እኛ ኢትዮጵያውያን ከመቼውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ የሰውነት መብታችን ተገፎ የዜግነት ነፃነታችን ተረግጦና ተዋርደን የምንገኝበት ጊዜ ቢኖር ዛሬ ነው፡፡ የጅምላ ግድያ፤ የጅምላ እስርና የጅምላ ስደት እንደ ዘመነ ወያኔ የታየበት ዘመን የለም፡፡ ህፃናት በረሀብ ከሚማሩበት ክፍል ውስጥ የሚወድቁበት ፤ ወንድ ልጅ በደህንነት ሀይሎች ታፍኖ የሚደፈርበት፤ ሴት ልጅ በገመድ የታሰረ የባልዋነወ ብልት መንገድ ለመንገድ እንድትጎትት የተደረገበት ዘመን ቢኖር ያሳለፍነው የወያኔ ዘመናት ብቻ ነው፡፡ ባጠቃላይ የሰው ልጅ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ መከራና ሰቆቃ እንድንሸከም የተገደድንበት ዘመን ላይ እንገኛለን፡
በአንፃሩም ስለ ለፃነት ስለ ፍትህና እኩልነት ሲሉ የተሰዉ ዋጋም የከፈሉ፤ አሁንም እየከፈሉ የሚገኙ ጥቂት አይደ ሉ ም፡፡ ከነዚህም አንዱ አርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ይህ ለነፃነት ለፍትህና ለ ዲሞክራሲ የሚደረገው ተጋድሎ ውሎ አድሮ ዛሬ ከዋናውና ወሳኝ ከሆነው ምእራፍ ላይ መድረሱ ደግሞ የሁላችንንም ተስ ፋ ያለመለመና የተደፋው አንገታችን ቀና ያደረገ መሆኑና በተቃራኒው የወያኔን ካንፕ ያሸበረ መሆኑ በገሀድ እየታየ የሚገኝ እውነት ነው፡፡
እንግዲህ ይህን ወራዳ ስርአት አስወግዶ በምትኩ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ለመተካት የሚደረገው ትግል ዛሬ የደረሰበት ደረጃ ለመድረስ የተደረገው ርብርብ ቀላል ባይሆንም ቀሪውን አጠናቆ ከዳር ለመድረስ ከመቼውም ጊዜ በላይ የእያንዳዱን ኢትዮጵያዊ የተግባር ተሳትፎ የሚጠይቅ፤ ሁሉም ከያለበት ስለ ነፃነት የሚደረገውን የአርነኝነት ትግል በመቀላቀል የድርሻ ውን ሀላፊነት መወጣት ከሚጠይቅበት ወሳኝ ምእራፍ ላይ መድረሳችንን መረዳት ግድ ይላል፡፡
እኛ ኢትዮጵያውያን ያለ ማንም እርዳታና ድጋፍ ዋጋ ከፍሎ ለፃነትን የማሰከበር እንግዳ ሳንሆን በታሪክ የምንታወቅበት መለያችን መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ እንኳን ዛሬ አለም አለም በጠበበችበት ዘመን ቀርቶ ትናንት በጨለማው ዘመን እንኳ እነ ዶ/ር መላኩ በያን ከአኛ አልፎ ለአፍሪካ ነፃነት ፈር ቀዳጅ ሆነው የተገኙበትን ታሪክ ማስታወስ ይገባል፡፡
እናም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኟውም ስፍራ የሚገኝ ሁሉ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ የሚደረገውን ትግል እውቀት ያለው በእውቀቱ፤ ጉልበት ያለው በጉልበቱ፤ ገንዘብ ያለው በገንዘቡ ለመደገፍ ዛሬ ነገ ሳይል አሁኑኑ ከአርበኝነቱ ትግል መቀላቀል ይጠበቅበታል፡፡ ኢትዮጵያዊነታችንን ብቻ ሳይሆን ሰው መሆናችን የሚረጋገጠው ነፃነታችንን አስጠብቀን በነፃነት መኖር ስንችል ብቻ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