Monday, July 1, 2013

ኢትዮጵያውያኑ በአላሙዲ የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ተቃውሟቸውን አሰሙ

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል በሜሪላንድ ለ30ኛ ዓመት እያደረጉ ሲሆን በሌላ በኩል በአላሙዲ ስፖንሰር የተደረገው በRFK ስታዲየም ዲሲ በተመሳሳይ ቀን ተጀምሯል። በሜሪላንዱ የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የታደሙ ሲሆን አላሙዲ ስፖንሰር ባደረገው የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ደግሞ ጥቂት የወያኔ/ኢሕ አዴግን ሥርዓት የሚደግፉ ሰዎች ተገኝተዋል። ይህን አላሙዲን ስፖንሰር ያደረገውን ዝግጅት በመቃወም በስታዲየሙ ደጃፍ የተቃውሞ ሰልፍ ሲያደርጉ የዋሉት ኢትዮጵያውያን “የአላሙዲ የደም ገንዘብ እይደልለንም” ሲሉ ተሰምተዋል።

አላሙዲ እጁን ከሰሜን አሜሪካው ስፖርት ፌስቲቫል ላይ እንዲያነሳ የጠየቁት ሰልፈኞቹ በተለይ አላሙዲ የስር ዓቱ ደጋፊ በመሆኑ እርሱን ብቻ የሚጠቅም የኢኮኖሚ ስርዓት በሃገሪቱ መዘርጋቱንም ሰልፈኞቹ በተቃውሟቸው አሰምተዋል።
ለ30 ዓመት የቆየውን ፌዴሬሽን ለመገንጠል አስበው ያልተሳካላቸውን አሁን በአላሙዲ ስፖንሰር የሚደረጉትን ግለሰቦች ሰልፈኞቹ “ተጠያቂ ናችሁ” ሲሉ የተሰማ ሲሆን፤ በተቃውሞ ሰልፉ ላይ በኢትዮጵያ እየደረገ ያለውን የሰብ አዊ መብት ጥሰት በማስታወስ ከወያኔ ጋር ተባብረዋል ያሏቸውን ሰዎች ስም በመጥራት አውግዘዋቸዋል። አላሙዲ በኢትዮጵያ የወሰደውን የመሬት ቅርሚትና በዚህም መሬት ላይ ያገኘውን ገንዘብ “የደም ገንዘብ” ሲሉ የገለጹት ሰልፈኞቹ በቀጣይም የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያደርጉ ታውቋል።

በዋሽንግተን በአላሙዲ ስፖንሰርነት የተዘጋጀው የስፖርት ፌስቲቫል በሰው እጥረት ድርቅ መመታቱን የታዘቡት አስተያየት ሰጪዎች “አላሙዲ ከፍሎ ከሌላ ስቴት ያመጣቸው ሰዎች ሳይቀሩ የርሱን ፌስቲቫል በመተው ወደ ኢትዮጵያውያኑ የሜሪላንድ ዝግጅት መምጣጣቸውን” ጠቁመዋል።

ከሲያትል በአላሙዲ ገንዘብ ሆቴልና የአየር ትኬት ተቆርጦልኝ ነው የመጣሁት ያለው አንድ አስተያየት ሰጪ “አላሙዲ ከኢትዮጵያ የወሰደውን ገንዘብ በዚህ በኩል ላካክሰው በሚል ነው በነፃ ሲቆርጡልኝ እሺ ብዬ እዚህ ከመጣሁ በኋላ በሜሪላንዱ የመክፈቻ ዝግጅት ላይ የተገኘሁት” ሲል ተናግሯል።

Source: Zehabesha.com

No comments:

Post a Comment