Sunday, July 12, 2015

የሐይለማርያም ደሳለኝ የጭንቀት ንግግር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን አስታወሰኝ!!

በቅዱስ ዮሃንስ

ከሰሞኑ የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሰራዊት የሕወሓትን ጦርን እያርበደበደና ድባቅ እየመታ መሆኑን ተከትሎ  የሕወሓት ሹማምንት የሚይዙት የሚጨብጡት ነገር እንደጠፋባቸው ከተዘበራረቀ ንግግራቸው መረዳት ይቻላል። ከሕወሓት መንደር ትንቅንቁን በተመለከተ አስተያየት ለመስጠት ቀድሞ ብቅ ያለው የጠቅላይ ሚንስትሩ አማካሪ ጌታቸው ረዳ ሲሆን ግለሰቡ ስለሁኔታው ሲናገር "ግንቦት ሰባት የሚባል ድርጂት የለም፤ ምንም ጦርነት የለም፤ ገንዘብ ማሰባሰቢያ አጀንዳ ናት" በማለት የተለመደ የቅጥፈት እምቢልታውን መንፋቱ የሚታወስ ሲሆን የሕወሓቱ ቅጥረኛ ጌታቸው ይህንን ባለ ሳልስት እንኳ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የትንቅንቁን መካረር ያራደው የሕወሓት ቡድን በአሻንጉሊቱ ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካኝነት ፓርላማ ሰብስቦ ሕወሓት ‘‘ከሻዕብያ’’ ለሚመጣው ትንኮሳ ተመጣጣኝ እርምጃ ሲወስድ መቀየቱን አስታውሶ ‹‹ ‘’የሻዕብያ’’ መንግስት ይህንን ድርጊቱን የሚቀጥል ከሆነ ህዝብ አስፈቅደን አስፈላጊውን እርምጃ እንወስዳለን›› ሲል ተደመጠ። ትላንት ከትላንት ወዲያ ሲክዱት የነበረውን ሃቅ ዛሬ ውጥረትና ፍርሃት ሲንጣቸው ለአደባባይ አበቃው። በዚህ ሁሉ መተረማመስ ውስጥ ታዲያ የሹማምንቱን ግራ መጋባትና እርስ በእርስ የሚጣረዝ አስተያየት በሕወሓት መንደር የነገሰውን የፍርሃት ድባብ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ሲሆን እኔን ፈጽሞ የገረመኝ ነገር ግን ሕወሓት በአሻንጉሊቱ ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካኝነት ያስነገረውና ጦርነቱን ‘’ከሻዕብያ’’ ጋር ለማያያዝና ርካሽ ድጋፍ ከህዝብ ለማግኘት ያደረገው ጉዞ ነው።

በጣም ነው የሚደንቀው። የጠይቅላይ ሚኒስትር ተብየውን ንግግር ሳደምጥ በቅጽበት በአንድ ወቅት የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ የሆነውን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ፍጹም አረመኔያዊ ውንብድ በሆነ መንገድ ከየመን ሰነአ ታፍነው ለጨካኞቹ የሕወሓት ወሮበሎች ተላልፎ መሰጠታቸውን አሰመልክቶ ቃላቸው ለኢሳት የሰጡትን የየአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሊቀመንበር የዶ/ር ብርሃኑ ነጋን ንግግር አስታወኝ።  ዶ/ር የኢትዮጵያን ፖለቲካ በተለይም የሕወሓትን የማፍያ ቡድን ጠንቅቀው በማወቃቸው ይመስለኛል ብዙ ጊዜ የሚናገሩት ነገር ሆኖ አየዋለሁ። ዶ/ር ብርሃኑ ነገ ከነገ ወዲያ የትጥቅ ትግሉ የመቀስቀሱ ነገር አይቀሬ በመሆኑ እና ትንቅንቁ ሲጀመር ሕወሓት ህዝብን በማደናገር ርካሽ ድጋፍ ሊያገኝበት ይራወጣል ብለው ላሰቡት ነገር ቀድመው ምላሻቸው በቃልመጠይቁ ላይ ሰጥተዋል። ዶ/ሩ በቃለ መጠይቁ ወቅት የሰጡትን ማብራሪያና ጥሪ በተመለከተ በዚህ ሰአት እየሆነ ላለው ነገር ግልጽ የሆነ አቋም እንዲኖረን ይረዳል ብየ ሰለ አሰብኩ ለየኢትዮጵያ ህዝብ ለማቅረብ ወደድኩኝ። ምንም እንኳ ፍርዱ የህዝብ ቢሆንም ከትላንት ጀምሮ ሕወሓት በቅጥረኛው ሃይለማርያም አማካኝነት እያስነፋው ባለው የውሸት ነጋሪት ሕዝብ እንዳይሸውድ ለማሳሰብ እወዳለሁ።

