Saturday, June 6, 2015

የወያኔ 100% የምርጫው ድራማ – ከደምሰው ደስታ

መላዋ ኢትዮጵያ እስር ቤት በሆነችበት ከአሳሪዎቹ ከወያኔ ኢህአዴግ በስተቀር ከ 82 በላይ ብሄር በሄረሰቦች በጠቅላላ በጽኑ እስር ላይና አሳራቸውን በመብላት ላይ ይገኛሉ። ለናሙና ያህል ብንመለከትም ኦልባና ለሊሴና ጓደኞቹ ከኦሮሞ፤ አንዷለም አራጌ፣ የሽዋስ አሰፋና ጓደኞቹ ከአማራ፤ አብርሃ ደስታ ከትግራይ፤ ኦኬሎ አኳይና ጓደኞቹ፣ ከጋምቤላ፤ ባሽር ማክታልና ጓደኞቹ፣ ከሶማሌ ጂጅጋ፤ ዳንኤል ሽበሺና ጓደኞቹ ከደቡብ፤ እስክንድር ነጋ፣ ርእዮት፣ ዉብሸት፣ አቡበክር ፣ከአዲስ አበባ እና ሌሎች ወዘተ ስብጥር ስናይ በእስር ቤት የብሄር ብሄረሰቦችን ተዋጽኦ ለማረጋገጥ በሚመስል መልኩ ወገኑ ያልታሰረበት የሃገሪቱ ክልል በሌለበት ሁኔታ እንዴት ወያኔ 100 % ተመረጡኩኝ ሲለን ትንሽ እንኳን ኢትዮጵያዊ ይ ሉንታ የለበትም።

ከእስር ቤት በስተቀረ የመከላከያ አዛዥነትን ብንመለከት ግን ከ 60 ከፍተኛ መኮንን ውስጥ 58 ቱ ከትግራይ ብቻ በጤናውም እንደዛው የተመደቡ ናቸው ። በየሃይማኖት ተቋማት፥ ብ አዴንም ሆነ በሌሎችም መሰሎች የኢህዲግ ፓለቲካ ድርጅቶች፥ በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የመሪነቱን ሚና በሞኖፓሊ የሚሾፍረረው ወያኔና ወያኔ የሆነ ብቻ ነው።

አባዱላ የተወዳደሩበትን ጨምሮ በበርካታ የምርጫ ጣቢያዎች በህጉ ከተቀመጠው ከመራጭ ቁጥር በላይ ድምፅ ተሰጥቷል ይለናል ሪፖርተር። ነገርዬዋ ግን የድምር ስህተት ናት ወይስ የአስመራጮቹ የኮሮጆ አሞላል ልምድ እጥረት ??? መቼም ከ 1000 በላይ መራጭ ባልተመዘገበበት ጣቢያ ከ 1400 ሰው በላይ ድምፅ ሰጥቶ ኢህአዴግ አሸነፈ ብሎ ማወጅ “ሁሉን አቀፍ” ተቀባይነት አግኝቷል ከተባለለት ቦርድ የሚጠበቅ ሊሆን አይችልም ። ወይ አላጋጭ ቦርድ።

ኢትዮጵያን በገጠርና በከተማ ከፍለን ብናይም መላ ገጠሬው መላ ከተሜው ታስሯል። ገበሬውን አንድ ለአምስት በሚሉት የትብተባ ገመድ በመተብተብ ወሬኛ አድርጎታል። በሰንበት ሳይቀር የሃይማኖት ተቋማትን እንዲተው በማደረግ የክህደት አብዮታዊ ወያኔነትን በግድ ይግቱታል። ከወያኔ መዋቅር አልታቀፍም ካለ የእህል ማዳበሪያ ይከለከላል ስለዚህ ይታሰራል።አንዱ ገበሬ ሌላውን እንዲሰልል በማድረግ ጥንታዊ አብሮነቱን እየሸረሸሩት ነው።

በከተማ ያለው የትራንስፓርት ችግር ሰልፈኛ አድርጎናል። የኑሮ ውድነት የስራ አጥነት ገዝፎ ስራ ለመቀጠር ዬኢ ህ አ ዴ ግ አባል መሆን የግድ ነው። የወጣት ሊግ የአዛውንት ሊግ የሴቶች ሊግ ፎረም ወዘተ የወያኔ የመዋቅር እስር ቤቶች ናቸው። መደገፍ እንጂ መቃወም አይችሉም። ጠቅላይ ምኒስትሩ ኃይለማሪያም ደሳለኝም አሻንጉሊት ናቸው። ሌሎቻችን የበይ ተመልካች መባሉ ቀርቶ ሲበሉ እንዳናያቸው ጭለማ እስር ቤት አጉረውናል። ተፈጥሮኣዊ በሆነው የመናገር የመጻፍ መብታችንን በመጠቀም ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ይኑር፣ ዜጎች በእኩልነት ይታዩ፣ መልካም አስተዳደር ይስፈን፣ የሀገር አንድነት ይጠበቅ ብለን ስንናገር ስንጽፍ እንቀሰፋለን። ይባስ ብሎ ነጻነታችንን ለመለጎም ባወጣው የጸረ ሽብር ህጉ ሰበብ ስለ ፍትህ ስለነጻነት፣ ስለዲሞክራሲ ማቀንቀን ግንቦት ሰባት ወይም ኦነግ አሰኝቶ በአሸባሪነት እድሜ ልክ ያስወነጅላል።

