Saturday, August 9, 2014

የወያኔን ሴራ በማጋለጥ የድርሻችንን እንውጣ!!!

በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ፋሽስቱ የወያኔ ቡድን የሚያደርገው ነገር የአምባገነኖችን ልዩ በሀሪ የሆነውን ስራ በመስራት ላይ ተጠምዶ ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየሰራ ያለውን ሴራ እንደሚከተለው በእኔ አስተያየት መግለጽ እፈረልጋለሁ፡፡

ሴራ 1
የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን፤ አባላትን እና ደጋፊዎችን በማዋከብ እና በማሰር ቀጣዩን “ምርጫ” ልክ እንደ አለፉት “ምርጫዎች” ብቻውን አሸንፎ እንደገና ሌላ የመደንቆሪያ ና ህዝብን የማሰቃያ 5 ዓመታትን በእጁ ለመጨበጥ የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው፡፡ እስኪ ተመልከቱት እነዚህ የተቃዋሚ መሪዎች ላይ እንደዚህ አይነት ውንብድና የተሰራው (እንደዚህ አይን ያወጣ ባይሆንም)” በምርጫ” 2002 ጊዜ በዳኛ ብርቱካን ሚደቅሳ ላይ የተፈፀመውን አይነት ውንብድና ማለት ነው፡፡ ምርጫው ካለፈ በሁዋላ የተቃዋሚ መሪዎችን በመፍታት ከሀገር እንዲኮበልሉ በማድረግ ኢትዮጵያን ( በወያኔዎች አጠራር ሀገሪቱን) የግል ንብረታቸው ለማድረግ የተጠነሰሰ ሴራ ነው፡፡

ሴራ 2
ጋዜጠኞችን በማሰር፤ በማዋከብ፤ በመደብደብ፤ አልበቃቸው ብሎ ግማሽ ደርዘን የህትመት ውጤቶችን በመዝጋት የቻሉት ከሀገር ተማረው እንዲወጡ ያልቻሉት ደግሞ ወደ ቃሊቲ፤ ቂሊንጦ፤ ዝዋይ….እንዲሰደዱ በማድረግ ለህብረተሰቡ ትክክለኛ እና ሚዛናዊ የሆነ መረጃ እንዳይደርሰው በማድረግ የዜና ምንጮችን በማድረቅ ላይ ተጠምደው ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ጋዜጠኞችን በአሸባሪነት መፈረጅ ማለት ምን ማለት ነው? ማንኛውም ግለሰብ ወይም የፖለቲካ ፓርቲ በአሸባሪነት ለመፈረጅ አለማቀፋዊ መመዘኛወችን ወደጎን በመተው ስለተቃወሙ ብቻ ወይንም የወያኔን ፖለቲካዊ አመለካከት ስላልተቀበሉ ብቻ በገዛ ወገኖቻቸው ለግርፋት እና ለስቃይ በቅተዋል፡፡ ስለዚህ ለእነዚህ ወገኖቻችን ከጎናቸው መሰለፋችንን እንዲያውቁት እና ተስፋ እንዳይቆርጡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለወያኔዎች ማሳየት ያለብን ፍርድ ቤት በሚቀርቡበት ጊዜ በመገኜት እና ሞራል በመስጠት ልናበረታታቸው ይገባል፡፡ በየማህበራዊ ድሀረረ ገጾች ላይ ወያኔዎች እየፈጸሙት ያለውን ግፍ ለህብረተሰቡ ማጋለጥ ይሄ ሀገር ወዳድ የወያኔ አባላትንም ይመለከታል(እንደ ንስሃ ይቆጠርቸዋልም) መረጃ በመስጠት መተባበር፡፡


ሴራ 3
የእምነት ተቁዋማትን በማሽመድመድ ለእምነታቸው ቀናያን የሆኑትን በተለይም የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን በአክራሪነት ሽፋን እየወነጀሉ የማዳከም ስራን በመስራት ተጠምድው ይገኛሉ፡፡ ሙስሊሙን ደግሞ የሽብር ወንጀል ተባባሪ ወይም የሽብር ወንጀል ለመፈፀም ከፀረ-ሰላም ሃይሎች ጋር ሲሰራ ያዝነው በማለት የመፍተሄ አፈላላጊ ኮሚቴውን ጨምሮ እስር ቤት በመወርወር ይህም አልበቃቸው ብሎ ፀሎት ከሚአደርጉበት ቦታ እየገቡ ህዝበ ሙስሊሙን ህፃን፤ አዋቂ፤ ሽማግሌ፤ ሴት፤ እርጉዝ…ሳይመርጡ በመረበሽ ህዝቡ በእምነት ቦታወች ሁሉ እየተማረረ እንዲቀር በማድረግ አንዱ ከሌላው ጋር ሳይገናኝ ታፍኖ እንዲቀር ነው የተፈለገው፡፡

