Sunday, March 8, 2015

የነዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ

“ሸላሚም እኛ፣ ከሳሽም እኛ!“

አብርሃም ሰለሞን የ25 ዓመት ወጣት ነው፡፡ ያሳደገው ኢሕአዴግ ራሱ(ወይም ዘመነ መንግስቱ) ነው፡፡ በቤተልሄም የመጀመሪያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ IT መምህር ነበር፡፡ በትምህርት ቤቱ መልካምዝና ነበረው፡፡ በ2006 በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገ ውድድር ላይ ይዞ በቀረበው የመምህራን ዳታ ቤዝ እና የመማሪያ ማኑዋል ዝግጅትንአሸናፊ መሆን ከቻሉ ሦስት ወጣቶች አንዱ ለመሆን በቅቷል፡፡ ጥቅምት 16/2007 - በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሸላሚነት ሲካሄድ በነበረውየሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች የሽልማት ሥነ ስርዓት ላይ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን IT ለማስተማር የሚረዳ የዴስክቶፕሶፍትዌር እና የሞባይል አፕልኬሽን በማዘጋጀት የሜዳልያ ተሸላሚ ተብሎ ተመዝግቧል፡፡ ይሁን እንጂ የዘንድሮውን የስራውን ውጤት በአካልተገኝቶ ሰርተፍኬቱንም፣ ሜዳልያውንም መቀበል አልቻለም፤ በእሱ ፈንታ እናቱ በውክልና ተቀብለውታል፡፡ ምክንያቱም እሱ በሽብር ወንጀልተጠርጥሮ ቂሊንጦ ማቆያ ቤት ይገኛል፡፡

አብርሃምን ስለ አገሪቱ የወደፊት ተስፋ ሰጪ ስራ ሰርተሃል ብሎ በቀኝእጁ የጨበጠው መንግስት፣ በግራ እጁ ደግሞ ለአገሪቱ የወደፊት ተስፋ አደገኛ አሸባሪ ነህ ይለዋል፡፡

“የማይተዋወቁ ግብረ - አበሮች”

በሽብር የሚከሰሱ ሰዎች ከማያውቋቸው ሰዎች ጋር በአንድ መዝገብ (እንደግብረ አበር) የሚታሰሩበት አሰራር የተለመደ ሆኗል፡፡ ለዚህ አንዱ ማሳያ የነዘላለም ወርቅአገኘሁ መዝገብ በመባል የሚታወቀው (መዝገብቁጥር 166/07) አንዱ ነው፡፡ በዚህ መዝገብ አራት የተለያዩ ፓርቲ አባላት እና ሌሎች 6 ተጠርጣሪዎች ተከስሰዋል፡፡ የመጀመሪያዎቹ5 ተከሳሾች (ዘላለም ወርቅአገኘሁ፣ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ አብርሃ ደስታ እና የሺዋስ አሰፋ) በፀረ- ሽብርተኝነት አዋጁአንቀፅ 4 ሲከሰሱ፣ ቀሪዎቹ አምስቱ (ዮናታን ወልዴ፣ አብርሃም ሰለሞን፣ሰለሞን ግርማ፣ ባህሩ ዳኑ፣ እና ተስፋዬ ተፈራ) በአንቀፅ 7/1 እና 9ኛ ተከሳሽ (ባህሩ ዳጉ) በሌላ ክስ በወንጀለኛ መቅጫው288/1 መሰረት ከመከላከያ ሰራዊቱ በመኮብለል ተከስሰዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ክሳቸው በአንድ መዝገብ ታጭቀው ቢመጡም ባብዛኛው እርስበርስ አይተዋወቁም፤ በጋራ የሰሩት ስራም የለም፡፡

በፌስቡክ እንቅስቃሴው በስፋት የሚታወቀው እና የአረና ትግራይ ፓርቲአመራር አባል የነበረው አብርሃ ደስታ ለምሳሌ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል ከሆነው ሀብታሙ አያሌው በቀር የሌሎቹን ስም እንኳንአብረው ከመከሰሳቸው በፊት አለመስማቱን ይናገራል፡፡ ተሸላሚው አብረሃም ሰለሞንም ከተከሳሾች የሚያውቀው ዘላለምን ብቻ ነው፡፡‹‹እሱንም›› ይላል አብርሃም ‹‹በ2006 አንድም ቀን አግኝቼው አላውቅም››፡፡ ከተከሳሾች መካከል ብዙ ሰው ያውቃል የተባለለት1ኛው ተከሳሽ ዘላለም እንኳን የሚያውቀው ሦስቱን ብቻ ነው - ዮናታን፣ አብርሃምን እና ባሕሩን ብቻ፡፡
“በስልክ የማውራት አሸባሪነት”

