Thursday, September 26, 2013

እንደ ቆራጥ ንስር ፓይለቶቹ…

ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያውያን ዘንድ ዋና የመነጋገሪያ አርዕስት የነበረው አራት የአየር ሃይል አብራሪዎችና አስልጣኝ መኮንኖች ከዘረኞቹና ከዘራፊዎቹ ጎራ ወጥተው ወደ ነፃነት ታጋዮች ጎራ የመቀላቀላቸው ጉዳይ ነበር። እነዚህ ቆራጥና አገር ወዳድ አብራረዎች የወሰዱት እርምጃ ወገንን የሚያኮራና ከፍተኛ ጀግንነትን የሚጠይቅ ትልቅ ውሳኔ ነው።ይህ ውሳኔ ሰው ባጣች አገር፤ጀግና ባጣች አገር፤ለአገር ለወገን ተቆርቋሪ ባጣች አገር ውስጥ ትልቅ ተስፋ ሰጪ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በያለበት በተለያየ መንገድ ይህን የጀግና ውሳኔ የወሰኑ ልጆቹን እያደነቀም እያመሰገነም ይገኛል::

የግንቦት ሰባት ንቅናቄም ይህን የጀግና ውስኔ የወሰኑ ወንድሞቹን እንኳን ተወለዳችሁ፤ እንኳንም ተማራችሁ፤ እንኳንም ወደ ነፃነቱ ትግል ተቀላቀላችሁ እያለ ደስታውንና ለጀግኖቹ ያለዉን ከፍተኛ አክብሮት ይገልፃል። ውሳኔያችሁ ከፈርዖን ቤተ-መንግስት ምቾት ይልቅ ከህዝቤ ጋር መሰደደ ይሻለኛል ያለውን የታላቁን ሰው የሙሴን ውሳኔ ይመስላልና የወሰዳችሁትን ትክክለኛ እርምጃ ትውልድ ምን ግዜም አይረሳዉም።

የእነዚህ ቆራጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆች፣ ሙያና ችሎታ ስጋዊ የሆነ ፍላጎታቸውን ለማርካት ከበቂ በላይ ነው።ከዘረኞቹና ከቃየላውያኑ ቡድኖች ጋር እየተሞዳሞዱ ለመኖርም የሚሳናቸው አልነበሩም።ሆኖም ግን ዘረኞቹ(ህወሃቶች) የሚፈፅሙትን ግፍ ተሸክመው ፤ብኩርናቸውን ሽጠው እና ከሰው ተራ ወርደው ለመኖር ሂሊናችው አልፈቀደላቸውም።ለሚበላና ለሚጠጣ ከንቱ ነገር ብለው ጥቂት ዘረኞችን ተሸክሞ ከመኖር ይልቅ የነፃነቱን መንገድ መርጠዋልና ጀግኖች ብለን ብናወድሳቸው ተገቢ ይሆናል። እንዲህ ዓይነቱን ውሳኔ የሚወስን ሃሞተ ኮስታራ ጀግና እንጂ ሌላ አይደለም።

አሁንም ለራሳችሁ ክብር ያላችሁና ተመሳሳይ እርምጃ ለመዉሰድ በዝግጅት ላይ የምትገኙ የአገር መከላከያ አባላት እንዳላችሁ እናውቃለን። ቅምጥሎቹ ጄኔራል ተብየዎች ከድሃ ወገኖቻችሁ ላይ የዘረፉትን ዘርፈው አገሪቷን ጥለው መሄድ ጀምረዋል። ቀሪዎችም የዘረፉትን የድሃ ንብረት ወደ ውጪ አገር እያሸሹ እንደሆነም ይታወቃል።በአጠቃላይ በእናንተ ምርኩዝነት አገራችንን እያፈራረሷት፤ህዝቧንም እያወረዷት ነው።የህዝቡም መከራና እሮሮ ተወርቶ የሚያልቅ አይደለም።እንዲህ አይነቱን ግፍና በደል እያዩ ከንፈር መምጠጥ እያበቃ ነው።እንግዲህ አሁን እኔ ብቻየን ምን አደርጋለሁ የሚባልበት ግዜ እያለፈ ነው።ጋሻ መከታ እና የኋላ ደጀን የሚሆኗችሁ ብዙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን በየቦታው አሉ።ብትወድቁ የሚያነሷችሁ፤ብትደሙ ደማችሁን የሚያብሱላችሁ፤ብትሰው መስዋእትነታችሁን ለትውልድ የሚዘክሩላችሁ ወገን አለላችሁ።አትፍሩ። ከዘረኞቹ መንደር ወጥታችሁ የነፃነቱን ትግል እንድትቀላቀሉ ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን።

ህውሃት ማለት የዘራፊዎች እና የጨካኝ ነፍሰ ገዳዮች ስብስብ መሆኑን ያለምንም ጥርጥር ማመን አለባችሁ።ህወሃት ስንቱን አርዶ፤ስንቱን ገድሎ፤ስንቱን አጥፍቶ፤የስንቱን ኑሮ በትኖ፤ስንቱን ዘርፎ ባዶ እጁን አስቀርቶ በትረ ስልጣኑን እንደያዘ ምስክር የሚያስፈልገን አይደለም።

የህውሃት ዘረኝነትና ዝሪፊያ የቆጨህ እና ለራስህ ክብር ያለህ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ተነስተህ ትግሉን ተቀላቀል።እነዚህን ግፈኞች የሚፈፅሙትን በደል እያዩ ዝም ማለት ግፉን ከመደገፍ ተለይቶ የሚታይ አይደለም።እናንተ ለራሳችሁ፤ ለወገናችሁና ለአገራቸችሁ ክብር ያላችሁ ዜጎች ዝም በማለታችሁ ህወሃቶች ዝምታችሁን እንደ በጎ ፈቃድ ቆጥረውት የግፍ ሰይፋቸውን ወደ ሰገባው ሊመልሱ ፈቃደኞች አልሆኑም።በማን አለበኝነታችውም ፀንተው ቆመዋል።እነዚህን ግፈኞች በቃ ለማለት ግዜው ደርሷልና የነፃነቱን ትግል ሳትዘገዩ አሁኑኑ ተቀላቀሉ።

እኛም ወደ ነፃነት ትግሉ እንድትቀላቀሉ ጥሪ ስናደርግላችሁ ለአገራችን ክብርና ለወገኖቻችን በሰላም መኖር ስንል ቆርጠን የተነሳን መሆናችንን ልንገልጽላችሁ እንወዳለን።የግንቦት ሰባት ንቅናቄ በምንም ሁኔታ በዘረኞች እጅ ተንቆና ተዋርዶ መኖርን አይቀበልም።እንዲህ ዓይነቱን ውርደት ተቀብሎ ለመኖር ሰው መሆናችን ይከለክለናል።እነዚህን ዘራፊዎች ተሸክመን ከመኖር ከነፃነታችን ጋር አያቶቻችን በተሰውበት ተራራ ላይ ቆመን መሰዋትን እንመርጣለን።አሁን ተነስተናልና የሚያቆመን የለም። እግዚአብሄርም መንገዳችንን ያከናውንልናል። ኑ ሀገርን ለማዳን የነጻነት ትግሉን ጎራ ተቀላቀሉ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Wednesday, September 25, 2013

የሙስሊሞች ጉዳይ መፍትሔ ይሻል!!!

በአብርሃ ደስታ

የናይሮቢው የዌስትጌት ሞል ጥቃት አሰቃቂ ነው። ግን ጥቃቱ ለኛ ኢትዮዽያውያን ምን ዓይነት ስሜት ፈጠረ? “የተለያየ ስሜት” እንበለው ላለመሳሳት። በዚህ ጉዳይ ኬንያና ኢትዮዽያ ይመሳሰላሉ እንዴ?

በኬንያ ግለሰቦች ንፁሃን ሰለማዊ ዜጎችን በገበያ ማእከል ያግዳሉ፣ ያሰቃያሉ፣ ይገድላሉ። በኢትዮዽያ ደግሞ የገዢው ፓርቲ ፖሊሶች ንፁሃን ሰለማዊ ዜጎችን በመስጂዶች ያግዳሉ፣ ያሰቃያሉ፣ ይገድላሉ። ስለዚህ በኬንያና በኢትዮዽያ ዉስጥ የሚፈፀሙ ድርጊቶች የሚመሳሰሉበት ነጥብ በሁለቱም ተጠቂዎቹ ሰለማዊና ንፁሃን ዜጎች መሆናቸው ነው። የሚለያዩበት ደግሞ በኬንያ ጥቃት የሚፈፅሙ ግለሰቦች ሲሆኑ በኢትዮዽያ ግን የመንግስት ሃይሎች ናቸው።

ይቅርታ!

በሁለቱም ሀገሮች የሚፈፀሙ ጥቃቶች ይመሳሰላሉ። በኬንያ ለተፈፀመ ድርጊት ሓላፊነት የወሰደ አልሸባብ አይደለምን? ስለዚህ በናይሮቢ የሽብር ተግባር የፈፀሙ ሃይሎች ግለሰቦች ሳይሆኑ ድርጅት ነው። ምክንያቱም ጥቃቱ የፈፀመው አልሸባብ ነው። አልሸባብ ደግሞ ድርጅት ነው። በኢትዮዽያ የሚፈፀመውም በገዢው ፓርቲ ነው። ገዢው ፓርቲ ድርጅት ነው። ስለዚህ በሁለቱም ሀገሮች የሚፈፀሙ ጥቃቶች በድርጅቶች የትፈፀሙ ናቸው። ስለዚህ ይመሳሰላሉ።

እንደገና ይቅርታ!

በሌላ ነጥብ ደግሞ ይለያያሉ። አልሸባብ ስልጣን ያልያዘ፣ የህዝብ ሓላፊነት ያልተሸከመ፣ በግልፅ የተወገዘ ቡድን ነው። የኢህአዴግ መንግስት ግን ስልጣንና የህዝብ ሓላፊነት አለበት። ሌላ ደግሞ አልሸባብ ጥቃቱ የፈፀመው በሌላ ሀገር ህዝቦች ነው (ለመበቀል)። ኢህአዴግ ግን በራሱ ህዝብ ላይ ነው የሚፈፅመው (በስልጣን ለመቆየት)።

ጥቃት ይፈፀማል፤ የሚፈፀመው ግን ተስፋ በቆረጡ ሃይሎች ነው። የግል (ወይ የድርጅት) ዓላማቸው ለማሳካት በሰለማዊ ህዝብ ላይ የሽብር ጥቃት የሚሰነዝሩ አሉ። እነ አልሸባብና ቦኮ ሃራም የሚጠቀሱ ናቸው። ግን የአልሸባቦችና የቦኮ ሃራሞች ተግባር በማጣቀስ የኢትዮዽያውያን ሙስሊሞች ጥያቄ ለማድበስበስ መሞከር ተገቢ አይደለም። የኢትዮዽያ ሙስሊሞች ሕጋዊ ጥያቄና ሰለማዊ ተቃውሞ ከነ አልሸባብ የሽብር ተግባር ጋር ምን አገናኘው?

ጥያቄያቸው በሰላማዊ መንገድ የሚገልፁና በህዝቦች ላይ ጥቃት የሚፈፅሙ እንዴት ይገናኛሉ? ስለዚህ የኢትዮዽያ ሙስሊሞች ጥያቄ ላለመመለስ ጉዳያቸው ከቦኮ ሃራሞች ተግባር ማመሳሰል ተገቢ አይደለም። 

የኢትዮዽያ ሙስሊሞች ጥያቄ አላቸው። ጥያቄያቸውም በሰለማዊ መንገድ እያሰሙ ነው። ጥያቄያቸው ምን ይሁን ምን መልስ ያስፈልገዋል። የዜጎችን ጥያቄ መመለስና በግዛቲቱ ለሚነሱ ማናቸውም ችግሮች መፍትሔ ማፈላለግ የመንግስት ግዴታ ነው። መንግስት ለችግሩ መንፍትሔ ካላመጣ ግዴታው በአግባቡ እየተወጣ አይደለም ማለት ነው። ግዴታው መወጣት ካልቻለ ስልጣኑ (የህዝብ ሓላፊነቱ) ለህዝብ መልሶ ማስረከብ አለበት፤ ምክንያቱም ሊሰራበት አልቻለማ።

የአብዛኞቹ ሙስሊሞች ጥያቄ ሃይማኖታዊ ነው ብዬ አስባለሁ። ግን የተወሰኑ ግለሰቦች የራሳቸው ሌላ ዓላማ ሊኖራቸው (ወይ ላይኖራቸው) ይችላል። ሁሉም ሙስሊሞች የተለያዩ ሰዎች እስከሆኑ ድረስ ተመሳሳይ ሃይማኖት ስላላቸው ብቻ ተመሳሳይ ሓሳብና ፍላጎት ይኖራቸዋል ማለት አይቻልም። ግን አንድ ግልፅና ለሁሉም ሙስሊሞች የጋራ ነጥብ የሆነ ጥያቄ አላቸው፤ “መንግስት በሃይማኖታችን ጣልቃ አይግባብን” የሚል። ሌላ ተጨማሪ ጥያቄም ቢኖር መብታቸው ነው። የመንግስት ግዴታ ጥያቄያቸው ማፈንና ማጥላላት ሳይሆን የመፍትሔ መልስ መስጠት ብቻ ነው።

የኢትዮዽያ መንግስት ግን ለሙስሊሞቹ ጉዳይ መፍትሔ ከማፈላለግ ይልቅ ጥያቄያቸውን ማጥላላት ይዟል። ጥያቄያቸው በሰለማዊ ሰልፍ ለሚገልፁ የኢትዮዽያ ሙስሊሞች ዓላማቸው በሃይል ማስፈፀም ከሚፈልጉ አልሸባቦችና ቦኮሃራሞች ጋር ማመሳሰል?

የኢትዮዽያ መንግስት እየተከተለው ያለው ስትራተጂ አደገኛ ነው። ዜጎች ሰለማዊ ሰልፍ ሲወጡ በፖሊስ ከተደበደቡ አማራጫቸው ምን ሊሆን ነው? መንግስት ምን ዓይነት መልእክት እያደረሳቸው ነው? “በሰለማዊ መንገድ ስለማይሳካ ሌላ የዓመፅ መንገድ ብትሞክሩ ይሻላችሃል” እያላቸው ነው? ወይስ ምንድነው? ሙስሊሞቹ ከአንድ ዓመት በላይ ጥያቄያቸው በሰለማዊ መንገድ ሲገልፁ ቆይተዋል። እስካሁን ተስፋ አልቆረጡም (ተስፋ ባለመቁረጣቸው አደንቃቸዋለሁ)።

ሰማያዊ ፓርቲ ሕገ-መንግስት አረቀቀ!!!

‘‘የአሁኑ ሕገ-መንግስት የኢህአዴግ ፕሮግራም ቅጂ ነው’’ ኢንጂነር ይልቃል

በቅርቡ የተመሰረተው የሰማያዊ ፓርቲ ‘‘የዜጎች የቃል ኪዳን ሰነድ ለዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ’’ በሚል መርህ ወደፊት የፖለቲካ ሥልጣን ሲይዝ የሚመራበትን አዲስ ህገመንግስት ማርቀቁን አስታወቀ። ረቂቅ ሰነዱ ላይ ምሁራንና ባለሙያዎች ውይይት ካደረጉ በኋላ ለሕዝብ እንደሚቀርብ ፓርቲው አስታውቋል።

የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት በአዲሱ ረቂቅ ሕገ-መንግስት ላይ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ውይይት እንደሚደረግ አስታውቀዋል። በውይይቱ ላይ ከዚህ በፊት የነበሩ ሦስት ህገ-መንግስቶች ድክመትና ጥንካሬ ምንድን ነው? አዲስ በሚረቀቀው ህገ-መንግስት ምሰሶዎች ምን ይሆናሉ፣ ስልጣንና ሕዝብን እንዴት ማገናኘት ይቻላል በሚሉ ወሳኝ ንድፈ ኀሳቦች ላይ የጠለቀ ውይይት እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

‘‘የአሁኑ ሕገ-መንግስት የኢህአዴግ ፕሮግራም ቅጂ ነው’’ ያሉት ኢንጂነር ይልቃል እያረቀቁ ያሉት ሕገመንግሥት የሰነድ ዝግጅቱም ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁንና ምሁራን በሚያደርጉት ውይይት ከዳበረ በኋላ ለሕዝቡ ውይይት ቀርቦ ለባለሙያዎች ተመርቶ ዝርዝር ህጎች እንዲፃፉ ይደረጋል ብለዋል።

ፓርቲው ሰላማዊ ሰልፍ የሚያካሂደው ሕዝቡን ለማነቃቃትና ለማስተማር አባላትንም ለመመልመል ቢሆንም በተጓዳኝ ፓርቲውን ለማጠናከርና ምን አይነት ስርዓት እንገነባለን የሚለውንም ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ኢንጂነር ይልቃል ገልፀዋል።

ሰማያዊ ፓርቲ ሕገ-መንግስት ባለበት ሀገር ሌላ ሕገ-መንግስት ከማውጣት የሚያግደው ነገር እንደሌለ የጠቀሱት ኢንጂነር ይልቃል፤ ፓርቲው እያካሄደ ያለው ትግል በሕገ-መንግስት የማይመራን አገዛዝ በዲሞክራሲያዊ ስርዓት የመተካት ስለሆነ አዲስ ህገ-መንግስት ማስፈለጉ የግድ ነው ብለዋል።

የፓርቲው ዋና አላማ በሀገሪቱ ሕጋዊ ስርዓትን መትከል በመሆኑ አሁኑ ባለው ሕግ-መንግስት በሚደረግ ምርጫ አብላጫ ወንበር ማግኘቱን ሲያረጋግጥ አዲሱን ሕገ-መንግስት ተግባራዊ ያደርጋል ብለዋል። በዚህ ሀገር ምርጫ ከተካሄደም ሰማያዊ ፓርቲ 99.6 በመቶ አብላጫ ወንበር ለማግኘት የሚያግደው ነገር እንደሌለም እርግጠኞች ነን ሲሉ አያይዘው ገልፀዋል።

ፓርቲው ከፖለቲካና ኢኮኖሚ አማራጭ ፕሮግራም በዘለለ አዲስ ህገ-መንግስት ማርቀቁ ቀዳሚ ተግባር መሆኑን የጠቀሱት ኢንጂነር ይልቃል፤ የፓርቲው አማራጭ ፕሮግራም የሚመነጨው ከረቀቀው ሕገ-መንግስት ነው ብለዋል። አዲሱ ህገ-መንግስት በሀገሪቱ ስለሚኖረው አጠቃላይ ስርዓትና መንግስታዊ አወቃቀር፣ የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ የገበያ ስርዓት፣ ዓለም አቀፍ ግንኙነት፣ የመሬት ፖሊሲ፣ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ ገዥ ኀሳቦች የሚመነጩት ከህገ-መንግስት እንደሆነ ገልፀዋል። የፓርቲው ፕሮግራም ከህገ-መንግስቱ የሚመነጩ ዝርዝርና ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ በመሆኑ ቀዳሚውና ምሰሶው ሕገመንግስት ነው ብለዋል።