ስድስት ሰላማዊ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንና ሶስት ጋዜጠኞችን ያገተው የካድሬነት ስራ የሚሰራው ፖሊስ የረባ የሃሰት ክስ መጎንጎን አቅቶት ለሁለት ወራት ያህል የፍርድ ቤት ቀጠሮ ሲያራዝም ነበር። ጦማሪያኑ በየብእሮቻቸዉ የሃይል አማራጭ የሚወስዱትን ግንቦት ሰባትንና ኦነግን የሚቃወሙና በሰላማዊ ምርጫ መንግስት እንዲለወጥ የሚወተውቱ መሆናቸው እየታወቀ ግማሾቹን ከግንቦት ሰባት ገሚሶቹን ከኦነግ ጋር ግንኙነት የነበራቸው በማለት የክስ ድራማ ስክሪፕት ከሁለት ወራት መጉላላት በኋላ ጽፎ ሰጥቷቸዋል። የግንቦት ሰባት የፍትሕ የነጻነት የዴሞክራሲ ንቅናቄ መስራችና ዋና ጻሃፊ የነበሩት አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ ታፍነው መያዛቸው በተገለጸበት ቅጽበት በሰላማዊ መንገድ ሲታገሉ ከነበሩ የፓለቲካ ፓርቲዎች አባላት በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች ከሆኑት መካከል አቶ ሐብታሙ አያሌው እና ዳንኤል ሺበሺ ከአንድነት፣አቶ የሺዋስ አስፋ ከስማያዊ ፓርቲ፣አቶ አብርሃ ደስታ ከአረና ትግራይ ተይዘው ወደ ሰቆቃው ማእከላዊ ተወርውረዋል።የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን ከግንቦት ሰባት እና ከአንዳርጋቸው ጋር አቆራኝቶ ለመወንጀል እየሮጠ ያለው ወያኔ ጉልበቱን እና የሃገር አንጡረ ሃብትን በመጠቀም ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል በዜጎች ላይ እየፈጸመ ይገኛል።


እያንዳንዱን ሰው ባሰሩ ቁጥር አሽባሪ የሚል ሰም ይለጥፉበታል። የጸረ ሽብር ህጉ በጣም ልቅ የሆነ ስልጣን አጎናጽፏቸዋል ።ሕገ መንግስቱ ሰው በተያዘ በ 48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ አለበት ቢልም የጸረ ሽብር ህጉ ፓሊስ ከ ሁለት ወር እስከ አራት ወር ጊዜ በላይ ፍርድ ቤት ሳያቀርብ ማገት እንደሚችል ሰለሚፈቅድ ህገ መንግስቱ ተጥሷል። በተጨማሪም ፓሊስ በዘፈቀደ መንገድ ላይ አካሄዱ ያላማረውን ማንኛውም ሰው መያዝ እንዲሁም ያለ ፍርድ ቤት ፈቃድ ግለስብን መበርበር እንደሚችል መብት ሰጥቶታል።ፓሊስ ይህን መስል የካድሬነት ስራ እንዲሰራ ያደረገው ህገ መንግስቱ ተጥሶ ነው። በሰላማዊ መንገድ እንንቀሳቀሳለን የሚሉት ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎች ወያኔ በሰራው አጥማጅ ህግ ከመከሰስ አላመለጡም። ሃሳባችሁን በግል ሚዲያዎች ጋዜጦች፥በኢሳት ቴሌቪዥን በኢንተርኔት ወዘተ ለምን ገለጻችሁ ተብሎ ፓለቲከኞቻችንና የግል ጦማርያንም ታስረዋል።በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ኢብኮ) እንዳይጠቀሙ ማድረጉ ሳያንስ የግል ሚዲያዎች ኢሳትን ጨምሮ መከልከሉ ምንም አትተንፍሱ ሙቱ ማለት ነወ። ሃገር ቤት ያሉ የመጽሄት የጋዜጣ አዘጋጆች የጸረ ሽብር ህጉ ማንኛውም ጽሁፍ አንቀጸ ፮ ሊያስጠይቃቸው ሰለሚችል በጣም እየፈሩ ይገኛሉ። ሁላችንም የፖሊስን ዱላና እስር ቤት ጸበል ጸዲቅ እየተጋፋ እየቀመስን ነው። መንግስት በግልጽ ጣልቃ በሃይማኖት ውስጥ በመግባት የራሱን ካድሬ ቄስና ካድሬ ሼክ ሾሟል ። ይህንን የተቃወሙ ሙስሊሞች በየጁምአው እየታስሩ ይገኛሉ ።ድምጻችን ይስማ እያልናቸው ያፍኑናል። እስከመቼ አንዱ ሲታስር አንዱ ቆሞ ያያል። ቆሞ የሚያያውም ሰለማያገባው ሳይሆን የወያኔን ዱላና እስር በመፍራት ነው። እስከመቼ ሁላችንም በፍርሃት ተሽብበን እንኖራልን ????? የፍርሃት ድባብን በመስበር የታሰርንበትን የፍርሃት ሰንሰለት እንበጥስው።

ከቃሊቲ፥ከማዕከላዊ፥ከዝዋይ፥ከብርሽለቆና ሌሎችም ቦታዎች የታስሩት ወገኖቻችንን ማስፈታት የምንችለው በዞን አስር ታስረን በተወሰነ መልኩ የምንንቀሳቀሰው ሰዎች ነን። ኑሮ ተወደደ ዘረኝነት ስር ሰደደ ብለን ስለተቃወምን የሚገድለን ዘረኛ ፋሺስት ቅኝ አገዛዝ ተወግዶ በዲሞክራሲያዊ በህጋዊ መንገድ የተመረጠ የመንግስት ስርዓት እንዲኖረን የምንፈልግ ፍትህ የናፈቀን ለራሳችን ነጻነት ስንል ለፍልሚያ መዘጋጀት ግድ ይለናል።

No comments:

Post a Comment