በሽብር የተከሰሱ ሰዎች ላይ በተደጋጋሚ እና በተለይ ከሚቀርቡ የማስረጃዓይነቶች አንዱ የስልክ ግንኙነት ነው፡፡ ከላይ በጠቀስነው መዝገብ ውስጥ ብቻ ክስ ሆነው የቀረቡትን የስልክ ግንኙነቶች እንመልከት፡-

* 1ኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ፣ ‹‹በ 2000 ተድላ ደስታ ከተባለየሽብር ድርጅቱ አባልና አመራር ጋር በስልክ እና በፌስቡክ›› በማውራት፤
* 2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው ‹‹ዘመኑ ካሴ ከተባለ የግንቦት ሰባትታጣቂ›› ጋር በጥር 14/2005 በስልክ በማውራት፤
* 3ኛ ተከሳሽ ዳንኤል ሺበሺ ‹‹የግንቦት ሰባት አመራር ከሆነው ፋሲልየኔ አለም ›› ጋር በየካቲት 29/2003 በስልክ በማውራት፤
* 4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታ ‹‹የደ.ም.ሕ.ት. አመራር ከሆነው ጎይቶምበርሄ ›› ጋር ጥር 3/2006 በስልክ በማውራት፤
* 5ኛ ተከሳሽ የሺዋስ አሰፋ ‹‹የግንቦት ሰባት አመራር ከሆነው ፋሲልየኔአለም›› ጋር ጥቅምት 14/2006 በስልክ በማውራት፤
* 10ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ተፈሪ፣ የግንቦት ሰባት ክንፍ ከሆነው የአ.ዴ.ኃ.ንአባል ጋር ሕዳር 2003 በስልክ በማውራት፤


እነዚህ የስልክ ግንኙነቶች ያለሌላ ተጨማሪ ማስረጃ በብቸኝነት የክስመመስረቻ መሆናቸው ደግሞ ክሱን ተአማኒነት ያሳጡታል፡፡ ዜጎች የስልክ ግኑኝነቶችን በሙሉ እንዲፈሩም ያደርጋቸዋል፡፡ በሽብርተኝነትበተጠረጠሩ ድርጅቶች ውስጥ በዐቃቤ ሕጉ ቃል ብቻ አባል ናቸው የተባሉ ሰዎች ስለደወሉለት ብቻ የተደወለለት ሰው ‹‹አሸባሪ›› ተብሎይከሰሳል፡፡ ፈቅዶ ባልተደወለለት ስልክ ወንጀለኛ ነህ የሚባልበት አሰራር ከኢትዮጵያ ውጪ ያለ አይመስልም፡፡ አንዳንዶቹ የስልክጥሪዎች የተደረጉት ‹‹ሽብርተኛ ናቸው›› በተባሉ ድርጅቶች ውስጥ ባሉ እና በሚታወቁ ግለሰቦች ሳይሆን የአቃቤ ህግ ቃል ብቻ ያልሆነውንነው ብሎ ስላቀረበ ነው፡፡ በዚህ መንገድ የተፈረደባቸው ብዙ ናቸው፡፡ ሳይፈረድባቸው ራሳቸውን ለመከላከል ማረሚያ ቤት እንዲቆዩየተደረጉትም የዚያኑ ያክል ናቸው፡፡ በ2000 የፀረ ሽብርተኝነቱ አዋጅ አልወጣም ነበር፤ ሽብርተኛ የተባሉ ድርጅቶችም አልነበሩም፡፡ክሱ ላይ ግን በዚያ ወቅት የተደረገ የስልክ ግንኙነት ተጠቅሷል፡፡

በሁሉም የሽብር ክሶች ውስጥ copy/paste የተደረገች ውንጀላ አለች፤‹‹ራሱን [እከሌ ]ብሎ ከሚጠራው አሸባሪ ቡድን ግንኙነት በመፍጠርና ተልእኮ በመቀበል ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድበማሰብ . . . ‹‹የምትል ነች፡፡ ይህች ቃል ዐቃቤ ሕግ በተጠርጣሪዎች ላይ ምንም ዓይነት ድርጊት ሳይጠቅስ የሚያስቀጣበት ውንጀላ ነች፡፡ በዚሁ በነዘላለም መዝገብም ላይ በተደጋጋሚ ተጠቅሳለች፡፡ በስልክአንድ ሰው ጋር ያወራሉ ከዚያ ተልእኮ ይቀበላሉ፡፡ ሽብር ማለት በቃ ይኽው ነው፡፡

“ሥልጠናዎች ሁሉ ሽብር ናቸው”