‘‘የኢትዮጵያ ችግር መጠነኛ ችግር ሳይሆን አጠቃላይ ሕጋዊ ስርዓት የመትከልና፤ የሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎችን መብት፣ ባህል፣ ታሪክን ግምት ውስጥ ያስገባ ስርዓት የማቋቋም ጉዳይ ነው’’ ያሉት ኢንጂነሩ አሁን ካለው ህገ-መንግስት ሊካተቱ የሚችሉት የሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ ድንጋጌዎች እና ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የፈረመቻቸውን ድንጋጌዎች እንደሆኑም አስገንዝበዋል። ኢህአዴግ ለሀገር ደህንነትና ለህዝብ ጥቅም ሽፋን ከሕዝብ ነጥቆ የወሰዳቸው መብቶች በአዲሱ ህገ-መንግስት እንደሚካተቱ አመልክተዋል። ከኢህአዴግ መሠረታዊ ባህሪ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ የሕዝብን አንድነት የሚነኩ፣ የተዛባውን የፌዴራሊዝም ጉዳዮች እንደገና የሚታዩ መሆኑንም ጠቁመዋል።

አዲሱ ህገ-መንግስት በማርቀቅ ሂደት ላይ ታላላቅ ምሁራን የተሳተፉበት መሆኑን ያስረዱት ኢንጂነሩ ውይይቱ በቅርቡ የትና መቼ እንደሚደረግ ፓርቲው ያሳውቃል ብለዋል።

በተያያዘ ባለፈው ዕሁድ ፓርቲው የጠራው ሰልፍ አለመካሄዱን በተመለከተ ኢንጂነር ይልቃል ተጠይቀው ሕጋዊው ስርዓት የውሸት እንደሆነ፣ ኢህአዴግ ትልቅ የህዝብ ፍርሃት እንዳለበትና ሕዝባዊ ተቀባይነቱ ባዶ እንደሆነ የተገነዘብንበት አጋጣሚ ነበር ሲሉ መልሰዋል።


ባለፈው እሁድ መስከረም 12 ቀን 2006 ዓ.ም ፓርቲው የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በመንግስት በኩል ጃንሜዳ ማካሄድ እንደሚችሉ በመግለፅ በአንፃሩ ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፉን ለማካሄድ የጠየኩት መስቀል አደባባይ ነው በማለቱ ሰላማዊ ሰልፉ ከፓርቲው ጽ/ቤት በግምት አንድ መቶ ሜትር ከተካሄደ በኋላ ግንፍሌ ድልድይ ላይ በፖሊስ እንዲቋረጥ መደረጉ አይዘነጋም፡፡ 

ምንጭ፡ ሰንደቅ ጋዜጣ

Tuesday, September 24, 2013

ግንቦት ሰባት የኤርትራ ድጋፍ እንዳለው አስታወቀ!!!


“የወያኔን መንግሥት ከሥልጣን ማስወገድ ዋነኛው አጀንዳዬ ነው” የሚለው ግንቦት 7 የፍትሕ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ በኤርትራ ምድር እንደሚንቀሣቀስና ከኤርትራ መንግሥትም እገዛ እንደሚያገኝ አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ ዋሽንግተን ዲሲና በአካባቢው ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ትናንት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ እያከናወንኩ ነው ስለሚላቸው እንቅስቃሴዎች መሪዎቹ ማብራሪያና ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችም መልስ ሰጥተዋል፡፡


ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Monday, September 23, 2013

በሳውዲ ወላጆችና የኤምባሲ ኃላፊዎች ተካርረዋል!!!

ማቆሚያ ያጣው የኢህአዴግ ጣልቃገብነት

ወላጆች ንብረቶቻቸውን ከዘራፊዎች ለማስጣል በሪያድ ከኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ጋር እያደረጉ ያለው ትንቅንቅ ዛሬ ወደ ግጭት አመራ።

በወላጆች እና በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ በዲፕሎማቶች መሃከል ሴፕቴምበር 22፣ 2013 ምሽት ተፈጥሮ የነበረው ግጭት ለጊዜው ጋብ ቢልም መንግስት በጉዳዩ ጣልቃ ገብቶ የተማሪዎቹ ወላጆች በተደጋጋሚ ላቀረቡት ጥያቄ አስቸኳይ መላምት ካላፈላለገ ጉዳዩ የከፋ ሊሆን እንደሚችል የወላጆች ኮሚቴ አባላት ይገልጻሉ!

በተለይ ዛሬ ሴፕቴምበር 22/2013 ምሽት በሪያድ ዓለምአቀፍ የኮሚኒቲ ት/ቤት ተማሪ ወላጆች ኮሚቴ የሳውዲ መንግስት በውጭ ሃገር ዜጎች ላይ ያወጣውን ህግ ተከትሎ በኤምባሲው የተመረጠው የት/ቤቱ ህገወጥ፣ የቦርድ አስተዳደር «የመኖሪያ ፈቃድ አልተሞላም፣ ፓስፖርት አልታደሰም፣ ቦንድ አልገዛችሁም፣ ወላጆቻችሁ የድምጻችን ይሰማ ደጋፊዎች ናቸው፣ … ወዘተ» በጣም አሳዛኝ እና ግብረገብነት በጎደለው ሰንካላ ምክንያት ከ1ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው ማፈናቀሉ ይታወሳል።

በመሆኑም የአያሌ ኢትዮጵያውያን ህጻናት በሰው ሃገር ከትምህርት ገበታቸው መፈናቀል የአብዛኛውን ወላጆች በልጆቻቸው ላይ ያላቸው ተስፋ እንዲጨልም አድርጓ። ይህንንም የተረዳው 11 አባላት ያሉት የት/ቤቱ የወላጆች ኮሚቴ ከ1ሺህ የሚበልጥ የድጋፍ ፊርማ በማሰባሰብ ኤምባሲው በራሱ ስልጣን መርጦ ህገወጥ በሆነ መንገድ ያስቀመጠው የት/ቤቱ ቦርድ አዲስ የትምህርት ዘመን መጀመርን አስመክቶ ያወጣውን የአዲስ እና ነባር ተማሪዎች መመዝገቢያ መመዘኛዎች ትክክለኝነት በመጠራጠር ኮሚቴው የሳውዲ ት/ሚኒስቴር መ/ቤት ድረስ በመሄድ ለማጣራት ባደረገው ሙከራ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች በእጅ አዙር እንዳይመዘገቡ ታግደው ከነበሩ 1ሺህ ኢትዮጵያውያን ህጻናት ውስጥ 8 መቶው የሳውዲ ት/ሚ ያወጣውን ህግ የሚያሟሉ መሆናቸውን በማረጋገጥ፡ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ኮሚቴው ማስቻሉን ተከትሎ ወላጆች በተጠቀሰው ቦርድ እና ከቦርዱ ጀርባ ሆነው በሪያድ ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ት/ቤትን የመማር ማስተማር ሂደት እያመሰቃቀሉ ባሉ ወገኖች ዙሪያ ለመነጋገር ሴፕቴምበር 22 ፣2013 የወላጅ ኮሚቴው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ ስብሰባ ጠርቶ እንደ ነበር የወላጆች ኮሚቴ ተወካይ ይገልጻሉ።

ተወካዩም በማያያዝ ቀደም ብለው ስብሰባ ያደርጉባቸው የነበሩ ቦታዎች ወላጆች በግል በሚከራይዋቸው አካባቢያቸው በሚገኙ የመዝናኛ ቦታዎች መሆኑንን ጠቀሰው በሪያድ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ሃላፊ የሆኑት አቶ ተመስገን ኡመር ይህ አዳራሽ እያለ ለምን ለድህነታችሁ አስተማማኝ ያልሆነ ቦታ ትሰበሰባላችሁ ከኤምባሲው እና ከኮሚኒቲው ርቃችሁ በድብቅ ስብሰባ ለምን ታደርጋላችሁ በሚል ቅን አስተሳሰብ ለወላጆ ኮሚቴው በሰጡት ሞራል እና ምክር ኮሚቴው ለእሁድ ቀን ሴፕቴምበር 22 2013 ከምሽቱ 7 ስዓት ጀምሮ ወላጆች በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ፡ እንዲገኙ የስብሰባ ጥሪ በደብዳቤ እንደበተኑ ያወጋሉ።

Sunday, September 22, 2013

ወጣቱን ፖሊስ በጥይት ደብድቦ ገደለው!!!

* በሚያዝያ ወር 2006 ዓ.ም. ጋብቻ ለመፈጸም ፕሮግራም ነበረው

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ጎጃም ዞን በጐንጅ ቆለላ ወረዳ በሸበሌ ቀበሌ ዘመናዊ የግብርና አሠራር ለአካባቢው ነዋሪዎች በማሠልጠንና አብሮ በመሥራት ላይ የነበረ ወጣት የግብርና ኤክስፐርት፣ ፖሊስ በጥይት ደብድቦ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደገደለው ዘመዶቹና የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡


በአካባቢው ለፖሊሲ ኮሙዩኒቲንግ ሥራ ከወረዳው በተላከ ፖሊስ በጥይት ተደብድቦ ሕይወቱ አልፏል የተባለው የግብርና ኤክስፐርት ዘለዓለም ፀሐይ የሚባል የ29 ዓመት ወጣት መሆኑን የገለጹት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ በ2002 ዓ.ም. ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በግብርና የትምህርት ዘርፍ ከተመረቀ በኋላ፣ ላለፉት ሦስት ዓመታት ‹‹ያሳደገኝን አርሶ አደር መርዳት አለብኝ›› በማለት ከከተማ ሥራ ይልቅ ገጠሩን መርጦ ሲያገለግልና ሲያሠለጥን እንደነበር አስረድተዋል፡፡ 

ከክልሉ፣ ከዞኑና ከወረዳው ሳይቀር ልዩ ምሥጋናና አድናቆት ሲቸረው የቆየ ኤክስፐርት እንደነበር የሚናገሩት ነዋሪዎቹ፣ ለቀበሌው ተመድቦ የነበረው ረዳት ሳጅን ታከለ በላይ የተባለ ፖሊስ፣ ከቤቱ ጠርቶ ለሕጋዊ ሥራ በተሰጠው መሣሪያ በጥይት ደብድቦ እንደገደለው ተናግረዋል፡፡ በጥይት ከመግደሉ በፊት በድንጋይ መትቶ ጥሎት እንደነበረም ጠቁመዋል፡፡ 

ፖሊሱ ግድያውን ሊፈጽም የተነሳበት መሠረታዊ ምክንያት ይኑረው ወይም አይኑረው ለጊዜው የሚያውቁት ነገር እንደሌለ የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ ግድያውን በፈጸመበት ነሐሴ 30 ቀን 2005 ዓ.ም. ግን፣ ገዳይ ሟችን ከተኛበት ቀስቅሶ ‹‹ኳስ እንጫወት›› በማለት ወደ ሜዳ ወስዶት ሲጫወቱ ቆይተው ለማንም ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ ከተጨቃጨቁ በኋላ፣ ተጠርጣሪው ገዳይ በድንጋይ ጭንቅላቱን መትቶ ከጣለው በኋላ፣ ወደ ቤቱ በመግባት መሣሪያ አምጥቶ እንደገደለውና እጁን ለፖሊስ እንደሰጠ አስረድተዋል፡፡ 

የገደለበትን ምክንያት ምን እንደሆነ ወደፊት በምርመራ የሚታወቅ ቢሆንም፣ መግደሉን አምኖ እጅ ሲሰጥ የክልሉ ፖሊስ ኃላፊነቱን በመውሰድ ቤተሰቦቹንና የአካባቢውን ነዋሪዎች ማፅናናትና እንዲረጋጉ ማድረግ ሲገባው፣ ይህንን ሳያደርግ በመቅረቱ ቤተሰቦቹንና ነዋሪውን እንዳስቆጣ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ 

መንግሥት ለዜጎች ደኅንነት በማሰብ የመከላከያና የፖሊስ ሠራዊትን ሲመለምል ከአቋም መለኪያ በተጨማሪ ያለውን ሥነ ምግባር፣ አስተዋይነትና የትምህርት ደረጃውን መሠረት አድርጎ ይሆናል የሚል ግምት እንዳላቸው የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ አሁን አሁን ግን በክልሉ ከባህር ዳር ጀምሮ፣ በአንዳንድ ዞንና ወረዳዎች በታጣቂ ፖሊሶች እየደረሰ ያለው የግድያ ወንጀል ሥጋት ውስጥ እንደከተታቸው አስረድተዋል፡፡ የፌዴራልም ሆነ የክልሉ መንግሥት በፖሊስ አመላመልና ሠልጥነው በሥራ ላይ ያሉትን ፖሊሶች ሥነ ምግባር፣ ከተሰጣቸው ተልዕኮና ሕዝብን ከማገልገል አንፃር እየተገበሩት ስለመሆኑ መፈተሽ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ የአገሪቱ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነውን ግብርናን በተሻለና ዘመናዊ በሆነ መንገድ ለማስቀጠል ከተማ ትቶ ከአርሶ አደሩ ጋር ደፋ ቀና ሲል በአሰቃቂ ሁኔታ በፖሊስ ስለተገደለው ወጣት የግብርና ባለሙያ፣ ትኩረት ሰጥቶ ለቤተሰቦቹና ለነዋሪናዎች ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡ 

የዛሬው የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ፎቶና የሚያሰሟቸው መፈክሮች በጥቂቱ !!!


በአሁኑ ሰዓት ሰማያዊ ፓርቲ ከሶሰት ወር በፊት የጠራውን ሰልፍ እያካሄደ ይገኛል:: ሰልፉ በደማቅ ሁኔታ ተጀምሮ ነበር የሰልፉ መድረሻ መሰቀል አደባባይ ቢሆንም ሕዝቡ አራት ኪሎ አካባቢ ሲደርስ የአዲስ አበባ ፓሊሶች ሰልፈኛውን ወደ መሰቀል አደባባይ እንዳይሄድ ሲያግዱ የፌድራል ፓሊስ ደግሞ በርቀት እየተመለከተ ነው::ሰልፈኞቹ ወደ ስማያዊ ፓርቲ ቢሮ እንዲመለስ ተደርጓል ሕዝቡ ግን ድምጹን ከማሰማት ወደኋላ አላለም

ርዮት ትፈታ !! ውብሽት ይፈታ !! እሰክንድር ይፈታ !! አንዷለም ይፈታ !!! አቡበከር ይፈታ !!! ፍትህን መጠየቅ አሽባሪነት አይደለም !! ነፃነት እንፈልጋለን !! እኛ አሽባሪ አይደልንም!! ፍትሕ እንፈልጋለን !!! የሙሰሊም ኮሚቴ ይፈቱ !!! ዜጎችን ማፈናቀል አግባብ አይደለም !!! አንለያይም !!! አንለያይም !! ፍትህን ያሉ ቃልቲ ገቡ!! አሽባሪ አይደለንም !! ፍትህ ናፈቀኝ !! ድምፃችን ይሰማ!! ፍትሕ እያሉ ቃልቲ ገቡ !! ውሽት ሰለቸን !! ፍትህ ናፈቀን !!



Saturday, September 21, 2013

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ዋነኛ ጠላት ወያኔ ብቻ ነው!!

የግንቦት 7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በቅርቡ ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ዋነኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊና ዘላቂ ጥቅም ጠላት ወያኔ መሆኑን አስረግጦ ተናግሮ ነበር። ይህንን አባባል አንድ ተቃዋሚ ለተቃውሞ ያህል ወይም ስርዓቱን የሚጠላ አንድ ግለሰብ ስርአቱን ስለሚጠላዉ ብቻ እንደተናገረው አድርጎ አቃልሎ ማየት ትልቅ ስህተት ነው። ወያኔ ከፍጥረቱ ጀምሮ እስከአሁኑ ቅጽበት ድረስ በሀገራችን ላይ የፈጸመውን ደባ በቅጡ ያላዩ ሰዎች ይህ አባባል የተጋነነ ይመስላቸው ይሆናል። ኢትዮጵያ ዛሬም አንደ አገር የቆመችዉ በህዝቦቿ ታላቅነትና እንዲሁም ለታሪካቸው ባሳዩት ክብርና ብርታት ነዉ እንጂ እንደወያኔማ ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ ህልውና አደጋ ላይ ከወደቀ ሰንብቷል።

ኢትዮጵያ የሚለውን ውብና ታሪካዊ የስም ለመጥራት እየተጸየፈ “የሀገራችን ህዝቦች” እያለ ሲጠራን የነበረው የወያኔዉ ሹም የንቀት አጣራር ወያኔዎች ከሀገሪቱ ስም ጋር ሳይቀር የገቡበትን ጠብ ያሳያል። ወያኔ አባቶቻችን ባቆዩልን ዳር ድንደር የሚደራር ብቻ ሳይሆን የአገራችንን መሬት ላብዕዳን እንካችሁ ያለ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ነዉ። በወያኔ እንደባሪያ ፈንግሎ የሚገዛት አገራችን ኢትዮጵያን የታሪክ አጋጣሚ እጁ ላይ ጥሎለት ነዉ እንጂ እሱ እንደሚነግረን ወያኔ ከራሱና ከጉጅሌዎቹ ጥቅም አስበልጦ ኢትዮጵያን አስቧት አያውቅም።

መገነጣጠል ግብ እንዲሆን በህገ መንግስት ደረጃ አንቀጽ ጽፎ ያስቀመጠው ወያኔ እሱ እንደሚለዉ ለብሔረሰቦች መብት አስቦ ሳይሆን ኢትዮጵያ አልዘረፍ ካለችን በትነናት ብንሄድስ ከሚል አላማ መሆኑን ሌናጤን ይገባል። ከምር ለብሄረሰቦች መብት በመቆርቆር ቢሆን ኖሮ ከጠመንጃና ከፍጅት በፊት የብሄረሰቦችን መብትና ነጻነት አክብሮ እራሳቸዉን በራሳቸዉ እንዲያስተዳድሩ ይተዋቸዉ ነበር።።

ወያኔ ኢትዮጵያን የሚፈልጋት ለርሱና ለጋሻ ጃግሬዎቹ የወርቅ እንቁላል የምትጥል ዶሮ ሆና ስላገኛት ብቻ ነው። ሀገሪቱን እያለማሁ፣ እያሳደግኩ ነው የሚለው ዲስኩር ለተራ መደለያ እንኳን የማይሆን ውሸት ለተራበው ህዝብ ምኑም እንዳልሆነ ያውቀዋል።