ሴራ 4
ወጣቱ ትውልድ ስለ አገሩ እንዳያውቅ ስለ ነፃነት እንዳይወያይ የነገ አገር ተረካቢ መሆኑን እንዲዘነጋ ስለተፈለገ ይህንን እኩይ ምግባራቸውን በሁለት ነገር እያስፈፀሙት ይገኛሉ፡፡ አንደኛው(ይሄ ገንዘብ ያለውን እና በልቶ የሚአድረውን ነው) በተለያዩ ሱሶች እንዲጠመዱ በማድረግ ይሄም በጫት፤ ሺሻ፤ ሀሺሽ፤ መጠጥ፤ ዝሙት፤ በበሽታ በተለይም የከፍተኛ ተቁዋማት(ዩኒቨርስቲዎች) ባሉበት አካባቢ እነዚ ነገሮች እንዲበዙ በማድለግ ሲሆን ገንዘብ የሌለውን ደግሞ ከተሜውን በአነስተኛ እና ጥቃቅን ገበሬውን በሴፍትኔት በማደራጅት 1፡5 በሚል መርህ ባል ሚስቱን ልጆቱን ሚስትም፤ ልጆችም፤ ሰራተኛም እንደዛው በመጠርነፍ አንዱ ከአንዱ ጋር ሳይግባባ እንዲኖር፡፡ ሁለተኛው ከእነዚህ ከላይ ከጠቀስኩዋቸው ካመለጠ በF.M ሬድዮኖች ስለ ፍቅር፤ ስለ ኩዋስ፤ ስለ ውጭ አገር ታዋቂ ሰዎች ታሪክ እየተሰበከ ኢትዮጵያዊነት ስሜት ሳይኖረው እንዲያድግ ተፈርዶበታል፡፡ ታዲያ ትውልድን ከመግደል በላይ ምን ሴራ አለ?

ሴራ 5
የመከላከያ ሰራዊተወን ሃቅም በማጎልበት በገንዘብም፤ በመሳሪያም፤ በቴክኒዮሎጅ በማበልፀግ እና በመገናኛ ብዙሀንም ውስጥ በተለያዩ ዜናዎች ህዝቡ እንዲፈራ ለማድረግ መከላከያ በጥሩ ሁኔታ የተደራጅ መሆኑን ማሳየት፡፡ እዚህ ላይ ከአፄ ኃይለሥላሴም ሆነ ከደርግ መማር ያቃተው አይነ ስዉሩ የወያኔ ቡድን ተመሳሳይ ስራ በመስራት ተጠምዱዋል፡፡ እዚጋ አንድ ነገር በዝርዝር ማለት እወዳለሁ የአፄ ኃይለሥላሴ መንግስት የትም ጦርነት ተደርጎ አይደለም የወደቀው የስርአቱ አገልጋዮች ያውም የበታች ሹማምንቶች ናቸው የጣሉት፡፡ የደርግም ቢሆን የወያኔዎች ጀግንነት ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ለደርግ ያለው ጥላቻ ነው፡፡ ይህን ጥላቻ ያ ብዙ የተነገረለትን ሰራዊት በአጭር ጊዜ እንዲወድቅ አደረገው፡፡ግብጽ የመከላከያ ሰራዊቱአ ነው ለዚህ ሁሉ ብጥብጥ ያበቃት፡፡ ሊቢያ ያን የመሰለ የመከላከያ ሰራዊቱአ የጋዳፊን ስልጣን ያቆየው ለወራቶች ብቻ ነበር፡፡ ከዛም ህዝብ ነው ያሸነፈው፡፡ የመሳሪያ ጥራት በለው የሰራዊት ብዛት ለመንግስታት የቀናት ታማኝነት ብቻ ነው ያላቸው ምክነያቱም ሰራዊቱ ለህዝቡ ከመሪዎቹ በተሻለ ቅርብ ስለሆነ፡፡ ሰራዊቱ የወጣው ከተበደለው ህብረተሰብ ስለሆነ ነው፡፡

በመጨረሻ፡ አለም በአሁነተ ሰዓት ለአምባገነኖች ፊቱዋን እያዞረች ትገኛለች፤ ማንኛውም የተበደለ ህዝብ ነፃነቱን ማንም ሊሰጠው አይችልም ስለዚህ እነዚህን እድሎች በመጠቀም ወያኔን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ በቃህ የምንልበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ ምናልበትም ይህን እድል ሳንጠቀም እነሱ(ወያኔዎች) ባዘጋጁልን የዘር ድንኩዋን ተቀምጠን ለውጥ ይመጣል ብሎ መጠበዉ የዋህነት ነው፤ ስለዚህ በአሁኑ ጊዜ አለም አንድ በሆነችበት ዘመን ውስጥ ሆነን ትግል በጫካ ብቻ ነው ያለው የሚለውን አመለካከት በመተው ለነፃነታችን እንነሳ እላለሁ፡፡ ወያኔ ያዘጋጀልንን ሴራ የመበጣጠስም ሀላፊነት አለብን፡፡

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!

No comments:

Post a Comment