ወደ ዋናው ጉዳይ ስመለስ በቃለ መጠይቁ ጊዜ ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ጦርነት ቢነሳ ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል ተብለው የተጠየቁት ዶ/ር ብርሃኑ ምላሻቸውን የሰጡት እንዲህ በማለት ነበር ‘‘ከዚህ በኋላ ለሚንሳው ጦርነት ምክንያቱ ባድመ አይደለም፤ የጦረነቱ ምክንያት አሰብ አይደለም፤ የጦርነቱ ምክንያት ሌላ ነገር አይደለም። የጦርነቱ ምክንያት የወያኔን ስልጣን የሚቀናቀኑ የዲሞክራሲ ሃይሎችን ማጥፋት እንፈልጋለንና ይህንን ለማድረግ ደግሞ እናንተን (የኤርትራ መንግስትን) ማጥፋት አለብን ብሎ የሚነሳ ነው’’ ሲሉ ቁርጥ ያለ መልስ ሰጥተዋል። ዶ/ር ብርሃኑ በማከልም ጦርነቱን በተመለከተ የጥንቃቄ መልዕክታቸውን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲህ በማለት ነበር ያስተላለፉት፤ ‘‘አሁን የምትዋጋው ያለኀው የውጭ ሃይል ወሮህ፤ የውጭ ሃይል ለመመለስ አይደለም። አሁን የምትዋጋው ያለኅው ላለፉት 23 አመታት በዘር እየከፋፈለ፤ እየረገጠ ሲገዛህ የነበረውን ስርአት አንተን ነፃ ለማውጣት የሚፈልጉ የዲሞክራሲና የነፃነት ሃይሎችን ለማጥፋት እሄዳለው ብሎ  የሚነሳ ጦርነት ነው። ’’

እዛ ጦርነት ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ከማን ጋይ ይሰለፋል ለሚለው ለእኔ ቅንጣት ታክል ችግር ያለው issue አይደለም። ስለዚህ በምንም መልኩ ሲታይ ይሄ የሚያዋጣ ስሌት ነው ብየ አላማንም በወያኔ በኩል። ግን ወያኔ የሚሰራው ስራ የሚያዋጣውን ስሌት ነው እየወሰደ የሚል ሃሳብ ካቆምኩ ብዙ ጊዜ ነው። ብዙ ለእነሱም ቆምንለት ለሚሉትም ለምኑም ይጠቅማል የሚባሉ ነገሮች ፊት ለፊት እየተነገራቸው እምቢ እያሉ የሃይልና የጉልበትን የዝርፊያን መንገድን ብቻ መስመራችን ብሎ የያዘ ውንበዴ ሃይል ባለበት ሁኔታ ምክንያታዊ መንገድ የቱ ነው ብለህ ልታሰላ አትችልም።


በመጨረሻም የያኔው ግንቦት 7 የአሁኑ የአርበኞች ግንቦት 7  ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ድርጅታቸውንና በድርጅታቸው የተጀመረው የነፃነት ትግልን አስመልክቶ ለተጠየቁት ጥያቄ እንዲህ የሚል መልስ ነበር የሰጡት፤ ‘’ንቅናቄያችን በአንድ ሰው ላይ፤ በሁለት ሰው ላይ፤ በ አስር ሰዎች ላይ ብቻ የቆመ የፖለቲካ ድርጅት ሳይሆን የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን የነፃነትና የዲሞክራሲ ስሜት መገለጫ የሆነ ለዛ እስከመጨረሻው ድረስ ለመሄድ ዝግጁ የሆነ በጣም ብዙ የተማሩ፤ ያውቁና የበቁ ብዙ የተሻለ ኑሮ ምኖር ሲችሉ ለኢትዮጵያ ነፃነት እስከመጨረሻው ድረስ እንታገላለን ብለው የቆረጡ ሃይሎች ያሉበት ድርጅት ነው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔ ሹማምንት ለሚያደርጉት ማንኛውም የስነ ልቦና ትግል ጆሮ ሳይስጥ በጣም እየፈጠነ ያለውንና በጣም እየተራመደ ያለውን የነፃነት ትግል አካል ሆነን፤ ንቅናቄው የሚጠራቸውን የትግል ሂደቶች እየተቀላቀልን ወደ ነፃነታችን የምናደርገውን ጉዞ እናፋጥን ነው የምለው። ይሄ ደግሞ በፍፁም የሚቀር ነገር አይደለም። እንደዚህ የሚያንግበግባቸውና የሚያቃጥላቸው (የወያኔ ሹማምንትን) መምጣቱን እያዩት ያለ ነገር ነው። እኔ ወያኔዎች በአሁኑ ጊዜ ያሉበት ሁኔታ የሚመስለኝ አንድ በፍጥነት እየመጣ ያለ ባቡር ሲመጣ እያዩት ሊያቆሙት ያልቻሉት ነገር፤ ምን እናድርገው ብለው እየተራወጡ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለ የሚመስለኝ እና የኢትዮጵያ ህዝብ ለማይቀረው ትግል ተዘጋጅ፤ እየመጣን ነው!! ይሄ ትግል ደግሞ ዳር መድረሱን ቅንጣት ታክል አትጠራጠር ነው ማለት የምፈልገው።’’

No comments:

Post a Comment