የሀገሪቱን ለም መሬት በሄክታር ባንድ ፓኮ ሲጋራ ዋጋ የሚቸረችረው ወያኔ እነዚህ ባእዳን በጎን የሚሰጡትን የሀገራችንን መሬት ዋጋ ኪሱ መክተቱን አረጋግጦ ነው። ዛሬ በመላ ሀገሪቱ የሚነዛው የኬሚካል ማዳበሪያ በጥቂት አመታት ውስጥ የሀገሪቱን አፈር ድራሽ እንደሚያጠፋ ወያኔ የአዋቂዎች ምክር ሳይሰማ ስለቀረ አይደለም። በአጥፊ ስራው የቀጠለው መዝረፍ የሚችለዉን ንብረት ካጋበሰና ከዘረፈ በኋላ ነገ ኢትዮጵያ እንደአለ ባድማ ብትሆን ቅንጣት ስለማይሰማዉ ነዉ። ለሀገር የሚያስብ መንግስት ቢሆን ኖሮ የአገሪቱ ወጣትና የተማረ የሰዉ ኃይል እንደ ጎርፍ ከአገሪቱ እየጎረፈ ሲወጣ ይቆረቆር ነበር። ወያኔ የተማረ ሰው ቢሰደድ፣ ዜጎች ቢራቡና በገዛ አገራቸዉ ቢዋረዱ ጉዳዩ አይደለም። በሰላማዊና ህገመንግስታዊ መንገድ ጥያቄ ያነሳን ዜጋ ሁሉ እንደአውሬ የሚቀጠቅጠውና ወህኒ ቤት የሚያጉረው ይህ በደል ነገ በሀገሪቱ ዘላቂ ህልውና ላይ የሚያመጣውን መዘዝ አጥቶት አይደለም። የአገራችን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ጉዳዩ ስላልሆነ እንጂ።

የኢትዮጵያን ብሄር ቤሄረሰቦች የሚያይዟቸውን በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአንድነት ክሮች እያንቋሸሸና እንደሌሉ እየሰበከ በሚለያዩንን ጥቃቅን ውጭያዊ የቋንቋና የዘር ግንዶች አጉልቶ የሚያሳየን አገራችንንና ህዝቧን እንደ አንድ ሀገር ሳይሆን እንደጊዚያዊ የዝርፊያ ቀጠና ስለሚመለከት ብቻ ነው።

ወያኔና ሎሌዎቹ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ጠላቶቹ ናቸው እያሉ አንዴ የፈረሰችዉ ሶማሊያን፤ ሌላ ጊዜ ወደ ኤርትራና ግብጽ ጣቱን የሚጠነቁሉት አይናችንን ከወያኔ ላይ እንድናነሳ ነዉ እንጂ ከወያኔ በላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ጠላት የለም። ወያኔ በአካል እኛን ከሚመስሉ ኢትዮጵያውያን መሃል ይውጣ እንጂ፣ በተግባር ከቀን ጅብ ያልተናነሰ የዘረኞችና የዘራፊዎች ቡድን ነው። ብዙ ጊዜ ወያኔ ራሱ የጻፈውን ህግ ሲጥስ ለምን ብለን የምንገረም አለን። ወያኔ ሕግና ሕገ-መንግስት፣ ለአገራቸዉ የሚቆረቆሩ ምሁራንን የሚያፈሩ የትምህርት ተቋማት፣ በህዝብ የሚታመን ሰራዊት፣ ለህግ ብቻ የሚሰራ ፍርድቤትና የመሳሰሉት ዘላቂ ተቋማት እንዳይኖሩን የሚያደርገውና ያሉትንም የሚያፈርሰው ለኢትዮጵያ ብሄራዊና ዘላቂ ጥቅም ምንም ደንታ ስለሌለዉ ነዉመሆኑን የሚዘነጋ ኢትዮጵያዊ በእጅጉ የዋህ ነው። ወያኔ የኢትዮጵያ ጠላት ነው።

ስለዚህም እንላለን እኛ የግንቦት 7 ልጆችህ ሀገርህ ትውልድ ተሻግራ እንድትቀጥል አንተም የምትኮራባት ዜጋ እንድትሆናት የምትሻ የኢትዮጵያ ልጅ ሁሉ ሀገርህን ከወያኔ የቀን ጅቦችና ወራሪዎች አድን። አጎንብሰህ ሳይሆን ቀና ብለህ የምትሄድባት ሀገር እንድትኖርህ የምትሻ ሁሉ ለማይቀረው የጀመርነውን የአርበኝነትና የነጻነት ትግል ጉዞ ተቀላቀለን። እኛ የተባበርን እለት አብረን የተነሳንና በቃ ያልን እለት ታሪካዊቷ ሀገራችንና ታላቁ ሕዝባችን ዘላቂ ብሄራዊ ጥቅማቸው ይከበራል።

አዎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ዋነኛ ጠላት ወያኔ ብቻ ነው!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Tuesday, September 17, 2013

ርዕዮትና እስክንድር የአውሮፓ ህብረት በሚያዘጋጀው “ሻካሮቭ የነጻነት ሽልማት” የ2013 ተሸላሚ ለመሆን ከሰባቱ እጩዎች ውስጥ ገቡ፡፡

ርዕዮትና እስክንድር የአውሮፓ ህብረት በሚጋጀው  “ሻካሮቭ የነጻነት ሽልማት” የ2013 ተሸላሚ ለመሆን ከሰባቱ እጩዎች ውስጥ ገቡ፡፡ ከ15 ቀን በኋላ መስከረም 20 ለመጨረሻ ውድድር ሚቀሩት 3 እጩዎች የሚታወቁ ሲሆን መስከረም 30 በሚደረገው የአውሮፓ ህብረ
ት ፓርላማ ስብሰባ የአመቱ ተሸላሚ እንደሚለይ ከህብ
ረቱ መግለጫ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ህዳር 11 ቀን በምስራቅ ፈረንሳይ በምትገኘው ስትራስበርግ ከተማ የሽልማት ስነስርዓቱ ይከናወናል፡፡
መልካም ዕድል ለርዕዮትና ለእስክንድር!
ሙሉ መግለጫው የሚከተለው ነው።


2013 Sakharov Prize for Freedom of Thought – seven nominations
The 2013 Sakharov Prize nominees, presented at a joint meeting of the Foreign Affairs and Development committees and the Human Rights Subcommittee on Monday, are: Malala Yousafzai (Pakistan), Edward Snowden (USA), Reeyot Alemu and Eskinder Nega (Ethiopia), Ales Bialatski, Eduard Lobau and Mykola Statkevich (Belarus), Mikhail Khodorkovsky (Russia), the "Standing Man" protesters (Turkey), and the CNN Freedom Project: Ending Modern - Day Slavery (USA).

Malala Yousafzai - nominated jointly by 3 political groups:

• for the EPP group, by José Ignacio Salafranca (ES), Elmar Brok (AT), Michael Gahler (DE), Arnaud Danjean (FR), Joseph Daul (FR), Gay Mitchell (IE) and Mairead Mc Guinness (IE),

• for the S&D group, by Hannes Swoboda (DE) and Véronique de Keyser (BE),

• for the ALDE Group, by Guy Verhofstadt (BE), Sir Graham Watson (UK), and Annemie Neyts-Uyttebroeck (BE),

and also by Jean Lambert (Greens, UK) and the ECR group.


Ms Yousafzai was 11 years old when she began her fight for the right to female education, freedom and self-determination in Pakistan's Swat Valley, where the Taliban regime bans girls from attending school, by writing a blog under a pseudonym in 2009. She quickly became a prominent voice against such abuses, and Taliban gunmen tried to assassinate here in October 2012. She has since become symbol of the fight for women's rights and worldwide access to education.


Edward Snowden - nominated by the Greens/EFA group and GUE/NGL group

A computer expert who worked as a contractor for the US National Security Agency and leaked details of its mass surveillance programmes to the press, Mr Snowden has been charged with espionage in the USA and is now living in temporary asylum in Russia.

በሐሮ ወንጪ ቅ/ገብርኤል አንድነት ገዳም ላይ የቦምብ ጥቃት ተፈጸመ


  • መነኰሳቱ ገዳሙን ለቀው እንዲወጡ ዛቻና ማስፈራሪያ እየተደረገባቸው ነው
  • አስተዳደሩ ለመነኰሳቱ ተደጋጋሚ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት አልፈቀደም
  • ‹‹ከዚህ ቦታ ባትመጡ ይሻል ነበር፤ ብትውሉ አታድሩም!›› /ጥቃት ፈጻሚዎቹ/

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀ/ስብከት ወንጪ ወረዳ ሐሮ ወንጪ ቀበሌ በሚገኘው የሐሮ ወንጪ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳም ላይ የቦምብ ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመው ጳጉሜ ፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ምሽት 5፡00 ላይ ወደ ገዳሙ ቅጽር በተወረወረው ቦምብ ነው፡፡


በገዳሙ የኪዳነ ምሕረት፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱስ ዑራኤልና ቅድስት አርሴማ ታቦታት መኖራቸውን የገለጹት የገዳሙ አበምኔት መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ገብረ እግዚአብሔር ኣብርሃ፣ የተወረወረው ቦምብ በገዳሙ ቅጽር ውስጥ ቢፈነዳም በመነኰሳቱ ላይ ያደረሰው ጉዳት አለመኖሩን ለዜና ሰዎች ተናግረዋል – ‹‹ቢፈነዳም እርሱ ከልሎናልና ጉዳት አላደረሰብንም፡፡››

የአንድነት ገዳሙ አስተዳደር በቁጥር 17/2005 በቀን ፭/፲፫/፳፻፭ ለሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ፣ ለወንጪ ወረዳ መስተዳደርና ፖሊስ ጽ/ቤት በጻፈው የድረሱልን ጥሪ÷ ከዚህ ቀደም የገዳሙን ይዞታ በመጋፋት፣ መነኰሳቱና መናንያኑ ገዳሙን ለቀው እንዲሄዱ ተደጋጋሚ ዛቻና ስድብ በማሰማት የሚታወቁ 18 ግለሰቦችን በስም ለይቶ በመዘርዘር በጥቃቱ አድራሽነት እንደሚጠረጥራቸውና በቁጥጥር ሥር ውለው ሕጋዊ ርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቋል፡፡ በስም ከተዘረዘሩት 18 ግለሰቦች መካከል ጌቱ ታደሰ እና መኰንን ካሳ የተባሉ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች የኾኑ የቀበሌው ነዋሪዎች በዋና አስተባባሪነት ተጠቅሰዋል፡፡



ደብዳቤው ‹‹ፀረ ሃይማኖት የኾኑ ግለሰቦች›› ሲል የገለጻቸውና በቡድን የሚንቀሳቀሱት እኒህ አካላት፣ በገዳሙ ላይ ከዘጠኝ ጊዜ በላይ የተለያዩ ጥቃቶችን በገዳሙና በገዳማውያኑ ላይ በማድረስ ንብረት ማውደማቸውንና መነኰሳቱን ማሳደዳቸውን ጠቅሷል፡፡ ‹‹ለቀበሌው ብዙ ጊዜ አመልክተናል፤ ከአቅሜ በላይ ነው በማለቱ መፍትሔ ሳናገኝ እስከ አሁን አለን›› በማለት ከግለሰቦቹ ጥቃት ባሻገር አስተዳደራዊ በደልም እየተፈጸመ እንደሚገኝ ደብዳቤው አጋልጧል፡፡

የወረዳውና ቀበሌው ባለሥልጣናት በተገኙበት ነሐሴ ፳፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ከነዋሪው ጋራ በተደረገ ውይይት ሕዝቡ በቡድን እየተንቀሳቀሱ በገዳሙ ላይ ጥቃት የሚያደርሱ ግለሰቦችን የጠቆመ ቢኾንም ተገቢው ርምጃ ባለመወሰዱ÷ ግለሰቦቹ ገዳሙ በሚገለገልበት የውኃ ታንከርና የሶላር ቴክኖሎጂ ላይ ባደረሱት ጉዳት ሲስተሙ ለብልሽት ተደርጓል፤ መነኰሳቱ በሱባኤ ላይ ባሉበት ቀን ለቀን ወደ ገዳሙ ክልል ገብተው በይዞታው ላይ ችግኝ ከመትከል፣ የገዳሙ መውጫና መግቢያ በኾነ ቦታ ላይ አጥር ከማጠር አልተከለከሉም፤ ገዳማውያኑንም ‹‹ከዚህ ቦታ ባትመጡ ይሻል ነበር፤ ለዛሬ ብቻ ነው የምትኖሩት፤ ብትውሉ አታድሩም›› እያሉ በስልክና በአካል በተደጋጋሚ ዛቻና ስድብ ከማስፈራራት አልታቀቡም፡፡

‹‹በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በየዕለቱ ጨለማን ተገን በማድረግ የሚሰነዘርብን ጥቃት በዘመናዊ የጦር መሣርያ ጭምር የታገዘና በቀጣይም እየተጠናከረ እንደሚሄድ ያሳያል›› ያለው የገዳሙ አስተዳደር÷ ነሐሴ ፲፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ከሌሊቱ 7፡40 ዘመናዊ የጦር መሣርያ ታጥቀው ወደ መናንያኑ መኖርያ የመጡት ግለሰቦቹ በመናንያኑ መኖርያዎች ላይ የድንጋይ ውርጅበኝ ማዝነባቸውን፣ ጥይት መተኰሳቸውን፣ ገዳሙን በጥበቃ እንዲያገለግሉ የተቀጠሩ የአካባቢው ተወላጆች ሥራቸውን እንዲተዉ ያልተሳካ ሙከራ ማድረጋቸውን አስታውሷል፡፡

ገዳሙ ይዞታውን በሕግ ያረጋገጠበት ደብተር እንዳለው የጠቀሰው አስተዳደሩ የሹራብ ሽመና፣ የዶርና እንስሳት ርባታን ጨምሮ ራሱን የሚያግዝበት የልማት ጅምሮችና ዕቅዶች ቢኖሩትም ፍትሕ እያጡ በሚሰደዱት መነኰሳት ምክንያት ጥረቱ እየተሰናከለ ነው፤ በገዳሙ ምሥረታ ከነበሩት 15 መነኰሳት መካከልም ጸንተው የቀሩት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው፡፡

ወረዳው በተለይ ከ፳፻፬ ዓ.ም ጀምሮ ከገዳሙ ለሚቀርቡለት አቤቱታዎች ሁልጊዜ ተስፋ ይሰጠናል እንጂ የተጨበጠ ነገር አላስገኘልንም፤ ትኩረትም አይሰጡትም ያለው አስተዳደሩ÷ ‹‹መንግሥት ለሃይማኖታችንና ለገዳማችን ልማት የማይተኙልንን ፀረ ሃይማኖት የኾኑ ግለሰቦች›› በአስቸኳይ በቁጥጥር ሥር እንዲያውልና ሕጋዊ ርምጃ እንዲወስድባቸው ጠይቋል፡፡

የሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት ጥቃቱ በተፈጸመባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ መረጃው እንዲደርሰው ሲደረግ የቆየ በመኾኑ ‹‹ማመልከቻ አስገቡ›› ከሚለው ቸልተኝነቱ ተላቆ ገዳማውያኑ አስፈላጊውን ሕጋዊና አስተዳደራዊ እገዛ እንዲያገኙ ፈጥኖ መንቀሳቀስ ይኖርበታል፡፡

የሐሮ ወንጪ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳም መቋቋም በ፲፱፻፺፪ ዓ.ም መልአከ ሰላም አባ ገብረ ማርያም ኣብርሃ በተባሉ መነኮስ የተጀመረ ሲኾን የተገደመው ደግሞ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ሀ/ስብከቱን (ደቡብ ምዕራብ ሸዋን) ከምዕራብ ሸዋ ሀ/ስብከት ጋራ ደርበው በሚያስተዳድሩበት በ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. እንደኾነ የገዳሙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Monday, September 16, 2013

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ! ሰልፉ በታቀደለት ጊዜ ይካሄዳል!!!


የመስከረም 12 ሰልፍ በታቀደለት ጊዜ ይካሔዳል!!!!!

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ሰማያዊ ፓርቲ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ሊያካሂደው የነበረው የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፍ በመንግስት ታጣቂዎች ህገ ወጥ እርምጃ ከተደናቀፈ በኋላ ነሐሴ 3ዐ ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ፓርቲው መስከረም 12 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ሰላማዊ ሠልፍ እንደሚያደርግ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የሰላማዊ ሠልፍና ስብሰባ ማሣወቂያ ክፍል እንዲያውቀዉ አድርጓል፡፡ ይህንን ተከትሎ የሰላማዊ ሠልፍና ስብሰባ ማሣወቂያ ክፍል ጳጉሜ 1 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ የሰለፉን ዓላማ፣ የሰልፉ ተሳታፊዎች የሚጓዙበትን መስመርና የሰልፉ መዳረሻ ከግንባታ ስራና ከፀጥታ ጥበቃ ጋር ያለውን ችግር አስመልክቶ ማብራሪያ እንደሚያስፈልግ በጠየቀዉ መሠረት፡-

1ኛ. የሰልፉ ዓላማ፤
በህገ መንግሥቱ የተደነገጉት ሃሣብን በነፃነት የመግለፅ መብት እንዲከበር፣ዜጐች በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተዘዋውሮ የመሥራትና ሀብት የማፍራት መብታቸው እንዲከበር፣ በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 11፡3 በግልፅ የተደነገገው መንግሥት በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ኃይማኖትም በመንግሥት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም የሚለው ድንጋጌ እንዲከበር፣ መንግሥት የኑሮ ውድነትና ሥራ አጥነትን ለመቅረፍ የፖሊሲ ማሻሻያ እንዲያደርግ የሚሉትን ጥያቄዎች በሰላማዊ ሠልፍ መንግሥትን ለመጠየቅ መሆኑን፤

2ኛ. የሰልፉ ተሳታፊዎች የሚጓዙበትን መስመር
መነሻው ከፓርቲው ጽ/ቤት ግንፍሌ አካባቢ ተነስቶ በአራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል በኩል በአሮጌው ቄራ በአምባሳደር ቴአትር አልፎ መስቀል አደባባይ ሲሆን፣ በዚህ መንገድ ላይ ምንም ዓይነት የግንባታ ሥራ የሌለበትና ሠልፉ የሚደረገውም እሁድ ከጥዋቱ 3፡ዐዐ-7፡00 ሰዓት ባለው የእረፍት ቀን በመሆኑ በዕለቱ ምንም ዓይነት የመንግሥት ሥራና የትራፊክ መጨናነቅ የሌለበትና መድረሻ ቦታችንም መስቀል አደባባይ ከቅርብ ቀናት በፊት በኃይማኖት ተቋማት አስተባባሪነት ሠልፍ የተደረገበት መሆኑና ወደፊትም መስከረም 12 ቀን ከሚደረገው ሠልፍ አንድ ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከሁሉም ማዕዘናት በሚመጡ ምዕመናን የመስቀል በዓል የሚከበርበት ቦታ መሆኑን ጳጉሜ 04 ቀን 2005 ዓ.ም በፃፍነው ደብዳቤ አብራርተናል፡፡
የሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ሥነ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 3/1987 አንቀፅ 6 ቁጥር 2 “የከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት በዚህ አዋጁ አንቀፅ 6 ንዑስ አንቀፅ 1 የተመለከቱትን በማገናዘብ ሰላማዊ ሰልፉ በሌላ ጊዜ ወይም በሌላ ስፍራ ቢደረግ ይሻላል የሚል አስተያት ካለው ምክንያቱን በመግለፅ ይህንኑ ጥያቄው በደረሰው በ12 ሰዓት ውስጥ በጽሑፍ ለአዘጋጁ የማሳወቅ ኃላፊነት አለበት፡፡ ሆኖም የከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት ሰላማዊ ሰልፉ ምንጊዜም በየትኛውም ቦታ ሊካሔድ አይችልም ማለት አይችልም” በሚለው መሰረት የእዉቅና ጥያቄ የቀረበለት አካል በፅሁፍ በ12 ሰዓት ውስጥ መልስ የመስጠት ግዴታ ቢኖርበትም እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡

ፓርቲያችን በሕግ የሚጠበቅበትን ለሚመለከተዉ አካል የማሳወቅ ግዴታ በአግባቡ ስለተወጣና ለሰልፉም የሚያስፈልጉ ስራዎች እየተከናወኑ በመሆኑ መስከረም 12 ቀን 2006 ዓ.ም በታቀደው መሰረት ያካሂዳል፡፡ በመሆኑም በዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ የምናነሳቸው ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሲቪክ ማሕበራትና ዜጎች በአጠቃላይ በሰልፉ ላይ በመሳተፍ የዜግነት ድርሻቸውን እንዲወጡ ፓርቲያችን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

በመጨረሻም ሰላማዊ ሰልፉን በመቆጣጠርና የሕዝብን ሰላምና ፀጥታ የሚያውክን ሁኔታ በማስወገድ የሰላማዊ ሰልፈኞች መብቶችን ለመጠበቅ የፖሊስና የፀጥታ ኃይሎች በአዋጁ ቁጥር 3/1987 የተሰጣቸውን ኃላፊነትና ተግባር በአግባቡ እንዲያከናውኑ እናሳስባለን፡፡

መስከረም 6 ቀን 2006 ዓ.ም. 