በነዘላለም መዝገብ ከተከሰሱት ውስጥ 6ኛ እና 9ኛ ተከሳሽ(ዮናታንእና ባሕሩ) ክስ ላይ የተጠቀሰ ነገር አለ፡፡ይኸውም ‹‹ በመንግስት ላይ ያሉ ችግሮችን ለሕዝብ በተለያዩ የኢንተርኔትና የማህበራዊድህረ - ገፆች ላይ በመፃፍ ለግል ሚዲያዎች ግብአት የመስጠት ሥራ የሚሰሩ ቡድኖች አሉ፡፡ ለዚሁ ተግባር ተብሎ የወሰዱትን የኢንተርኔትአጠቃቀም፣ ኮሙኒኬሽን ስኪል እና ሊደርሺፕ በመሰልጠን ተጠቅመዋል እናንተስ እንዲህ አይነት ስልጠና አትፈልጉም ወይ?›› በሚል አንደኛተከሳሽ ለሁለቱ ተከሳሾች ቀርበዋል የተባሉት ጥያቄዎች ወንጀል ተብለው ተፅፈዋል፡፡ ‹‹ሠልጥነዋል›› ተብለው በምሳሌው የተጠቀሱት‹‹ቡድኖች›› ዞን ዘጠኞች መሆናቸው በሌላ ማስረጃ ተጠቅሷል፡፡ሥልጠናውን ዐቃቤ ሕግ 9ኛ ተከሳሽ ላይ ሲጠቅሰው መጀመሪያ ‹‹ተመሳሳይሥልጠና ለተመሳሳይ አላማ ›› ይልና ዝቅ ብሎ ‹‹የሽብር ድርጅቱን ተልዕኮ ለመፈፀም እንዲረዳቸው ባዘጋጁት ስልጠና ›› ይላል፡፡የመንግስታችን ችግሮች መፃፍ ፣ ወይም ለመፃፍ መሰልጠን በምን መሥፈርት አሸባሪነት ተባለ?

“አብርሃም ሰለሞንን ማን መለመለው?”

የክስ መዝገቡ መጀመሪያ ላይ ‹‹[አብርሃም ሰለሞን] በ1ኛ ተከሳሽ [ዘላለም] አማካኝነት ለሽብር ድርጅቱ በአባልነት ተመልምሎ . .. ›› ይላል፡፡ አንድ አንቀፅ ዝቅ ብሎ ደግሞ ‹‹[አብርሃምን] በአባልነት የመለመለው አንደኛ የአቃቤ ሕግ ምስክር [እዮብ] አማካኝነት. . . ›› ይላል፡፡ አብርሃምን የመለመለው ዘላለም ወይስ እዮብ? (ብቸኛው የዐቃቤ ሕግ ምስክር) መልምሏል የተባለው አብርሃምንብቻ አይደለም፡፡ 8ተኛ ተከሳሽ ሰለሞን ግርማንም ጭምር እንጂ፡፡ እዮብ ሰለሞንን ሲመለምል ተናግሯል የተባለው ይህንን ነው፤
‹‹ኤርትራ ሀገር ግንቦት ሰባት የተባለ ጥሩ ድርጅት አለ፡፡ ወታደራዊእና ፖለቲካዊ ሥልጠና ሠልጥነህ ከድርጅቱ ጋር ከተቀላቀልክ በኋላ ግንቦት ሰባት የሚሰጥህን ተልዕኮ ተቀብለህ ከኢትዮጵያ መንግስትጋር እንዋጋለን፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ሕዝቡን በኃይል እየገዛ ነው ስለዚህ ታግለን መጣል አለብን፡፡ ››

የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ከተጠርጣሪዎች ጋር ታስረው ቆይተው ኋላ ላይምስክር ለመሆን ሲስማሙ መለቀቃቸው የተለመደ ነው፡፡ የፀረ ሽብር ሕጉ ሽብርን ለማጋለጥ ለተባበረ ርሕራሔው ይኼን ይመስላል፡፡ ነገርግን ክፍተት አለው፡፡ ተጠርጣሪዎች በአባሪዎቻቸው ወይም ሌሎች ላይ መስክረው መፈታት እንደሚችሉ ቃል ሲገባላቸው በሐሰትም ቢሆንለማድረግ የሚስማሙበት ዕድል አለ፡፡ በዚህ መንገድ መልማዩ ምስክር ሆኖ የሚቀርብበት ተመልማዩ ላይ ይሆናል፡፡
በዚህ ዓይነት መንግስት ያልወደደውን ፖለቲከኛ (ዜጋ) ስልክ ሲደወልደዋዩ አሸባሪ ነው በማለት፣ ወይም የራሱን ሰው ልኮ በማባበል ለ‹‹ሽብር›› መልምሎ ሲያበቃ መልማዩንምስክር ተመልማዩን ተከሳሽ ለማድረግ ወይም ደግሞ በስጋት ሰብስቦ ካሰራቸው ሰዎች መሃከል ለነፍሳቸው ግድ የሌላቸው የሃሰት መስካሪዎችንእያሰለጠነ እየፈረደ ሊኖር ይሆን?!

No comments:

Post a Comment