
በህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ በየመን የፀጥታ ሃይሎች ተይዘው አለማቀፍ ህግን በጣሰ አካሄድ ለጉጅሌዎቹ ተላልፈው የተሰጡት የንቅናቄው ዋና ፀሐፊ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሥራዎች በምስልና በቪዲዮ ተቀናብረው ለእይታ የቀረቡ ሲሆን የነፃነት አርበኛው የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ስራዎችና አሁን ላይ በጠላት እጅ መውደቃቸው ኢትዮጵያውያኑን በቁጭት አስነብቷል፤ በበለጠ ትግሉ ለሚጠይቀው ማንኛውም መስዋዕትነት በእልህና በቁጣ ያነሳሱዋቸው እንደነበሩም ለማወቅ ተችሏል።
ኢትዮጵያውያኑ ፋሽስቱ ወያኔን ማስወገድ በሚቻልባቸው የትግል ስልቶች ላይ ሰፊ ውይይት ከድርጅቱ አመራሮች ጋር ያደረጉ ሲሆን ኢትዮጵያውያኑ በንቅናቄው የተነደፉትን የትግል ስሎች በማድነቅ ወደፊትም የጉጅሌው ወያኔን በመገርሰስ ትግሉን ከዳር ለማድረስ ለሚጠይቃቸው ማንኛውም አይነት መስዋዕትነት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፤ ኢትዮጵያውያኑ በአንድነት እጅ ለእጅ በመያያዝም ትግሉን ከዳር ለማድረስ ቃል ኪዳን መግባታቸው ተዘግቧል። ትግሉን ከዳር ለማድረስ በገንዘብ፤ በሰው ሃይልና በዕውቀት ረገድ ድጋፍ በማድረግ ከንቅናቄው ጎን እንደሚሰለፉ ቃል መግባታቸውንም ዘጋቢዎቻችን አመልክተዋል። በቅርቡ የተሰማው ውህደትን የተመለከተው የብስራት ዜና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ተቀራርቦ በጋራ መስራት የሚቻልበት ሁኔታዎች መመቻቸት እንዳለበት ኢትዮጵያውያኑ ማሳሰባቸው ታውቋል።
በመጨረሻም የነፃነት ትግሉ የደረሰበትን ደረጃ በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡት የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች አሁን ወሳኝ የትግል ምዕራፍ ላይ ደርሰናልና ሁሉም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በአንድነት ልንረባረብ ይገባል በማለት ኑ! ኢትዮጵያ አገራችንን፣ ኢትዮጵያዊ ወገናችንን እና ራሳችን ነፃ ለማውጣት እና በሀገራችን ፍትህና ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ለማድረግ በምናደርገው ትግል ተቀላቀሉን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። ለቀረበውን አገር አድን ጥሪ ምላሽ በመስጠት በሁሉም የህዝባዊው ስብሰባ ቦታዎች ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን በትግሉ ለማሳተፍ በአባልነትና ደጋፊነት አስተዋዕጽኦ ለማበርከት መመዝገባቸውንም ለማወቅ ተችሏል። በተጨማሪም በአገር ውስጥና በውጭ አገር ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች፤ እና ለኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የጉጅሌው ወያኔን አገዛዝ ለማስወገድ እየተደረገ ያለውን የሞት ሽረት ትግል እንዲቀላቀሉ ጥሪ መቅረቡንም ለማወቅ ተችሏል።
No comments:
Post a Comment