አዲስ አበባ




አንድነት ፓርቲ ሰላማዊ ሠልፍና ቅስቀሳ የሚከለክል ደንብ በድብቅ ወጥቷል አለ

‹‹በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም የምንለው ነገር የለም›› የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሕገ መንግሥቱና በምርጫ አዋጅ የተፈቀደን ሰላማዊ ሠልፍና ቅስቀሳን የሚከለክል ደንብ በድብቅ በማፅደቅና በማውጣት፣ ከነሐሴ 10 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ ማድረጉን አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) አስታወቀ፡፡

አንድነት ፓርቲ አስተዳደሩ አዲስ ደንብ አውጥቶ በሥራ ላይ ማዋሉን አረጋግጫለሁ ያለው፣ ‹‹የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት›› በሚል መሪ ቃል ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሠልፍ ቅስቀሳ ሲያደርግ አባላቶቹ ‹‹ፈቃድ የላችሁም›› እየተባሉ ስለሚታሰሩበት፣ ‹‹ለምን ይታሰራሉ?›› በማለት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ሲጠይቅ መሆኑን የፓርቲው ዋና ጸሐፊ አቶ አስራት ጣሴ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የፓርቲው አመራሮች የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኃላፊዎችን ሲያነጋግሯቸው፣ አስተዳደሩ ነሐሴ 10 ቀን 2005 ዓ.ም. በሸኝ ደብዳቤ የላከላቸው በግምት 15 ገጽ የሚሆን ደንብ ቅስቀሳ ለማድረግና የተለያዩ ወረቀቶች ለመበተን ፈቃድ እንደሚያስፈልግ ስለሚገልጽ፣ ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅትም ሆነ ሌላ አካል ይኼንን ለማድረግ ሲነሳ ፈቃድ መያዝ እንዳለበት እንዳስረዷቸው አቶ አስራት ተናግረዋል፡፡

በምርጫ አዋጅ ሕግ 573/2000 አንቀጽ 46 ላይ እንደተደነገገው፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሕዝቡን የፖለቲካ ግንዛቤ ማዳበር፣ የፓርቲውን የፖለቲካ ዓላማ ለሕዝቡ ማስረዳት፣ ዜጐች በአገሪቱ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማንቀሳቀስ የዕለት ተዕለት ሥራዎች እንጂ፣ ፈቃድ የሚፈልጉ አለመሆናቸውን አቶ አስራት ጠቁመዋል፡፡ እነዚህን ሥራዎች የሚያከናውኑት ደግሞ በበራሪ ወረቀት፣ በመኪና ላይ ቅስቀሳና አዳራሽ ውስጥ ስብሰባ መሆኑን አክለዋል፡፡

‹‹እየታሰርንና የቅስቀሳ መሣሪያዎቻችንን ስንቀማ የከረምነው በማናውቀው ደንብ ኖሯል?›› ያሉት አቶ አስራት፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በካቢኔ ፀድቆ በመውጣት ተግባራዊ ተደርጓል የተባለውን ደንብ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ ስላልሰጣቸው ወደ አስተዳደሩ ማምራታቸውን አውስተዋል፡፡

ወደ ከተማ አስተዳደሩ ሄደው ከንቲባ ድሪባ ኩማን ለማግኘት ያደረጉት ጥረት ባይሳካላቸውም፣ በቅርቡ ከአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ሥራ አስኪያጅነታቸው ተነስተው የከንቲባው ጽሕፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ሆነው የተሾሙትን አቶ አሰግድ ጌታቸውን አግኝተው ማነጋገራቸውን አቶ አስራት አስረድተዋል፡፡ 

ደንቡ በካቢኔ ፀድቆ በሥራ ላይ መዋሉን፣ ለሕትመት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በመላኩ ሊሰጧቸው እንደማይችሉ አቶ አሰግድ እንዳረጋገጡላቸው የተናገሩት አቶ አስራት፣ በሕገ መንግሥቱና በምርጫ ሕግ የተሰጠን መብት በምን ዓይነት የሕግ ትርጉም ሊከለከል እንደተቻለ ባይገባቸውም፣ የአስተዳደሩ አካሄድ ግን ትክክል አለመሆኑን አስረድተዋል፡፡   

በአዲስ አበባ ከተማ መስከረም 5 ቀን 2006 ዓ.ም. ሰላማዊ ሠልፍ ለማድረግ ለአስተዳደሩ በደብዳቤ በማሳወቃቸው በዚህና በቅርቡ ወጥቷል ስለተባለው አዲስ ደንብ ከንቲባውን ለማነጋገር ቢመላለሱም ነገ ከነገ ወዲያ እየተባለ ሊያገኟቸው እንዳልቻሉም አቶ አስራት ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን ከአራት ወር በላይ ሲዘጋጁበት የነበረን ሰላማዊ ሠልፍ መስከረም 5 ቀን ፓርቲያቸው እንደሚያካሂድ ለአቶ አሰግድ ሲገልጹላቸው፣ ሰላማዊ ሠልፉን ከመስቀል በኋላ  እንዲያደርጉት እንደጠየቋቸው ጠቁመዋል፡፡ በሕገ መንግሥቱ በተፈቀደው መሠረት ፓርቲያቸው ካሳወቀ ከ48 ሰዓታት በኋላ ሰላማዊ ሠልፍ ማድረግ እንደሚችል የገለጹት አቶ አስራት፣ መስከረም 5 ቀን 2006 ዓ.ም. ሠልፉ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

አስተዳደሩ ያወጣው ደንብ ይከለክላል ከተባለ በሕዝቡ ላይ ችግር ቢፈጠር ኃላፊነቱ ማን እንደሚወስድ ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት አቶ አስራት፣ ሰላማዊ ሠልፍ በሚወጡ ዜጐችና ቅስቀሳ በሚያደርጉት ላይ ለሚከሰቱ ጉዳቶች ኃላፊነቱን የሚወስዱት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና መንግሥት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎችን ቦታ ባይሰጣቸውም ሕዝብ ለማገልገል በሕዝብ ተመርጫለሁ የሚል አስተዳደር አዲስ ደንብ ሲያወጣ ሕዝቡ እንዲጠነቀቅ ወይም የተፈቀደለትን መብት እንዲለማመድ ለምን ይፋ አይደረግለትም? በማለት የሚጠይቁት አቶ አስራት፣ ሰላማዊ ሠልፉን ፓርቲያቸው በሕገ መንግሥቱና በሕጉ መሠረት እንደሚያካሂድ አስታውቀዋል፡፡

‹‹እኛ እያሳሰበን ያለው የሰላማዊ ሠልፉ ጉዳይ ሳይሆን በሕግና በሥርዓት መመራታችን ነው፡፡ አገርን ያህል ትልቅ ነገር ይዘው እንደዚህ ነው የሚሠሩት? ይኼ አደጋ ነው፤›› ያሉት አቶ አስራት፣ ሕገ መንግሥቱን የማስከበር ተልዕኮ ያለው ፖሊስ በሕገወጥ መመርያ አባሎቻቸውን ከማሰርና ከማዋከብ እንዲቆጠብ ጠይቀዋል፡፡ አንድነት ፓርቲ መስከረም 5 ቀን 2006 ዓ.ም. ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሠልፍ የፀጥታ ማስከበር ኃላፊነቱን እንዲወጣም አሳስበዋል፡፡ 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በድብቅ አፅድቆ በተግባር ላይ እንዲውል አድርጐታል ስለተባለው ደንብ ማብራሪያ እንዲሰጡን የአስተዳደሩን የኮሙዩኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች አነጋግረናቸው፣ ‹‹በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም የምንለው ነገር የለም፤›› ከማለት ውጭ ዝርዝር ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ 

ምንጭ፡ ሪፖርተር ጋዜጣ

Sunday, September 15, 2013

“አዲሱ ቴሌ” እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ)፡ የህወሃት ኢህአዴግ የስለላ መረብ

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ከሚያካሂዳቸው በርካታ ተግባራት በተጨማሪ ላለፉት ወራት የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ያካሄደውንና ሊያካሂድ ያሰበውን የስለላ ተግባር ሲመረምር ቆይቷል፡፡ በተለይም ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም አዲሱ ቴሌን (ኢትዮ ቴሌኮምን) ከዋንኛው የስለላ መ/ቤት ብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል NISS (National Intelligence and Security Service) እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ወይም በእንግሊዝኛው (Information Network Security Agency (INSA) - ኢንሳ ጋር በማጋባት ስለላውን በምን ዓይነት መልኩ ለማካሄድ እንዳሰበ የሚያትት ባለ 47 ገጽ ግርድፍ ዘገባ አቅርበናል፡፡

“አዲሱ ቴሌ” እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ)፡ የህወሃት/ኢህአዴግ የስለላ መረብበሚል ርዕስ የቀረበው ይህ መረጃ በኢትዮጵያችን የተካሄደውንና በመካሄድ ላይ ያለውን የአፈና መዋቅር በጥቂቱ የሚያወሳ ነው። ዘገባው የህወሃት/ኢህአዴግ የደኅንነትና የአፈና ተቋማት ከቴሌኮም አገልግሎት ጋር እንዴትና ለምን እንደተቆራኙ፣ የምዕራብ አገራት የቴሌኮም ቴክኖሎጂ የተገፋበትን ምስጢር፣ አዲሱን ቴሌ ከአገር ወዳዶች በማጽዳት የህወሃት/ኢህአዴግን ፖለቲካና ስውር አጀንዳ ማስፈጸም ይችላሉ ተብለው ለታመነባቸው ክፍሎች ወይም የአገዛዙ “ቁሶች” እንዲዛወር የተደረገበትን ምክንያት፣ በፖለቲካ ድርጅቶችንና ኃላፊዎች እንዲሁም መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች (መያዶች) ላይ የሚካሄደውን ስለላ በመጠኑ ለማሳየት ጥረት ተደርጓል፡፡

በመጨረሻም ይህንን የስለላ መረብ በመጣስ ሕዝባችን ትግሉን በምን ዓይነት መልኩ ማከናወን እንዳለበትና እንዴት የመረጃ ጫካ ውስጥ በመግባት መደበቅ እንደሚቻል የተወሰኑ ሃሳቦችን ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡


ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ
SMNE Media & Public Relations
media@solidaritymovement.org
http://www.solidaritymovement.org

Saturday, September 14, 2013

ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ እሁድ ሴፕቴምበር 22 ቀን 2013 በዋሽንግተን ዲሲ / ቨርጂኒያ

ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ እሁድ ሴፕቴምበር 22 ቀን 2013 በዋሽንግተን ዲሲ / ቨርጂኒያ

እሁድ ሴፕቴምበር 22 ቀን 2013 በዋሽንግተን ዲሲ/ ቨርጂኒያ የግንቦት 7 ንቅናቄ አመራር የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሚገኙበት በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ከሕብረተሰቡ ጋር ውይይት ለማድረግ ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ ተዘጋጅቷል..

ቀን : እሁድ ሴፕቴምበር 22 2013


ሰአት: 2.00 pm – 6:00 pm


ቦታ : ሸራተን ናሽናል ሆቴል (ከዳማ ምግብ ቤት አጠገብ የሚገነው) 900 South Orme Street, Arlington, VA


መግቢያ: $20


ለተጨማሪ መረጃ: 571-239-7001



የግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ

Thursday, September 12, 2013

በኮንዶሚኒየም ቤቶች ሺያጭ ሥም ስደተኛውን የወያኔ ጭሰኛ ለማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ ይከሽፋል::

ወያኔ እንደ ድርጅት የሚፈልገውን የፖለቲካ ጥቅም የሚያስገኝለት እስከመሰለው ድረስ በህዝብና በአገር ላይ የማይፈጽማቸው ምንም አይነት እኩይ ተግባሮች እንደማይኖሩ በተግባር ያስመሰከረ ድርጅት ነው::

ለአብነት ያህል ለመጥቀስ ፤

1. ድርጅቱ ገና ትግራይ በረሃ ውስጥ ትግል ላይ በነበረበት ወቅት የትግራይን ወጣቶች ከትምህርት ገበታቸው እ
ያነቀ በመውሰድ አላማውን በግልጽ ላልተረዱትና ላላመኑበት ጦርነት ማግዶአቸዋል:: በዚህም የተነሳ ወያኔ እራሱ ይፋ ባደረገው አሃዝ ብቻ ቁጥራቸው 60 ሺህ የሆኑ ለጋ ወጣቶች ላለፉት 22 አመታት የህዝባችንን ስቃይና መከራ እያራዘመ ያለውን የድርጅቱን መሪዎች ሥልጣን ላይ አውጥቶ ለማንገስ ከፍተኛ የህይወት መስዋዕትነት ከፍለዋል ::

2. የአገራችንን ክብርና መልካም ገጽታ እስከዛሬ አበላሽቶ ባለፈው በዚያ አስከፊ የ1977ቱ ድርቅ ወቅት ለትግራይ ተጎጂዎች ከአለም አቀፍ ለጋሾች የተበረከተውን የነፍስ አድን እህል በሱዳን በኩል ወደውጭ አሳልፎ በመቸብቸብ መሪዎቹና ተከታዮቻቸው ለተንደላቀቀ ኑሮ ሲበቁ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ህጻናት፤ አሮጊቶችና አዛውንቶች እንደቅጠል እንዲረግፉ ምክንያት ሆኖአል::

3. የትግራይ ህዝብ ተማሮ በመንግሥት ላይ እንዲያምጽ ለመቀስቀስ በደሃው አቅማችን የተገነቡ ትምህርት ቤቶችን፤ የህክምን አገልግሎት መስጫ ተቋሞችን ፤ ድልድዮችንና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን በፈንጂና በመድፍ ከማውደም አልፎ የተሳሳተ መረጃ ለደርግ በመስጠት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ህዝብ ለገበያ እንደወጣ ሃውዜን ከተማ ላይ በጠራራ ጸሃይ እንዲጨፈጨፍ አድርጎአል::

4. የደርግ አገዛዝ ከተወገደ ቦኋላ ሥልጣን ላይ ለመደላደል የሚያስችል ድጋፍ ለመሸመት ሲባል የአገራችንን ሉአላዊ ጥቅም ለባዕድ አሳልፎ የሰጠ በርካታ ግልጽና ድብቅ ውሎችን ከ3ኛ አካላት ጋር ፈጽሞአል :: ከውሎቹ አንዱ የህዝባችንን ትኩረት ለማስለወጥ ካለፈው 2 አመት ጀምሮ በሰፊው እየተዘመረለት የሚገኘው የአባይ ወንዝን የመጠቀም መብታችንን የሚጻረር እንደነበረ ጉልህ ማስረጃ አለ::

5. በሚሊዮን የሚጠጋ ህዝባችንን ከቀያቸው በማፈናቀል ለም መሬታችንንና ድንግል የተፈጥሮ ሃብታችንን ለህንድ ፡ ለቻይናና ለአረብ ከበርቴዎች በመቸብቸብ በገዛ አገራችን የባዕድ አሽከር እንዲንሆን ፈርዶብናል::

6. በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሴት እህቶቻችን ለባርነት ሥራ ወደ አረብ አገር በመላክ ከፍተኛ ሰቆቃ እንድፈጸምባቸው በማድረግ ብሄራዊ ክብራችንን ኩራታችንን የሚያጎድፍ ተግባር ፈጽሞአል::

7. በሙስናና ዘረፋ የተጨማለቀ ሥርዓት በማቋቋም አብዛኛው ህዝባችን ከወለል በታች ወደወረደ የድህነት አረንቋ ውስጥ ገብቶ የቁም ስቃይ እንዲቀበል አድርጎአል::

8. መብታቸውን ለማስከበር በጠየቁ ወገኖቻችን ላይ እስከ አፍንጫው የታጠቀ ጦር በማዝመት በርካቶችን አስጨፍጭፎአል፤ ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎአል ፤ ለእስርና ለስደት ዳርጎአቸዋል:: ወዘተ

ወያኔ ይህንንና ግዝፈታቸው ከዚህ የከበዱ በርካታ ሰቆቃዎችን በአገርና በወገን ላይ እየፈጸመ የአገዛዝ ዘመኑን ሊያራዝም የቻለው፤

1. ህዝባችን በዘር ፤ በቋንቋና በሃይማኖት ተከፋፍሎ እርስ በርሱ እንዳይተማመንና የጎሪጥ እንድተያይ ሌት ተቀን ተንኮል በመሸረቡ;

2. የጦር ሃይል ፤ የፖሊስ ሠራዊት፤ የደህንነትና ሌሎች የኢኮኖሚና ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋሞች በሙሉ ከአንድ አካባቢ በተሰባሰቡ የጥቅም ተጋሪዎች ቁጥጥር ሥር እንዲወድቅ ተደርጎ እሺ ያለውን በጥቅም እምቢ ያለውን ደግሞ በጠመንጃ ሃይል ጸጥ ለጥ ለማድረግ በመመኮሩ፤

