደትና መከራ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመገርሰስ ወደ ክብር ለመለወጥ፤ ብሎም የናቋትን እና ያዋረዷትን ጉጅሌዎች በፍትህ ሚዛን ላይ እንዲቀመጡና ፍርዳቸውን እንዲያገኙ ማድረግን ቀዳሚ አላማው አድርጎ ወደ ዱር የከተተውና፤ በአገራችን የነገሰውን ፍጹም አምባገነናዊ አገዛዝ በሚገባው ቋንቋ ሁሉ ለማነጋገር እጅግ በዘመነ ሁኔታ እየተደራጀ የሚገኘው የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል 5 ዙር ታጋዮችን ሰኞ ጥቅምት 17 ቀን 2007 አ.ም ማስመረቁን ከህዝባዊ ሃይሉ የተላከልን መረጃ ያመለክታል።ተመራቂ ታጋዮቹ ላለፉት 3 ወራት በተከታታይ በወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ እና የመረጃ እና ደህንነት ትምህርቶች በበቂ ሁኔታ መሰልጠናቸው የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ያለውን የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበና ወቅቱ የሚፈልገውን ቴክኖሎጅ በመጠቀም መረጃን መቀበልና ማስተላለፍን የጨመረም እንደነበር ተያይዞ ተጠቅሷል።

ኮማንደሩ በስተመጨረሻም ‘’ይህ የህዝባዊ ሃይላችን ስልጠና በግንቦት ሰባት ስም ከሚደረጉት ስልጠናዎች የመጨረሻው ይሆናል በማለት የገለጹ ሲሆን ለተመራቂ ታጋዮች ባስተላለፉት መልዕክት ‘’ስልጠና ላንድ ታጋይ የትግሉ የመጀመሪያ ምዕራፍ ሲሆን በስልጠና ላይ ያገኛችሁትን ትምህርት በተግባር ለቆምንለት ዓላማ እና ተልዕኮ በቁርጠኝነት እንደምታውሉት ሙሉ እምነቴን እገልጻለሁ ‘’ ካሉ በኋላ የአገርና የትውልድ ጠላት የሆነውን የፋሽስቱ ወያኔ አገዛዝን ከኢትዮጵያ ምድር ጠራርገን ለማስወገድ በምናደርገው እልህ አስጨረሽ ትግል አብረን እንቁም፤ ሕዝባዊ ሃይላችንንም ተቀላቀሉ ሲሉ ለኢትዮጵያ ህዝብ ወገናዊ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በሀገር ውስጥ እንደማእበል እየገነፈለ ያለውን የአታግሉን የሕዝብ ጥያቄ በተደራጀና በተቀነባበረ መንገድ በተገቢው መልኩ ለማስተናገድ እንዲችል እንደ ድርጅት ከመቼው ጊዜ በላይ ራሱን እያደራጀና እያጠነከረ እንደሚገኝና ምቹ አታጋይ ተቋም ሆኖ ለመውጣት ሌት ተቀን እየደከመ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ ቀደም በ 4 ተከታታይ ዙሮች በርካታ ታጋዮችን ማስመረቁን መዘገባችን አይዘነጋም።
No comments:
Post a Comment