3. ከራሳቸው የግል ሚቾትና ቅንጦት አሻግረው በወገንና በአገር ላይ እየተፈጸመ ያለውን ሰቆቃ ማየት የማይፈልጉ ወይም የማይችሉ ተፈጥሮአዊ ባህሪያቸው “ እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል “ ካለቺው እንስሳ የማይለይ ሆዳሞች ከተለያየ የህበረሰተሰብ ክፍል ተመልምለው ከአገዛዙ ዙሪያ በሎሌነት ለመሰለፍ በመቻላቸው እንደሆነ ይታወቃል::

በሌላ አገላለጽ ወያኔ የአገዛዝ እድሜውን ለማራዘም የፈጸመውና እየፈጸመ ያለው ቀደም ሲል ፋሽስት ጣሊያን የአገራችንን ህዝብ በባርነት ለመግዛት አድርጋው ከነበረው ቅስም ሰባሪ እርምጃዎች በባህሪም ሆነ በአይነት አንድ መሆኑ ግልጽ ነው:: ለመብቱና ለነጻነቱ ቀናዕ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ትናንት ለጣሊያን መደለያዎች ተታሎ ወይም የሃይል እርምጃ ተንበርክኮ ነጻነቱን አስነጥቆ ለመኖር እንዳልፈቀደ ሁሉ ዛሬም ከአገሩ የሰሜን ክፍል የበቀሉ ባንዳዎች በጉልበታቸውም ሆነ ሌሎች መሸንገያዎች የሚያደርጉትን አሜን ብሎ እስከወዲያኛው ለመገዛት ፈቃደኛ አለመሆኑን በሚያደርገው ተቃውሞ እየገለጸ ነው::

ይህንን ሃቅ የተረዳው ወያኔ የጭቆና ክንዱን ለማፈርጠም የሚያስፈልገውን ገንዘብ በስደት ውጭ አገር ከሚኖረው ኢትዮጵያዊ ለመሰብሰብና የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ለማዳከም በኮንዶሚኒየም ቤት ሽያጭ ሥም አዲስ እቅድና ስልት ነድፍ መንቀሳቀስ ጀምሮአል::

ብቸኛው የፓርላማ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሠፉ በቅርቡ ከኢሳት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ እንዳረጋገጡት ወያኔ በስደት ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ የነደፈው የኮንዶሚኒየም ቤት ሺያጭ ዋና አላማ አገር ቤት ውስጥ እየተፏፏመ የመጣውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመምታት በተለያዩ የምዕራብ አገሮች ከፍ ብለው እየተደመጡ ያሉትን ድምጾች አሰቀድሞ ለማዳከም በመፈለጉ እንደሆነ አያጠራጥርም::

ምንም እንኳን ለራሳቸው ማንነትና ስብእና ክብር የሌላቸው አንዳንድ ዜጎች “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” በሚል ፈሊጥ በዚህ የወያኔ ወጥመድ ውስጥ ለመውደቅ ውር ውር እያሉና በየአገሩ የሚገኘውን የወያኔ ኤምባሲ በር ማንኳኳት የጀመሩ መኖራቸው ባይካድም አንድ ወቅት ላይ ግር ግር ፈጥሮ ወዲያው እንደተጨናገፈው የአባይ ቦንድ ሺያጭ የታሰበውን ያህል ውጠት እንደማያስገኝ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል::

ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በስደት የሚኖረው ሁሉም ኢትዮጵያዊ አገሩንና ወገኖቹን ጠልቶ ሳይሆን የተሰደደው ለዘመናት የዘለቀው ኢፍትሃዊነት የፈጠረው ኋላ ቀርነትና ድህነት አገሩ ላይ ለመኖር ያለውን ምኞትና ተስፋ አጨልሞበት አለያም በፖለቲካ ችግር ምክንያት ህይወቱን ለማቆየት ተገዶ ነው ብሎ ያምናል::

በዚህም የተነሳ ማንኛውም ስደተኛ ስደት የሚያስከትለውን ማህበራዊና ሥነ ልቦናዊ ቀውሶች ተቋቁሞ አንድ ቀን አገሬ ገብቼ ከወገኖቼ ጋር በሠላም እኖርበታለሁ ብሎ ያጠራቀማትን ጥሪት በከፍተኛ ንቅዘትና ሙሰኝነት ወደ መጨረሻው ታሪካዊ ሞቱ እየወረደ ያለውን የወያኔ ሥርዓት ተማምኖ በማውጣት ቦኋላ እንዳይጸጸት ወገናዊ ምክሩን ይለግሳል::

ወያኔ ለዲያስፖራው ያዘጋጀው የኮንዶሚኒዬም ቤቶች ሺያጭ የፖለቲካ ድጋፍ ለማግኘት የታለም የከተማና የገጠር ህዝባችንን የወያኔ ጭሰኛ ያደረገ የአገር ውስጥ ፖሊሲ አካል ነው:: ከ7 አመት በፊት ኮንዶሚኒዬም ቤት ለማግኘት ለተመዘገቡ 800 ሺህ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ያልተዳረሰ ቤት እንዴትና በምን ስሌት ነው በሰው አገር ያውም በአንጻራዊ ምቾት ለምንኖር ዜጎች የታሰበልን ብሎ እራስን መጠየቅ ከትዝብትና ከታሪክ ተወቃሽነት የሚያድን ተግባር ነው ::

ሃብት በተትረፈረፈበትና የሚበላ የሚጠጣ ነገር ከሰው ተርፎ ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ በሚጣልበት አሜሪካና አውሮጳ ለምንኖር ዜጎች ከሚስኪኑ ህዝባችን ጉሮሮ በተነጥቀ ገንዘብ ቤተመንሥት ውስጥ ተዘጋጅቶ የተላከ ምግብና መጠጥ ለመደለያነት ሲያጓጉዝ የኖረ መንግሥት አሁን ደግሞ በኮንዶሚኒየም ቤት ሥም ቢመጣብን ጥፋቱ የሱ ሳይሆን የእኛ ለክብራችንና ለነጻነታችን ዋጋ የማንሰጥ ስግብግቦች መሆኑን ምን ጊዜም መዘንጋት የለበትም::

ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በስደት ውጭ አገር የሚኖር ማንኛውም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ወያኔ በኮንዶሚኒዬም ቤት ሽያጭ ሥም ትግሉን ለማዳከም የዘረጋውን ይህንን የተንኮል ሴራ እንዲያከሽፍ ወገናዊ ሃላፊነት እንዳለበት ያስገነዝባል::

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

Saturday, September 7, 2013

ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ የተከሰሰው በጋዜጠኝነት ስራው ነው! (ድምፃችን ይሰማ)

ቅዳሜ ጳጉሜ 2/2005

በማእከላዊ ቆይታው አሰቃቂ ጊዜ አሳልፏል!


በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ ክስ የተመሰረተበት ከጋዜጠኝት ስራው ጋር በተያያዘ ነው፡፡ የቀድሞ የሙስሊሞች ጉዳይ መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተርና አዘጋጅ የነበረው ሰለሞን ከበደ ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ ከቤቱ ወደ ስራ ቦታው ሲሄድ ታፍኖ ከተወሰደ በኋላ በማእከላዊ ለአራት ወራት ያህል አሰቃቂ ምርመራ ተደርጎበታል፡፡ በምርመራ ወቅት በቀን ከ12 ሰዓታት በላይ በተለያዩ ገራፊዎች ተፈራራቂነት ቶርች ሲደረግ ከመቆየቱም በላይ ለተደጋጋሚ ጊዜያትም ራሱን ይስት እንደነበር ታውቋል፡፡ ጋዜጠኛ ሰለሞን በምርመራው ወቅት በድብደባም ሆነ በሌላ መልኩ ሊያስጠይቀው የሚችል ምንም ወንጀል ባይገኝበትም ክስ ተመስርቶበት አሁን በቂሊንጦ ወህኒ ቤት ይገኛል፡፡ 


ጋዜጠኛ ሰለሞን ሰለሞን በእነ አማን አሰፋ የክስ መዝገብ የተከሰሰ ሲሆን የክሱ ጭብጥም ‹‹የከተማ ጂሀድና መላውን ሙስሊም ያካተተ ጂሀድ ማቀጣጠል›› የሚል አሳፋሪ ውንጀላ ነው፡፡ በመንግስት ክስ ከተማ ጂሀድና የትጥቅ ትግል በመምራት፣ በማደራጀትና በማቀጣጠል የተከሰሰው ሰለሞን በዚህ ውንጀላ መነሻነትም የማእከላዊ ገራፊዎች ሰለሞንን ደጋግመው ‹‹የጦር መሳሪያዎችን የት ነው የደቅከው?››
ሲሉ ይገርፉት ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ‹‹ለወታደሮች ስልጠና ትሰጣለህም›› ተብሎ የማእከላዊ ገራፊዎች እረፍት የማይሰጥ አሰቃቂ ቶርች ፈጽመውበታል፡፡ ከአራት ወራት አሰቃቂ አስር በኋላም በሰኔ 2005 ክስ ተመስርቶበታል፡፡ 

ሰለሞን ከበደ ላይ መንግስት ክሱን ከመሰረተ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ክሱን ከልሶ ያቀረበ ሲሆን በዚሁ በተከለሰው ክስ ላይም ሰለሞን የተከሰሰው በጋዜጠኝት ስራው መሆኑን ተመልክቷል፡፡ ክሱ ‹‹… ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ከሽብር ቡድኑ አባላት ጋር በመገናኘትና በአወሊያና በየመስጂዶቹ የተጀመረው አመጽ እንዴት መቀጠል እንዳለበት በመወያየት ለአመጽ የሚያነሳሱ ጽሁፎችን በየወሩ በመጽሄት በተለያዩ ርእሶች ሲያወጣ ቆይቶ በመጨረሻም ይህንኑ በማሰባሰብ ‹‹የኢትዮጵያ ሙስሊም የት ጋር ነው?›› በሚል ርእስ አመጽ ቀስቃሽ ጽሆፎችን በማሰባሰብ መጽሀፍ በማሳተምና በማሰራጨት…›› በሚል በግልጽ በሙስሊሞች ጉዳይ መፅሄት ላይ ይሰራ በነበራቸው የጋዜጠኝነት ስራዎች መከሰሱ አውን ሆኗል፡፡ 

መንግስት ደጋግሞ ‹‹ጋዜጠኞች በሙያቸው በሰሩት ስራ አልተከሰሱም አይከሰሱም›› ሲል የቆየ ቢሆንም ሰለሞን ከበደ በዚሁ የጋዜጠኝነት ስራው ተከሷል፡፡ የመፅሄቱ ዋና አዘጋጅ የነበረው ዩሱፍ ጌታቸው በተመሳሳይ መልኩ በመፅሄቱና በቢ.ቢ.ኤን ሬዲዮ ላይ ያቀርባቸው በነበሩ ዘገባዎች ምክንያት ክስ ተመስርቶበት ከሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ዳኢዎችና ኡለማዎች ጋር ከ14 ወራት በላይ በእስር ላይ ይገኛል፡፡ የጋዜጠኛ መብት ተሟጋች የሆኑ አለም አቀፍ ድርጅቶች ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸውና ሰለሞን ከበደ ከእስር እንዲለቀቁ ተደጋጋሚ ጥሪ ለመንግስት አቅርበዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ ጋዜጠኞችን በማሰር መጥፎ ስም ማትረፏ የሚታወቅ ሲሆን በአፍሪካም ከኤርትራ ቀጥሎ ብዙ ጋዜጠኞችን ያሰረች አገር እንደሆነች አለም አቀፍ ሪፖርቶች ያመላክታሉ፡፡ 

አላሁ አክበር!

Friday, September 6, 2013

A prisoner of conscience's call for sanctions against Ethiopia

European aid has transformed my country's economy but also props up one-party rule. Let EU donors give us democracy.


To Ethiopia's archaic left, which dominates the ruling party, the new euphemism for the west is neoliberal. Compared to the jargon of bygones days – imperialists – when Lenin and Mao were still in vogue, neoliberal sounds decidedly wimpy. But this hardly matters to Ethiopia's ruling party. What it seeks is a bogeyman to tamp down rising expectations for multiparty democracy.

To this end, plying nationalist sentiment is the easy option. And so, we get a tale of heroes and villains in which there is a defender of national ethos, honor and economic growth (inevitably, the ruling party), and a foreign horde bent on subversion, domination and economic exploitation (infallibly, the west: the neoliberals).

In this narrative, Ethiopia's recent economic growth, amidst a global slump, is ascribed to the stability afforded by one-party rule, as in China – and not, as many experts are prone to point out, the generosity of donor countries. Hence the paradox of well-intentioned European money promoting Chinese interests in one of the more important economies in Africa.

Aggregate aid is to the Ethiopian economy what Obama's fiscal stimulus was to the American economy: minus these injections, both economics would suffer catastrophically. The theatrical blustering of the Ethiopian government notwithstanding, donor countries have a make-or-break power over the Ethiopa's prosperity.

ከኢሕአፓ የእርምት እንቅስቃሴ የተሰጠ መግለጫ !

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)

ኢሕአፓ አንድና አንድ ብቻ ነው

የኢሕአፓ ሕገ ፓርቲና መተዳደሪያ ደንብ በውልደቱ ከድርጅቱ ልደት ጋር ነበር አብሮ የተፈጠረው። አባላት በእነዚህ ሰነዶች የውዴታ ግዴታ ራሳቸውን ሲያስገዙ ኖረዋል። አባል ለመሆንም ይሁን ከአባልነት ለመወገድ ሰነዶቹ ለድርጅቱ አንድም እንደ መመዘኛ ሁለትም እንደ መዳኛ ህግጋት ሲያገለግሉ ኖረዋል። ስለሆነም አባላት በሰነዶቹ ላይ ብዥታ ኖሯቸው አያውቅም። ብዥታው ከድሮም ከአመራሩ እንጂ ከአባላት አልነበረም። ዳሩ የሰሞኑ አደናጋሪ መግለጫ ግን “መበደል መበደል ወታደር በድሏል ግን ባላገር ይካስ” እንዲሉ ይመስላል። አባላትን ህግ የተላለፉ ለማስመሰል ተሞክሯል። ሰነዶቹ ውይይትን፤ ሂስና ግለሂስን፤ ብሎም መተራረምን የሚያበረታቱ ሲሆኑ ቅጣትን እንደ መጨረሻ አማራጭ አድርገው ይወስዳሉ። ይህንን በሚመለከት በፍኖተ ሕብረት የኢሕአፓ ሬዲዮ ነሐሴ vw አሁድ በተሰጠው ቃለ መጠይቅ ሁለት የድርጅቱ ከፍተኛ አመራር ጓዶች አትኩሮት ሰጥተው አስረድተዋል። ሕግና ደንብን በሚመለከት ሁለቱ አመራሮች በሰጡት ቃለ መጠይቅ ውስጥ ገብተን ለመተቸት አንሞክርም። ዳሩ በአሁኑ ወቅት የተፈጠሩት ችግሮች ግን ከሰነዶቹ አፈጻፀም ጋር በእጅጉ የተቆራኙ መሆናቸውን አስረግጠን ማለፍ እንወዳለን።

የኢሕአፓን ሕገ ፓርቲ አና ውስጠ ደንብ መጣስ የተጀመረው ዛሬ በየቦታው እንደሚናፈሰው በእርማት እንቅስቀሴው አባላት ሳይሆን የድርጅቱ ከፍተኛ አመራር አባላት በነበሩት በአቶ ኢያሱና በአቶ ፋሲካ ነበር። ጠቅለል ባለ መልኩ ይህን ይመስላል፦

፩ኛ. የድርጅቱን መዋቅር በመከተል ድርጅቱን በሚመለከት ገንቢ የሆነ ሕጋዊ ጥያቄ ያቀረቡትን ቻፕተሮች ማፈን። በደርጅቱ ጉባኤ አካሄድ ላይ ያልተስማሙትን አንጋፋ አባላት፣ ለጥያቄያቸው መልስ ከመንፈግ አልፎ ከድርጅቱ ማግለል። መብታቸውን ነፍጎ ግን ግዴታቸውን እንዲወጡ ማስገደድ፣

፪ኛ. የድርጅቱ አባለት በማያውቁት ሁኔታ የድርጅቱ አቋም በማስመሰል መግለጫዎችን በመስጠት ህግ መጣስ፣

፫ኛ. እጅግ ጸያፍ የሆኑ ስነ ምግባሮችን ጨምሮ የዲሲፕሊን ጉድለቶችን በጽሕፈት ቤቱ ውስጥ መፈጸም፣

፬ኛ. አባለትን ወያኔያዊ በሆነ መንገድ መከፋፈል። በድርጅቱ ውስጥ የበኩርና የእንጀራ ልጅ መፍጠር። በጎጥና በዘር መከፋፋል፣ ከሌሎች የሕግና የደንብ ጥሰቶች በተጨማሪ ይህም ሙሉ በሙሉ ጸረ ኢሕአፓ አካሄድ ስለሆነ ግለሰቦቹ ኢሕአፓን አንደማይወክሉ ለማስታወቅ ተገደናል::

፭ኛ. የድርጅቱን ደንብ በሚጻረር መልኩ ድርጀቱን የሚጎዳ ጽሁፍ፣ ቃለ መጠይቅ፣ ወዘተ. በተደጋጋሚ ማድረግ፣

፮ኛ . ሂስና ግለሂስን ወደ ጎን ገፍቶ አሉባልታን በድርጅቱ ውስጥ ማስፋፋት፣

፯ኛ . የድርጅቱን ምስጢር አደባባይ ማውጣት፣

፰ኛ. የወጣቱን ክንፍ ለመበተን ተከታታይነት ያላቸው የከፉ አርምጃዎችን መውሰድ፣

የጋራ ንቅናቄው ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን ይቆማል!

የወጣት አመራሮቹን ሰላማዊ የትግል መስመር ይደግፋል!


ያለፈው እሁድ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጠርቶ በነበረው የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ላይ በህወሃት/ኢህአዴግ የተወሰደውን ጽንፈኛ፣ አክራሪና አጸያፊ የውንብድና ተግባር የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ይኮንናል፤ ያወግዛል፡፡ ፓርቲው ሰልፉን ለማካሄድ ከሁለት ወራት በፊት ፈቃድ ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም ቅዳሜ ነሐሴ 25፤2013 የፌዴራል ፖሊስና የደኅንነት አባላት የፓርቲውን ጽ/ቤት ጥሰው በመግባት የፈጸሙት ተራ የውብንድና ተግባር ብቻ ሳይሆን የህወሃት/ኢህዴግን ማንነት በግልጽ ያሳየ ለመሆኑ ከማንም በላይ ተግባሩ ራሱ ምስክር ነው፡፡


በዕለቱ እንደሆነው የህወሃት/ኢህአዴግ አሸባሪ ፖሊሶች የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤትን ከመውረራቸው በፊት ኤሌክትሪክ መስመሩን ቆርጠዋል፡፡ በቀጣዩም ለእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ዝግጅት እያደረጉ የነበሩትን አመራሮችና ፈቃደኛ ሠራተኞችን ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ ከደበደቡና ካሰቃዩ በኋላ ለሰዓታት አስረዋቸዋል፡፡ ወጣቶቹ ከተፈቱ በኋላ ለእሁዱ ስብሰባ ተመልሰው ዝግጅት እንዳያደርጉ የህወሃት/ኢህአዴግ አሸባሪዎች የፓርቲዉን ጽ/ቤት እስከ እሁድ ድረስ በመቆጣጠር ኮምፒውተሮችን፣ የጽህፈት መሣሪያዎችን፣ ሠንደቅዓላማዎችን፣ መፈክሮችን፣ … በማውደም፤ የሚፈልጉት በመውሰድ ሰልፉ እንዳይካሄድ አድርገዋል፡፡ ይህንን ተግባር የሚመሰክር ከበቂ በላይ የፎቶግራፍ፣ የሰው፣ … ማስረጃ ቢኖርም ህወሃት/ኢህአዴግ ሁሉንም በመካድ ለዓለምአቀፍ ሚዲያ አንዳች ነገር እንዳልተደረገ በመናገር የተለመደውን ዓይን ያወጣ ቅጥፈት ደግሟል፡፡

ጥያቄው ግን ሰላማዊ ሰልፍ እናድርግ ያሉ ቁርጠኛ ወጣቶች ያነሱት ይህ የመብት ጥያቄ ለምን ህወሃት/ኢህአዴግን ለምን አሸበረው? ለምንስ እንዲህ ያለውን ራሱን የሚያጋልጥ ተግባር እንዲፈጽም አደረገው? መልሱ ህወሃት/ኢህአዴግ ልምድ በሌለውና በማያውቅበት የሰላማዊ ትግል ጠንክረው ስለመጡበት ብቻ ነው! ለዚህ ደግሞ ለሁለት ዓመታት ያህል በጽናት መብታቸውን ለማስከበር የሚታገሉት ሙስሊም ወገኖቻችንና ሰሞኑን በአንድነት ፓርቲ የተጀመረው ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች ማስረጃዎች ናቸው፡፡

ህወሃት/ኢህዴግ ባስቀመጠው ትዕዛዝ መሠረት የሰማያዊ ፓርቲ ለእሁዱ ሰልፍ ከሁለት ወር በፊት ደብዳቤ አስገብቶ ፈቃድ ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም ባለፈው ሰሞን ህወሃት/ኢህአዴግ ባቀናበረው የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ “አሸባሪነትንና አክራሪነትን” ለማውገዝ ሕዝቡ ሰልፍ እንዲወጣ ጥሪ አድርጎ ነበር፡፡ በጥሪ ብቻ ያላበቃው ዘመቻ የከተማው ነዋሪ በግድ፣ በማስፈራራት፣ በጉቦ፣ … ሰልፍ እንዲወጣ የተቀናበረም ነበር፡፡ ይህ ሰልፍ በሚካሄድበት ቀን ታቅዶ የነበረው የሰማያዊ ፓርቲ ትዕይንተሕዝብ ካልተጨናገፈ በስተቀር ህወሃት/ኢህአዴግ በጠራው በራሱ ሰልፍ ላይ የሚደርስበት ክስረት መራራ እንደሚሆን ግልጽ ነበር፡፡

ከሰልፉ ጥሪ በፊት በተካሄደው ጉባዔ ወቅት “በኢትዮጵያ ህዳሴ የሃይማኖቶች ተስማምቶ መኖር” አስፈላጊነት የተሰበከ ሲሆን ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ በወቅቱ “የሃይማኖት አክራሪነትን” እንዲያጋልጡ ተሰብሳቢዎቹን በመጠየቅ መንግሥት በዚህ ዙሪያ የሚወስደውን እርምጃ አንደሚቀጥልበት አስጠንቅቀው ነበር፡፡ ቅዳሜ በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት የተፈጸመው ተግባር አሸባሪና አክራሪ ራሱ ህወሃት/ኢህአዴግ መሆኑን ያጋለጠበት ነው፡፡

የሃይማኖት ተቋማት ጉዳይ ያገባኛል በማለት ጉባዔ የሚጠራው ህወሃት/ኢህአዴግ፤ “በሃይማኖታችን ጣልቃ አትግባ፤ የራሳችንን መሪዎች እንምረጥ፣ መብታችን ይከበር” በማለት ላለፉት ሁለት ዓመታት ያህል እየጮሁ ያሉትን ሙስሊም ወገኖቻችን የመብት ጥያቄ መመለስ ያልፈለገ ወይም ያልቻለ ነው፡፡ ከዚህ ይልቅ ግን የራሱን ካድሬዎች በሃይማኖት መሪነት ሽፋን በመሾምና ሙስሊሙን ኅብረተሰብ በመከፋፈል የአፈናና የመብት ረገጣ ተግባሩን ቀጥሎበታል፡፡ ይህ የህወሃት/ኢህአዴግ አሠራር በሌሎች ሃይማኖቶችም የቀጠለ ለመሆኑ በሃይማኖት ተቋማት ስም የተጠራው ጉባዔና ሰልፍ በቂ ምስክር ነው፡፡

ህወሃት ገና ከጥንስሱ የሃይማኖት ጉዳይ የማይስበው፤ በበረሃው ቆይታ በተደጋጋሚ በአሸባሪነት ተግባር ላይ ለመሠማራቱ የተመሰከረለት መሆኑ፤ ራሱን በፈጣሪ የለሽ የሌኒኒስታዊ ፍልስፍና ያጠመቀ መሆኑ ራሱ የመሰከረውና በግልጽ የሚታወቅ ሆኖ ሳለ አሁን “በኢትዮጵያ የሃይማኖት ጉዳይ ያገባኛል፤ የሃይማኖት አክራሪነትን እታገላለሁ” ማለቱ ጅብ በማያውቁት አገር ሄዶ የአህያ ቁርበት አንጥፉልኝ ያለው ዓይነት ነው፡፡

በአመሠራረቱ የተለያዩ ኢትዮጵያውያንን የሚወክለው ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በኢትዮጵያ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ ካሉት “የድምጻችን ይሰማ” ሙስሊም ወገኖች፣ የአንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምጽ፣ የሰማያዊ ፓርቲና ሌሎች ወገኖች ጋር ያለውን ኅብረት ይገልጻል፡፡ የጋራ ንቅናቄው ባለው ዓለምአቀፋዊ ዕውቅናና ግንኙነት በመጠቀምም የህወሃት/ኢህአዴግን ቋት ለሚሞሉት ለለጋሽ አገራት፣ ለሕግ ተቋማት፣ ለሰብዓዊ መብት ድርጅቶች፣ ለሚዲያ ተቋማት፣ ወዘተ በአገራችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን የመብት ረገጣ ያሳውቃል፡፡ የህወሃት/ኢህአዴግን አገዛዝ እስካሁን የፈጸመውን የሽብር ተግባርና ወደፊት ለሚያደርሰው ማንኛውም በደል በቀጥታ ተጠያቂ እንዲሆን መረጃው በሕግ ተመዝግቦ እንዲቀመጥ ያደርጋል፡፡

በአገራችን በ1997 የተደረገውን ምርጫ ተከትሎ በሟቹ ጠ/ሚ/ር ቀጥተኛ ትዕዛዝ ህወሃት/ኢህአዴግ የፈጸመው የ193 ዜጎች ግድያ፣ የፖለቲካ መሪዎች እስር፣ አፈና፣ የመብት ረገጣ፣ … ያስከተለውን ፍርሃት ለመጀመሪያ ጊዜ በመግፈፍ የፖለቲካ ትዕይንተሕዝብ ያደረገው የሰማያዊ ፓርቲ ነው፡፡ “ድምጻችን ይሰማ” የሚያደርጉት በትክክለኛ የሰላማዊ ትግል መርህ ላይ የተመሠረተው እልህ አስጨራሽና መስዋዕትነትን የሚጠይቅ ትግል እንዳለ ሆኖ የሚሊዮኖች ድምጽ እንቅስቃሴም ከዚህ ጋር አብሮ ተጠቃሽ ነው፡፡

አርቆአሳቢና ራሳቸውን በሰላማዊ ትግል ዲሲፒሊን ያነጹ ወጣቶች ተሰባስበው በሰማያዊ ፓርቲ ሥር የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሰላማዊ ትግል በትክክለኛው መንገድ ከተከናወነ በኢትዮጵያ እንደሚሠራ በተግባር ያስመሰከረ ነው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን “ሰላማዊ ትግል ከኢትዮጵያ የፖለቲካ አንጻር አይሠራም” የሚለውን ስሜታዊ አስተሳሰብ ከሥሩ የመታ ትግል በመሆኑ የጋራ ንቅናቄው ለሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችንና አመራሮች ከፍ ያለውን አድናቆት ይሰጣል፡፡ በተለይም በሰላማዊ ትግል መስመር ስማቸው በዓለም የሚጠራው መሃትማ ጋንዲ፣ ዶ/ር ኪንግ፣ ማንዴላ፣ … በወጣትነታቸው ይህንን ዓይነቱን የትግል መስመር ከመምረጣቸው አኳያ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች የተጠና እንቅስቃሴና የዓላማ ጽናት ሌሎችም የእናንተን መስመር እንዲከተሉ የሚያደፋፍር እንጂ በምንም ዓይነት መልኩ የያዛችሁትን እርግጠኛ አቋም እንድትመረምሩ ሊያደርጋችሁ እንደማይገባ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በአጽዕኖት ያስታውቃል፡፡ ለመስከረም 12፤ 2006 ዓ.ም. የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ሁሉም ሰላም ወዳድ ወገኖች ድጋፋቸውን እንዲሰጡት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም በስደተኛው ሲኖዶስና በማህበረ ቅዱሳን ያሉ ምእመናንን የግንቦት 7 ከበሮ መቺ አሏቸው

የፌደራል ጉዳዮች ሚ/ር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ከሰሞኑ መንግስት በአዲስ አበባ በጠራው ጽንፈኝነትን እና አክራሪነትን የሚኮንን ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር በስደተኛው ሲኖዶስና በማህበረ ቅዱሳን ውስጥ መሽገዋል ያሏቸውን ምእመናን የግንቦት 7 ከበሮ መቺ ሲሉ መናገራቸውን ሐራ ተዋሕዶ ዘገበ። ከዚህ ቀደም በሕይወት የሌሎት ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ማህበረ ቅዱሳንን አክራሪ ሲሉ በፓርላማ መናገራቸውን ያስታወሱ ምእመናን የሚ/ሩ ንግግር እንዳስቆጣቸው ለመረዳት ተችሏል። የሐራ ተዋሕዶ ዘገባ እንደወረደ ይኸው፦


‹‹በስደተኛው ሲኖዶስ የተሸፈኑና በማኅበረ ቅዱሳን የመሸጉ የትምክህት ኀይሎች የግንቦት ሰባትን ከበሮ ሲመቱ ከርመዋል››

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ባዘጋጁትና ከነሐሴ ፳፩ – ፳፫ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም በተካሄደው ‹‹አገር አቀፍ የሰላም እሴት ማጎልበቻ ጉባኤ›› ውይይት ከተካሄደባቸው ጽሑፎች መካከል የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም ‹‹የአክራሪነት/ጽንፈኝነት ዝንባሌዎችና መፍትሔዎቻቸው›› በሚል ርእስ ያቀረቡት ጽሑፍ ይገኝበታል፡፡

በሰባት ንኡሳን አርእስት ተከፋፍሎ በስፋት የቀረበው ጽሑፋቸው÷ አክራሪነትና ጽንፈኝነት ከሕገ መንግሥት አንጻር እንዴት እንደሚታይ፣ በአገራችን ይታያሉ ያሏቸውን የአክራሪነትና ጽንፈኝነት ዝንባሌዎች፣ አክራሪነትን/ጽንፈኝነትን የማስፋፊያ ስልቶችን፣ የአክራሪ/ጽንፈኛ ኃይሎች መነሻና መድረሻ ምስጢር፣ ሃይማኖትን ሽፋን ስላደረጉ የአክራሪነት አደጋዎች እና አክራሪነትን/ጽንፈኝነትን በአስተማማኝ ደረጃ ለማሸነፍ መሠራት ይገባቸዋል ያሏቸው ስድስት የመፍትሔ ሐሳቦች የተካተቱበት ነው፡፡

በሚኒስትሩ ጽሑፍ አክራሪነት/ጽንፈኝነት የሚለው ቃል የተበየነው በሦስት መንገዶች ነው፡፡ ይኸውም አክራሪነት/ጽንፈኝነት÷ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፳፯ ንኡስ አንቀጽ ፫ ዜጎች የፈለጉትን እምነት የመከተል መብት እንዳላቸው የተደነገገውን በመተላለፍ የሃይማኖትና እምነት ነጻነትን በተግባር ለመናድ መንቀሳቀስ ነው፡፡ የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፳፭ ስለ እኩልነት መብት በሚደነግጋቸው ንኡሳን አንቀጾች በሃይማኖቶች መካከል የማበላለጥ ጉዳይ እንደማይኖር የተቀመጠውን ድንጋጌ በመጣስ የሃይማኖት እኩልነትን በተግባር ለመናድ መንቀሳቀስ ነው፤ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፲፩ ስለ መንግሥትና ሃይማኖት መለያየት በግልጽ የተቀመጠውን ድንጋጌ በመፃረር መንግሥታዊ ሃይማኖት ወይም ሃይማኖታዊ መንግሥት ለመመሥረት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ነው፡፡

አክራሪው/ጽንፈኛው ኃይል ደረጃው ይለያይ እንጂ በሁሉም ሃይማኖቶች ሽፋን እንደሚንቀሳቀስ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ዓለም አቀፋዊና ከባቢያዊ ገጽታም ያለውና የሚመጋገብ እንደኾነ ያስረዳሉ፡፡ ስለዚህ እኔን የሚመለከተኝ አይደለም የሚል ሃይማኖትና አገር ይኖራል ተብሎ እንደማይታሰብ፣ እንደየአገሩ የሕዝቦች በሰላም አብሮ የመኖር ታሪክ፣ ከድህነትና ኋላቀርነት ተጋላጭነት የመላቀቅ፣ የሕገ መንግሥታዊ ሥርዐት የብዝሃነት አያያዝ ጥበቃ ዋስትና ሊለያይ እንደሚችል ይናገራሉ፡፡

በአገራችን በሁሉም ሃይማኖቶች (በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሽፋን፣ በእስልምና ሃይማኖት ሽፋንና በፕሮቴስታንት ሃይማኖት ሽፋን) የአክራሪነትና ጽንፈኝነት አስተሳሰብና ተግባር አራማጆች ከሃይማኖቱ መሪዎች ያልተላኩና መነሻቸውም መድረሻቸውም ሃይማኖታዊ ሳይኾን ፖሊቲካዊ መኾኑን ይጠቁማሉ፡፡

ከዚህ በታች ሚኒስትሩ ‹‹በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሽፋን›› ይታያል ለሚሉት ‹‹የአክራሪነት እና ጽንፈኝነት አስተሳሰብና ተግባር›› በማብራሪያነት የሰጡት ገለጻ ለሐራውያን ቀጥተኛ መረጃና ማገናዘቢያ ይኾን ዘንድ በጽሑፋቸው በሰፈረበት ይዘቱ ቀርቧል፡፡

* * *

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በንጉሡ ዘመን የመንግሥት ሃይማኖት እንደኾነች በ1948 ዓ.ም. ሕገ መንግሥት የተደነገገና እስከ ንጉሡ ሥርዐት መውደቅ ድረስ የቀጠለ እንደኾነ ይታወቃል፡፡ በዚያን ዘመን ንጉሡና የገዥ መደቡ አካላት ለሥልጣን ማራዘሚያ፣ የጥቅም ማካበቻና የሌሎች እምነት ተከታዮችን በማሸማቀቅ አንድ አገርና አንድ ሃይማኖት ፍልስፍና ለማራመድ ተጠቅመዋል፡፡

Thursday, September 5, 2013

ሰላማዊ ትግላችን ይቀጥላል (ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ)

ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፉ ወደ መስከረም 12 ቀን መተላለፉን አስታወቀ!!!


የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” የ3ወር መርሃ-ግብር በታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠናቀቃል! አንድነት ፓርቲ ጋዜጣዊ መግለጫ


አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

“የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” የ3ወር መርሃ-ግብር በታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠናቀቃል!

በአንድነትና በ33ቱ ፓርቲዎች በጋራ የተሠጠ ጋዜጣዊ መግለጫ


አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንቅስቃሴ የበለጠ ተጠናክሮ ህዝቡ የትግሉ መሪ ተዋናይና ባለቤትነት እንዲረጋገጥ ላለፉት ሶስት ወራት ፓርቲያችን ባስቀመጠው ስትራቴጂ እቅድ መሠረት ሰፊ ህዝባዊ ንቅናቄ ሲያደርግ ቆይቱዋል፡፡

በሃገራችን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ማለትም ፖለቲካዊ፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መረገጥ ፓርቲያችን “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል ሰኔ 13ቀን 2005 በይፋ ለጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄ ፖለቲካዊ ምክንያቶች ናቸው፡፡

ሕዝባዊ ንቅናቄው በእቅድ መመራት ከመጀመሩ በፊት ሀገራችን የምትገኝበትን ነባራዊ ሁኔታና የህዝባችን ተጨባጭ ኑሮ ላይ ጥናት በማድረግ የመፍትሄ አማራጮችን ማቅረቡ የፓርቲያችን አብይ ጥያቄ ሆኖ መገኘቱም የንቅናቄውን ወቅታዊነት ያገናዘበ አድርጎታል፡፡

በእቅዳችን መሰረት በመላው ሃገሪቱ ለመጀመሪያው ዙር በተመረጡ ቦታዎች ያደረግናቸው ህዝባዊ ስብሰባዎችና ሰላማዊ ሰልፎች በአባሎቻችን፤ በደጋፊዎቻችንና በህዝባችን ጠንካራ ትግልና መስዋእትነት ንቅናቄው የተሳካ ሲሆን ፓርቲያችን ለተከፈለው ዋጋ ሁሉ አድናቆቱን ይገልፃል፡፡

በገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በመታገዝ የፀጥታ ኃይሎች እንቅስቃሴዎቻችንን ለማጨናገፍ ከህግና ሥርዓት ውጪ ማስፈራራት፤ ማሸማቀቅ፤እስራትና ድብደባ በአባሎቻችን ላይ ሰብአዊነት በጎደለው ሁኔታ ተፈፅሞባቸዋል፡፡ የቅስቀሳ ቁሳቁስም በአካባቢ የፀጥታ ሰራተኞች ተዘርፈውብናል፡፡ እንዲሁም ህዝብ በነፃ አስተሳሰብ አማራጩን እንዳይከተል በአካባቢ ካድሬዎችና አመራሮች ማስፈራራትና ዛቻ ደርሶበታል፡፡ መርሃ ግብሩም ከተፈፀመ በኃላም ቢሆን ህዝባዊ ንቅናቄውን የተቀላቀሉ ዜጎቻችን በመኖሪያ ቀያቸው ሰርቶ የማደርና በነፃነት የመኖር መብታቸው አደጋ ላይ ነው፡፡

በተንቀሳቀስንባቸው አካባቢዎች ሁሉ ገዢው ፓርቲ ከህዝብ የተነጠለ መሆኑንና ህዝቡን እየመራሁ ነው የሚለው ህዘብን በማሸማቀቅ እንደሆነ መገንዘብ ችለናል፡፡ ከህግ ውጭ የገጠሙን መንግስታዊ ተፅእኖዎች ሁሉ ነፃነቱን በተነፈገውና በለውጥ ፈላጊው ህዘባችን ህዝባዊ እምቢተኝነት ተልኮአችን ሊሳካ ችልዋል፡፡

የሚሊዮኖችን ድምፅ ለማሰባሰብ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ያሉ ዜጎቻችን በንቃትና በቁጭት የተሳተፍበት በመሆኑ አመርቂ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ፊርማ የማሰባሰቡ መርሃ ግብር የሚቀጥል ይሆናል፡፡

የህዝባዊ ንቅናቄው የመጀመሪያው ዙር መርሃ ግብር በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ መስከረም 5ቀን 2006 በሚደረገው ታላቅ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ እስካሁን ካደረግናቸው ህዝባዊ ንቅናቄዎች ልዩ የሚያደርገው የ33ቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ይሁንታ ያገኘና ሰላማዊ ሰልፉን በባለድርሻነት የተሳተፉበት መሆኑ ነው፡፡

በአንፃሩ ገዢው ፓርቲ እስካሁን ካወጣቸው አፋኝ ህጎች በተጨማሪ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተጠናክሮ የመጣውን ህዝባዊ የፖለቲካ ተቃውሞ የበለጠ ለመደፍጠጥ አሳሪ ደንቦች ለማውጣት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተንቀሳ
ቀሰ ለመሆኑ ከገጠመን መልካም አስተዳደር እጦት መገንዘብ ችለናል፡፡

የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ ፓርቲዎች በጋራ በጠሩት በዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ የነፃነት ድምፁን እንዲያሰማ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

“የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት”

የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ ፓርቲዎች

ነሐሴ 30 ቀን 2005

አዲስ አበባ

Wednesday, September 4, 2013

አጭር ማስታወሻ የሰማያዊ ፖርቲ የተቃውሞ ሠልፍ…….

ነሀሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሰማያዊ ፓርቲ ታላቅ የተቃውሞ ሠልፍ መጥራቱ የሚታወቅ ነው፤ ይሁን እንጂ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እንደሰፈር ጉልበታኛ ዱንኳን ሰባሪ ዘው ብሎ በሃይማኖት ስበብ ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ቀንና ሰዓት እንዲሁም ቦታ በህግ አግባብ ሣይሆን በጉልበት ሠልፍ መሰል ሠልፍ ማካሄዱ የሚታወቅ ነው ፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም የተቃውሞ ሠልፍ በማድረግ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የተቃውሞ ሠልፈኞች እንዲሁም የአገር ውስጥና የውጪ የመገናኛ ብዙሃን በተገኙበት መንግስት ሊመልሳቸው የሚገባ ጥያቄዎችን የጠየቀ ሲሆን ለጥያቄዎቹም ምላሽ የሰጠው የጊዜ ገደብ ሦስት ወር መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

ይሁን እንጂ መንግስት በተሰጠው ጊዜ የተጠየቀውን ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ፓርቲውን በመወንጀል እና ስም የማጥፋት ዘመቻውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ሰማያዊ ፓርቲ መንግስት ላሣየው ቸልተኝነት እርማታ እንዲያደርግ በመግላጫ የጠየቀ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ ከ1 ወር በፊት በፓርቲው ጽ/ቤት በተሰጠ መግለጫ ነሀሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ፓርቲው ቀድሞ ለጠየቃቸው ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ በድጋሚ በተጠናከረ መልኩ የተቃውሞ ሠልፍ መጥራቱን ለመንግስትም ለህዝብም ተገልፃል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ በሠላማዊና በህጋዊ መንገድ የሚታጋል እንደመሆኑ መጠን ለአ/አ መስተዳደር በኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀፅ 30 ንዑሰ አንቀፅ 1 መሰረት በማድረግ ነሀሴ 13 ቀን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት የሰላማዊ ሰልፍ ስብሰባ ማሳወቂ ቢሮ ነሀሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም የተቃውሞ ሠልፍ አንደሚያካሂ ያሳወቀ ሲሆን፤ የከንቲባ ፅ/ቤት የሰላማዊ ሰልፍ ስብሰባ ማሳወቂ ቢሮ ነሀሴ 15 ቀን ለፓርቲው በላከው በአስቸኳይ የደብዳቤ መልዕክት ሦስት ጥያቄዎችን ለፓርቲው ሲጠይቅ ሰማያዊ ፓርቲ ነሀሴ 17 ቀን የተጠየቁትን ጥያቄ በመመለስ የማሰወቂያ ደብዳቤ አስገብቷል፡፡

ይሁን እንጂ የከንቲባ ፅ/ቤት የሰላማዊ ሰልፍ ስብሰባ ማሳወቂ ቢሮ ምንም ዓይነት ምላሽ አልሰጠም፤ይህ ደግሞ የማሳወቂያ ደብዳቤ ከገባ በ48 ሰዓት ውስጥ ምንም ዓይነት ምላሽ ካልተሰጠ የተጠራው የተቃውሞ ሠልፍ እውቅና እንዳለው ይቆጠራል ተብሎ በአዋጅ ተደንግጎ ይገኛል፡፡በዚህም መሰረት ሰማያዊ ፓርቲ በ48 ሰዓት ውስጥ ምንም ዓይነት ምላሽ ስላልደረሰው የህጉን ስርዓት ጠብቆ ለተቃውሞ ሠልፉ ዝግጅቱን አጠናክሮ በመቀጠል ላይ እንዳል ነሀሴ 20 ቀን የሀይማኖት ጉባሄ የተባለ በመንግስት ድጋፋ የሚንቀሳቀስ አካል ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ቀንና ሰዓት እንዲሁም ቦታ ሠልፍ መጥራቱ ታወቀ፡፡

ይህ ደግሞ ተገቢ አለመሆኑ ምን አልባትም ከመረጃ እጥረት ከሆነ ወይም ሌላ ምክንያትም ቢኖርም ሰማያዊ ፓርቲ የህግ አግባብ ተከትሎ ቀድሞ የያዘው ፕሮግራም መሆኑ እና ለተፈጠረው የፕሮግራም መደራረብ መንግስት በአስቸኳይ ማስተካኪያ እንዲያደርግ፤ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚፈጠሩ ማናቸውም ችግሮች መንግስት ሃላፊነቱን እንደሚወስድ ሰማያዊ ፓርቲ በሰጠው መግለጫ አሳስቧል፡፡

ይህ በእንዲ እንዳለ ነሀሴ 24 ቀን 2005 ዓ.ም የአዲስ አበባ ፖሊሲ ኮሚሺን ሦስት የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን የንወያይ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮችም ጥሪውን በማክበር በቦታው ተገኝተዋል፡፡‹‹የአ/አ አስተዳደር ፓርቲያቹ ለጠራው የተቃውሞ ሠልፍ እውቅና አልሰጠም በዚህም መሰራት ሰልፉን ማካሄድ አትችሉም›› በማለት ፖሊስ መስጠንቀቂያ የሰጠ ቢሆንም ፤ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ‹‹ ፖሊስ ይህን የማለት መብት የለውም፤ የአ/አ አስተዳደር ፓርቲያችን ላስገባው ደብዳቤ በ48 ሰዓት ውስጥ የሰጠው ምንም ዓይነት ምላሽ የለም ይህ ደግሞ የጠራነው የተቃውሞ ሠልፍ የህግ አግባብነት ያለው ነው፤በመሆኑም ምንም ዓይነት የህግ ስእተት ባለመፈጸማችን ሰልፉን እናካሂዳልን በዕለቱም ፖሊሲ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ አለበት››በማለት አሳባቸውን ገልፀዋል፡፡

ከሁሉም የአለም አቅጣጫዎች (አሜሪካንና አውሮፓን)ጨምሮ ብዙ ኢትዮጲያውያን ምሁራን መሳሪያ አንስተው ለመታገል ጫካ ገብተዋል :- አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ













ከሁሉም የዐለም አቅጣጫዎች (አሜሪካንና አውሮፓን)ጨምሮ ብዙ ኢትዮጲያውያን ምሁራን መሳሪያ አንስተው ለመታገል ጫካ ገብተዋል። ይህን ያሉት ለስራ ጉዳይ አሜሪካን ያሉት የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ዛሬ ከኢሳት ቲቪ ጋር ባረጉት ቃለ ምልልስ ነው ።  በትግሉ ጉዳት ለሚደርስባቸውም ለቤተሰብ ማቋቋሚያ ፈንድ ተቋቁሟል።በኤርትራ ኖረውና ተዘዋውረው ባዩት መሰረት ከፕሬዝዳንቱ እስከገበሬው ድረስ ከኢትዮጲያውያውያን ጋር በወንድማማችነት መኖር ይፈልጋሉ ብለዋል አቶ አንዳርጋቸው። ስለ አሰብ እና ስለ አሁን ስላለውም መከለከያ አመራር  በተመለከተም ተናግረዋል።


ምንጭ፡ debirhan.com


የእኛ ማርቲ ሉተር ኪንግ ከየት ይሆን?

ግርማ ሠይፉ ማሩ (የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር)

የቤተክርሰቲያናችን ሰባኪዎች ለመስቀል ጦርነት ተዘጋጁ የሚሉ ይመስላሉ፡፡ ይህ የመንግሰት ስራና አቅጣጫ ነው፡፡ በቤተክርስቲያን ሰብከቱ ሁሉ ማሳረጊያው ክርስቲያኖች በተለይ ወጣቶች ዓይማኖታችሁን ለመጠበቅ እሰከ ሞት ድረስ ዝግጅት እንዲያደርግ እየተሰበከ ነው፡፡ እንደ ምሳሌ እየተጠቀሰ ያለውም የግብፅ ሙስሊሞች ከጊዜ ብዛት እየበዙ ክርስቲያኖቹ ላይ ጫና እያደረጉ አሁን አናሳ ሆነው ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ እኛም ወደፊት እንዲህ ልንሆን እንችላለን የሚል ነው፡፡ በእኔ እምነት ይህ ሊሆን የሚችለው በሀገር ውስጥ ያለው የሀይማኖት አባት በየደረጃው፤ ዲያቆን፣ ወዘተ ሀገር ለቆ እየሄደ ህዝቡም በስደት ሀገር ለቆ ወጥቶ የሰው ሀገር ሀገሬ ያለ እንደሆነ እና በተቃራኒው ሙስሊሙ ሀገሬ ብሎ በሀገሩ ከቆየ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሰድት በዓይማኖት ይህን ዓይነት አወቃቀር ያመጣል የሚል ዕይታ የለኝም - ይህ ለጥናት ክፍት መሆን ይኖርበታል፡፡ አንድ ጥናት ግን ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ሀገራቸውን ለቀው ለመሄድ ያላቸው ፍላጎት እጅግ አደገኛ ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱንም ሰነ ህዝብ አወቃቀር (ዲሞግራፊ) እንደሚለውጠው ድምዳሜ ላይ ደርሶዋል፡፡ ይህን እያልኩ ያለሁት ኢትዮጵያዊ ሙስሊሞች ክርስቲያኑን ለማጥፋት ወይም ወደ አናሳ ለማውረድ እየሰሩ ነው የሚል ድምዳሜ ስለሌለኝ ስለማይገባኝ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ቅዥት ያላው አንድም ሰው ግን የለም ማለት አይደለም፡፡

በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ወደ መንበሩ ሲመጡ ቀላል የማይባሉ የፕሮቴስታን ክርስትና ተከታዮች በደስታ ጮቤ እንደረገጡ ትዝ ይለኛል፡፡ በአንዳንዶቹ የእምነት ተቋማትም የምስጋና ፕሮግራም እንደነበር ሰምተናል፡፡ ሙስሊሞች ኢትዮጵያ ውስጥ ሙስሊም ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲመጣ ቢመኙ መሻታቸውንም አይቶ ዓምላክ ቢሰጣቸው ክፋቱ አይታየኝም፡፡ በግሌ እኔም በእምነቱ ጠንካራ የሆነ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ መንበሩን ቢይዝ ጮቤ ባልረግጥ እንኳን ደስ እንደሚለኝ ይሰማኛል (የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦርቶዶክስ ነበሩ?)፡፡ ነገር ግን እነዚህ ቦታዎች የሚያዙበት መስመር ሰዎች ባላቸው የፖለቲካ አመራር እና ሌሎችን እምነቶች በእኩል ለማስተዳደር ባላቸው ብቃት እና የሁሉንም ይሁንታ ሲያገኝ ነው እንጂ በእምነት ተቋማቱ በኩል ተወክለው ሲመጡ አይደለም፡፡ ለምሳሌ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ሲሆኑ የፓርቲ ፕሮግራም ለማስፈፀም ካላቸው ቁርጠኝነት ብቻ ነው እንጂ ፕሮቴስታን መሆናቸውን ያሰበውም የለም፡፡ መሆን ያለበትም እንዲህ ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡ ሌላ ምሳሌ ልስጥ ባራክ ኦባማ ለአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሲሆኑ አብዛኛው ጥቁር ደስ ብሎታል በተለምዶ የሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊ የነበሩ አንድ አንዶችን ጨምሮ ኦባማ ግን የጥቁር ብቻ ሳይሆን የሁሉም አሜሪካ ፕሬዝዳንት ናቸው፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሙስሊም ጠቅላይ ሚኒስትር ለማየት ቢፈልጉ ክፋት የቱ ጋ እንደሆነ አይገባኝም፡፡ ይህን በጉልበት በተለይም ሌሎች ክርስቲያኖችን በማጥፋት እናድርገው እያሉ ከሆነ መረጃ ይሰጠን እና አብረን እንታገላቸው፡፡ ምክንያቱም ይህ የእልውና ጉዳይ ነው፡፡ እኔ እንደ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን እንደ ሰው መጥፋት አልፈልግም፡፡ ይህ ነገር ካለ በእውነት ኢትዮጵያ ውስጥ አክራሪነት አለ ብለን ልንስማማ እንችላለን መፍትሔም በጋራ መፈለግ አለብን ብዬ አምናለሁ፡፡ መሰመር ያለበት እብድ የለም እያለን እንዳልሆነ ነው፡፡

People left for abuse, a regime bankrolled to abuse




For Immediate Release

  September 4 2013

People left for abuse, a regime bankrolled to abuse

On Saturday August 31, 2013, the Ethiopian capital once again turned into a hell where heavily armed TPLF commando forces besieged the Blue Party headquarters, looted the entire office material, and assaulted young men and women who at the time were on their last minute preparation for a peaceful demonstration planned for the following day. According to eye witnesses, leaders, members and supporters of Blue party were handcuffed; frog marched and badly beaten by heavily armed Special Forces. The assault and humiliation on young female members of the party was even worse and strange to the Ethiopian culture that treats all women as mothers. Many female members of the party were taken to police stations and army barracks, ordered to take out their clothes, and forced to roll in stinking sewage sludge.

Just like the absolute majority of the over 90 million Ethiopians, the dream of young men and women of Blue party is to see the important values of justice, liberty, and democracy prevail in their country. The only weapons they carry are pen and paper, their sole goal is peace and prosperity, and their slogan is “Let our voices be heard”. However, last Saturday; the response from an excessively brutal regime that knows only violence was to use an overwhelming force to silence the voices of freedom. This past Saturday, as it usually does; the TPLF regime took the constitutional right of the people and by doing so; the brutal regime has once again demonstrated its utter intolerance to multi-party politics and any kind dissent in Ethiopia.

Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy denounces the savage and heartless acts of the TPLF regime in its strongest sense and holds the regime accountable for all of its actions. Ginbot 7 understands that no words can comfort those who endured last Saturday’s horrendous assault and humiliation at the Blue party headquarters. However, we at Ginbot 7 want the courageous Blue Party leaders and members to know that we are thinking of you and sharing your pain at this difficult time. Most importantly, we want to reassure you that regardless of what the brutal regime does, no one can close the opened gates of liberty, and we shall overcome.

After 22 years of brutal killing, complete neglect for human right, utter intolerance for dissent, ever shrinking democratic space and unprecedented corruption; Ethiopia is left completely shattered and is now a failed State. At this historic juncture, Ginbot 7 wants to ask donor nations and other enablers of Ethiopia’s brutal dictators a very important question: Are you for the Ethiopian people or against the Ethiopian people? Are you financing dictatorship or development?

At the meantime, Ginbot 7 makes a call for all democratic forces of Ethiopia inside and outside the country to set aside their minor differences and stand firm for a nation that has been bleeding for so long. The question of how to fight the TPLF regime has already been answered by the continued and unabated brutal actions of the regime. We as a nation have been pushed to the limit and there is no more space to be pushed. We either fight collectively and declare our freedom or perish collectively. The nation has called us, let us answer the call.

We shall overcome!

pr@ginbot7.org | +44 208 133 5670

ልማት ምንድነው? እውን የወያኔ መንግሥት ልማታዊ ነው?

በዶ/ር ታደሰ ብሩ

1. መግቢያ

“ሰላም ምንድነው?” በሚል ርዕስ ለፃፍኩት መጣጥፍ ከደረሱኝ በርካታ አስተያየቶች ውስጥ “በነካ እጅህ ልማት ምን ማለት እንደሆነ ብትገልጽልን” የሚለው ጥያቄ ለዚህ ጽሁፍ ምክንያት ሆኗል።

ከአሰልቺ የወያኔ ካድሬዎች ክርክሮች አንዱ “ልማታችን፣ ልማታችን” መሆኑ የማውቀውና በራሴም ላይ ከተራ ማሰልቸት በላይ የመብት ጥሰቶች ያደረሰብኝ ጉዳይ ነው። ወያኔ በአገራችን ላይ ላሰፈነው አገዛዝ ተቀባይነት (ligitimacy) ዋነኛ መከራከሪያው “ለኢትዮጵያ ልማትን ያመጣሁ፤ አሁንም በማምጣት ላይ ያለሁ መንግሥት ነኝ። ለወደፊቱም ኢትዮጵያን ለማልማት ከኔ የተሻለ የለም” የሚል ነው። በዚህ ክርክር ውስጥ (1) ከዚህ በፊት በአገሪቱ ውስጥ ልማት የሚባል ነበር አልነበረም፤ (2) እኔ ልማትን እያመጣሁ ነው፤ ሌላውን ቻሉት፤ እና (3) ለወደፊቱም ከኔ የተሻለ ኢትዮጵያን ማልማት የሚችል የሌለ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ሲባል እኔ ለረዥም ጊዜ በስልጣን መቆየት አለብኝ የሚል መልዕክት አለው።

በዚህ ጽሁፍ እነዚህን ሶስቱም መከራከራዎች ውሸት መሆናቸውን ለማስረዳት እሞክራለሁ። ከሁሉ አስቀድሞ ግን “ልማት” በተሰኘው ጽንሰ ሀሳብ ላይ የጋራ ግንዛቤ እንያዝ።

2.የልማት ትርጉም

በዛሬቷ ኢትዮጵያ መብራት ሲቋረጥ፤ ውሀ ሲጠፋ፤ ጤፍ ሲወደድ፤ መንደሮች ሲፈርሱ፤ የመኪና አደጋ ሲበዛ፤ ገበሬዎች ሲፈናቀሉ ሰበቡ ልማት ነው። ማናቸውም ችግር “እድገት ያመጣው ነው፤ ቻሉት” እየተባለ ይታለፋል። ለረሀብ፣ ለጥማት፣ ለበሽታ እና መሰል መጥፎ ነገሮች ልማት ምክንያት ሆኖ ሲቀርብ፤ “መብቴ ይከበርልኝ ብሎ መጠየቅ “በፀረ-ልማትነት” ሲያስከስስ “ለመሆኑ ልማት ምንድነው?” የሚል የጅል አልያም የልጅ የሚመስል ጥያቄ ለማንሳት እንገደዳለን።  ………..

የደቡበ ክልል ሦስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች ከኃላፊነት ተነሱ

ሙስና እንደምክንያት ተጠቅሷል፤ የሥርዓቱ መበስበስ ማቆሚያ አጥቷል!!!

የደቡብ ክልልን ከሚመሩት አራቱ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች መካከል ሦስቱ ከኃላፊነት መነሳታቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡
ለሦስቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መነሳት ከነሐሴ 15 እስከ 19 ቀን 2005 ዓ.ም. ከተደረገው ግምገማ ጋር የተያያዘ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች፣ ለእያንዳንዳቸው መነሳት የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን ያስረዳሉ፡፡ ከኃላፊነታቸው ከተነሱት መካከል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ከሆኑ አንድ ዓመት ያልሞላቸው አቶ ታገሠ ጫፎ ሲሆኑ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ አሰፋና በተመሳሳይ ማዕረግ  የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳኒ ረዲ ናቸው፡፡

የአቶ አለማየሁ አሰፋና የአቶ ታገሠ ጫፎ መነሳት የተጠበቀና ውስጥ ለውስጥ ሲነገር የቆየ መሆኑን፣ ያልተጠበቀው ግን የአቶ ሳኒ ረዲ ነበር በማለት አስተያየት የሰጡት የደኢሕዴን አባልና ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ የክልሉ ባለሥልጣን፣ ሦስቱም ሹማምንት የተገመገሙት በተለያዩ ችግሮች እንደሆነ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡ ‹‹አቶ ታገሠ በአመራር ብቃት ማነስ በተደጋጋሚ ይተቹ እንደነበር ገልጸው፣ አቶ አለማየሁና አቶ ሳኒ ደግሞ አላስፈላጊ ‹‹ኔትወርክ›› በመፍጠር ብልሹ አሠራር በማስፈናቸው ነው፤›› ብለዋል፡፡

በግምገማው የተሳተፉ ምንጮች ደግሞ በተለይ አቶ አለማየሁ ባለፈው ዓመት መጨረሻ አካባቢ በተወከሉበት ዳውሮ ዞን ከፍተኛ ተቃውሞ ሲነሳባቸው የኃይል ዕርምጃ እንዲወሰድ ማድረጋቸው እንደ አንድ ምክንያት መነሳቱን ያስረዳሉ፡፡
በሌላ በኩል የክልሉ የመንግሥት ሠራተኛ የሆኑ አንዳንድ አስተያት ሰጪዎች ለሦስቱም ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከኃላፊነት መነሳት የአመራር ብቃት ማነስ ብቻ ሳይሆን የኪራይ ሰብሳቢነትና የሙስና ችግሮች መኖራቸውን ይገልጻሉ፡፡

በሥነ ሕይወት ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ በዓሣ ዕርባታ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙት አቶ ታገሠ ጫፎ እስከ 2000 ዓ.ም. ድረስ የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ ከ2000 እስከ 2003 ዓ.ም. መስከረም ድረስ ብቸኛው የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የንግድ ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ፣ እንዲሁም ወደ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊነት እስከተዛወሩበት ህዳር 2005 ዓ.ም. ድረስ አራተኛው ምክትል ርዕስ መስተዳድር ሆነው ቆይተዋል፡፡ ከአምስት ዓመት በላይ በኃላፊነት የቆዩበት ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ አንዳንድ ሠራተኞች፣ ‹‹ከአራት መቶ በላይ ሠራተኞች ያሉበትን ቢሮ ሲመሩ አንድም ቀን ሠራተኞችን ሰብስበው አናግረው ችግር የፈቱበት ጊዜ አልነበረም፡፡  ግንኙታቸው ከሥራ ሒደት ባለቤቶች ጋር ስለነበር ዕርምጃም የሚወስዱት ከነዚያ ሰዎች በሚያገኙት መረጃ ብቻ ነበር፤›› በማለት በርካታ ሠራተኞች ሳያውቁዋቸው እሳቸውም የሚያስተዳድሩዋቸውን ሠራተኞች በቅጡ ሳያውቁ መነሳሳታቸውን ይናገራሉ፡፡

Tuesday, September 3, 2013

የአብዮቱ የምፅአት ቀን ምልክቶች! (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)

‹‹በአፍሪካ ትልቁ አምባገነን›› የሚል ተቀፅላ የተሰጣቸው የሊቢያው ኮሎኔል መሀመድ ጋዳፊ እና የግብፁ ሆስኒ ሙባረክ በህዝባዊው እምቢተኝነት ከስልጣን መነሳታቸው በመሰል አገዛዞች ስር ያደሩ ሕዝቦችን ለለውጥ ማነቃቃቱ የሚጠበቅ ነው፡፡ በተለይም ከራሳቸው መንግስት ተኳርፈው አስተማማኝ የዲሞክራሲ ተቋማትን በገነቡ የምዕራብ ሀገራት በብዛት የሚኖሩ ዜጎች ላሏት ኢትዮጵያ ንቅናቄው የፈጠረው ተመሳሳይ መነሳሳት ቀላል ባለመሆኑ ኢህአዴግን ሊወጣው ከማይችለው ቅርቃር ውስጥ ከቶታል፡፡ የዚህ ተጠየቅም ቀድሞ እንዲህ አይነት ችግሮች ሲፈጠሩ ድርጅቱ ‹እሳት ማጥፊያ› ያደርጋቸው የነበሩ አጀንዳዎቹ ያለፈባቸው (Expired) መሆናቸውን ማሳየት ነው፡፡


ሰባቱ ‹‹ቀኖና››ዎች


ስርዓቱ ከሃያ ሁለት ዓመታት በላይ በስልጣን የመቆየቱ ምስጢር ከሁለት ምንጭ የሚቀዳ ነው፡፡ አንዱ የታዘዘውን ሁሉ ያለ ምንም ማንገራገር የሚፈፅመው ጠመንጃ አንጋቹ (መከላከያ ሰራዊት፣ ፌደራል ፖሊስ እና የደህንነት መዋቅሩ) ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ ከፖለቲካው ፍልስፍና የሚወረሱ አጀንዳዎቹ ናቸው፤ ይሁንና ለጊዜው የታጠቀውን ኃይል ወደ ጎን ብለን ስርዓቱ ‹‹የፖለቲካዬ መገለጫዎች›› ብሎ እንደ ቀኖና ይዟቸው የነበሩትን ሰባት ጉዳዮች በደምሳሳው ብንቃኝ የመቃብር አፋፍ ላይ የቆመ ስርዓት ስለመሆኑ የማመላከት አቅም አላቸው ብዬ አስባለሁ፡፡

1. የገጠር ፖሊሲ

ኢህአዴግን የሶስት ፓርቲዎች ግንባር አድርጎ በመመስረቱ ሂደት የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው፣ በሀገሪቱ ከሚገኙ የገጠር ከተሞች ከሽሬ ጋር በሚዋሰነው ‹‹ደደቢት በርሃ›› ላይ የተመሰረተው ህወሓት ሲሆን፣ መስራቾቹም ሆኑ አብዛኛው አባላቱ ከአርሶ አደሩና የገጠር አካባቢዎች የወጡ ናቸው፡፡ የህወሓት የታሪክ ንባብ እንደሚያረጋግጠው ትጥቅ ትግል ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያቶች ሁለት ነበሩ፤ የብሄር ጭቆናን እና የትግራይ አርሶ አደር ለአስከፊ መከራ ተዳርጓል የሚል፡፡

ድርጅቱ ለትግል ካሰለፋቸው አባላቱ ሁለት ሶስተኛው ከእርሻ ሥራ በቀጥታ የተቀላቀሉ ስለመሆናቸው ድርሳናቱ ያወሳሉ፡፡ በወቅቱ በተድበሰበሰ መልኩ የቀረፁት የፖለቲካ ፕሮግራም በመሬትና በብሄር ጥያቄ ላይ የተንጠለጠለ እንደነበር ይታወቃል፤ ይሁንና ከትምህርት ገበታ ተሰውረው፣ በረሃ የገቡት ወጣቶች ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ምናልባትም ‹‹‹መሬት የመንግስት ነው› የሚለው ፖሊሲያችን የሚቀየረው በመቃብራችን ላይ ነው›› ወደሚል ኦሪታዊ የፖለቲካ አቋም (ቀኖና) የተመለሱት የኢትዮጵያ ተማሪዎች የ‹‹መሬት ላራሹ››ን ትግል ጠልፎ ወደስልጣን የመጣው ደርግ፣ ህወሓት በተመሰረተ ልክ በአስራ አራተኛው ቀን የካቲት 25 ቀን 1967 ዓ.ም መሬትን በተመለከተ መሬትን ያራሹ ባደረገው አዋጅ የሰጠው ምላሽና ያገኘው ድጋፍ ሌላ አማራጭ የነፈጋቸው ይመስለኛል (ህወሓት የተመሰረተው የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም መሆኑን ልብ ይሏል) በነገራችን ላይ ለኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች መሬት ከኢኮኖሚ ይልቅ ፖለቲካዊ ጠቀሜታው እንደሚበልጥ በርካታ ማሳያዎች አሉ፡፡

የሆነ ሆኖ ከኢህዴንና ኦህዴድ ጋር ተጣምሮ ኢህአዴግን የመሰረተው ህወሓት በ1983 ዓ.ም ለመንግስታዊ ስልጣን መብቃቱን ተከትሎ ራሱን ‹የኢትዮጵያ አርሶ አደር ነፃ አውጪ› አድርጎ አስተዋውቋል፡፡ በተጨማሪም ‹‹በቅዱስ መፅሀፌ ‹አብዮታዊ ዲሞክራሲ› መርህ መሰረት የቀመርኩት›› የሚለውን ‹‹ገጠርን እና ግብርናን ማዕከል ያደረገ የልማት እስትራቴጂ›› በፖሊሲ ደረጃ ከማውጣቱም በተጨማሪ በተለያየ ጊዜ ባሳተማቸው መጻህፍት እና ጥናቶች የአርሶ አደሩን ህይወት በከፍተኛ ደረጃ እየቀየረው እንደሆነ ለማስረዳት ሞክሯል፡፡ በአናቱም ሀገሪቱ ያላት ሀብት የሰው ኃይልና መሬት መሆኑ ለሚከራከርበት ንድፈ-ሃሳብ ቅቡልነት አስተዋፅኦ ያደረገ ይመስለኛል፡፡

በቀዳሚዎቹ ሶስት ሀገር አቀፍ ምርጫም አፅንኦት ሰጥቶ የተሟገተው ‹‹ለአርሶ አደሩ የምታገል ፓርቲ ነኝ›› እና ‹‹አርሶ አደሩ ይደግፈኛል›› የሚል እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ይሁንና በምርጫ 97 በከተሞች በደረሰበት ያልተጠበቀ ሽንፈት እንዲያ ከበሮ የደለቀለትን ‹‹ገጠርና ግብርናን ማዕከል ያደረገ የልማት ስትራቴጂ›› ለድንገቴ (አልቦ ቅድመ-ዝግጅት) ለውጥ ይዳርገ ዘንድ መገደዱን የሚጠቁሙ ምልክቶች እየታዩ ነው (የትራንስፎርሜሽን እቅዱ፣ የአባይ ግድብ፣ የመከላከያ ኢንዱስትሪ እና የኮንዶምኒየም ቤቶች ግንባታ የተበጀተላቸው ባጀት ስርዓቱ በአዋጅ የነገረንን የገጠር ልማት ፖሊሲ፣ ያለኮሽታ መቀየሩን ያመላክታል) የአብዮቱን የምፅአት ቀን ካቃረቡት ዋነኛ ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡

2. የብሔር ጥያቄ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝየህወሓት መስራቾች በርሃ ለመግባት ሌላኛው ዋና ምክንያት ‹‹ነፃ የትግራይ ሪፕብሊክ››ን ለመመስረት ቢሆንም በጊዜው በአቅራቢያቸው የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ ይህንን ሴራ ኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነትን ለሚያስቀድመው የአካባቢው ህዝብ በማጋለጥ ትልቅ የፖለቲካ ኪሳራ ስላደረሰባቸው የ‹‹ነፃነት›› ጥያቄያቸውን ወደ‹‹የብሄር ጭቆና›› እንዲቀይሩ መገደዳቸውን በጉዳዩ ዙሪያ የተዘጋጁ በርካታ ድርሳናት አጋልጠውታል፡፡ ከድርጅቱ በተለያዩ ምክንያቶች የወጡ የአመራር አባላትም በፃፏቸው ‹ገድሎች› እንደአተቱት ከዚህ በኋላ ነው ‹‹በሀገሪቱ የአንድ ብሄር የበላይነት ነግሷል›› የሚለው ተረታ ተረት በማርክሲዝምና ሌኒንዝም አስተምህሮ ተተንትኖ በማጎን የድጋፍ መቀስቀሻ የተደረገው፡፡ የሆነ ሆኖ ለህወሓት መደርጀት ዋናው ምክንያት ተጋኖ የተቀነቀነው የጎጠኝነት ፕሮፓጋንዳ ሳይሆን፣ የወታደራዊው ደርግ ጭካኔ የተሞላበት ጭፍጨፋና አፈና ያስመረረው በሙሉ በቅርብ ያገኘውን የፋኖዎች ድርጅት መቀላቀል መምረጡ እንደነበር ከጊዜው ንባብ መረዳት ይቻላል፡፡

ከድል በኋላ ኢህአዴግ የቀድሞውን ‹‹አሀዳዊ መንግስት›› በብሔር ላይ ወደ ተመሰረተ የ‹‹ፌደራል መንግስት›› ያስቀየረኝ መግፍኤ ‹‹በኢትዮጵያ አስከፊ የብሄር ጭቆና መንበሩ ነው›› የሚለው መከራከሪያውን ዛሬም ድረስ እንደ በቀቀን ሲደጋግመው ይደመጣል፡፡ የግንቦት ሃያ ድልን ተከትሎ ሀገሪቱን የአፍ መፍቻ ቋንቋን መስፈርት ባደረገ ቀመር በዘጠኝ ክልላዊ መንግስት እና በሁለት ራስ ገዝ ከፍሎ ማስተዳደሩ ለብሄር ጭቆና የማያዳግም መፍትሄ ቢያስመስለው፣ ዛሬም ድረስ በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው በሰላማዊ መንገድ ከሚታገሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል አርባ አራቱ ‹‹የብሄራችን ጥያቄ ገና አልተመለሰም›› በሚል ሀቲት በብሄር የተደራጁ መሆናቸው፤ በኦሮሚያ፣ በሶማሊያ እና ጋምቤላን መሰል አካባቢዎች ደግሞ ጠመንጃ ያነሱ የብሄር ድርጅቶች መኖራቸው ስርዓቱ በብሄር ጥያቄ ረገድ የታሪክ ፈተናን ማለፍ እንደተሳነው መረዳት ይቻላል፡፡

በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የብሄር ጥያቄ ‹ዳግም ላይነሳ መልስ አግኝቷል› ትርክት ምፀት የሚሆነው በሀገሪቱ ከሚገኙ ክልሎች በብዙ እጥፍ ያነሰ የህዝብ ቁጥር ያለው ሐረሪ፣ የኢህአዴግ አጋር የሆነው ‹‹የሐረሪ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት-ሐዲድ››ን ጨምሮ ‹‹የሐረሪ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ-ሐሕዴፓ›› እና ‹‹የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ-ሐብሊ›› የተሰኙ የፖለቲካ ድርጅቶች መኖራቸው ነው (በአፋርም አራት ህጋዊ የፖለቲካ ድርጅቶች አሉ) እነዚህ እውነታዎች ለስርዓቱ ክሽፈትና የአብዮቱ የምፅአት ቀን በጣም የተቃረበ ለመሆኑ በቂ ምልክቶች ናቸው፡፡

3. የኢኮኖሚ ዕድገት

ኢህአዴግ ስልጣን ላይ በወጣበት የመጀመሪያዎቹ ዓመታት የቀድሞ ሊቀ-መንበሩ ‹‹ህዝባችን በቀን ሶስቴ እንዲበላ እናደርጋለን›› ብሎ በአደባባይ ቃል መግባቱም ሆነ ‹‹በአጭር ጊዜ ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ያቆመኛል›› በሚል ሽፋን ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን የደፈጠጠበት የ‹‹ልማታዊ መንግስት›› ጩኸቱ አለመሳካት ሌላኛው የአደባባይ ተቃውሞን የሚጋብዝ ነው፡፡ የስራ አጥ ቁጥር አለቅጥ መጨመር እና የዋጋ ንረትን መቆጣጠር አለመቻሉም የምፅአት ቀኑን መቃረብ አብሳሪ ‹ሰይጣን› ከአንዳች ሸለቆ መቀሰቀሱ አይቀሬ ነው፤ የዶ/ር መረራ ጉዲና ‹‹የሚበላውን ያጣ ህዝብ መሪዎቹን ይበላል›› ትንቢትም የሚያመላክተው ይህንኑ ነው፡፡

በሀገሪቱ ከፍተኛ ተከታይ ካላቸው ዋነኛ ኃይማኖቶች መካከል እስልምና አንዱ ነው፡፡ እንደኃይማኖቱ ልሂቃኖች ምስክርነት ኢህአዴግ የእምነቱን ተከታዮች መብት ለማክበር ከቀድሞ አገዛዞች የተሻለ ውጤት አለው፡፡ ይሁንና በምትኩ ከምዕመኖቹ ያገኘው ጠንካራ የፖለቲካ ድጋፍ ብቻውን ያረካው አይመስልም፡፡ ምክንያቱም ከተባባሪዎቹ የመጅሊስ መሪዎች ጋር በመመሳጠር ኃይማኖቱን ‹አጋር ፓርቲ› አድርጎ እስከ መቁጠር ደርሷልና፡፡