- የአውሮፓ ልኡክ ቡድን ቃሊቲን እንዳይጎበኝ ትእዛዝ ያወረደው ደብረጺሆን ነው::
- በረከትን እና አዜብን ከነቡድናቸው በሙስና ለመጥለፍ ታቅዶ ነበር::
ወያኔ ለሁለት የተከፈለው ቡድን በአቶ ስብሃት በኩል ያለው በሃገር ቤት ያሉትን ወታደሩን እና ደህነንቱን በድጋፍ መልክ የያዘ ሲሆን የነበረከት ቡድን ደሞ አስተዳደራዊ ባለስልጣናትን እና የውጪ ሃይሎችን የሙጥኝ ብሏል:: በተለያየ ጊዜ የነበረከት ቡድን ቡድን ሃሳብ ለማስቀየር ሲሰራ የነበረው እና የሞከረው የሳሞራ የኑስ የስብሃት ደጋፊ መሆኑ ታውቋል::
የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ የበረከት እና የኣዜብ ቡድን የመንግስት ቁልፍ መዋቅሮችን ለመቆጣጠር እያደረገው መፍጨርጨር እና በአቶ ስብሃት ነጋ እና በአቶ አባይ ጸሃዬ ጥምር አመራር በሃገሪቱ ህግ እና ባለስልጣናት ላይ እያደረገ ያለው ጫና እና ተጽእኖ አነጋጋሪ እየሆነ መቷል::
የአቶ ስብሃት ቡድን የመረጃ ባለስልጣኑን ደብረጽዮን እና የስለላ መዋቅር አናት የሆነውን ጌታቸውን በመያዝ በሃገሪቱ አስተዳደራዊ ሂደቶች ላይ ከፍተኛውን ሚና እየተጫወቱ ሲገኙ በአሁኑ ወቅት ሃይለማርያም ምንም ምርጫ ስለሌለው በቅርብ እየተከታተለው የሚገኘውን የደብረጽዮንን ትእዛዝ እያስፈጸመ ሲሆን ይህ የሚያሳየውበሃገሪቱ ላይ እየተካሄደ ያለውን ቡድናዊ አምባገነነት ስብሃት እየመራው መሆኑን ይጠቁማል::
በወያኔ መዋቅር ውስጥ በከፍተኛ ፍርሃት ባለስልጣናት የሚመለከቷቸው እነ አቶ ስብሃት ነጋ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ አማካሪ ሆኖ የተሾመውን በረከት ስምኦንን በፍርሃት ወጥመድ ውስጥ በመክተት ከጨዋታው ውጭ እያደረጉት ሲሆን የስብሃት ቡድን እየሰራ ያለውን ስራ ተከትሎ በሁለቱ ጎራዎች መካከል ከፍተኛ የሆነ የመዘላለፍ እና የመዛዛት ሁኔታዎች እስከመከሰት መድረሱ ታውቋል::
የስብሃት ነጋ ቡድን በሃገሪቱ መንግስትን እያሯሯጠ መምራቱን ተከትሎ እና በሃገሪቱ ህጎች ላይ ተጼኖ መፍጠሩን መረጃው የደረሳቸው የአውሮፓ ህብረት እና አምሬሪካ ጉዳዩ እንዳሳሰባቸው በደህንነት መዋቅሮቻቸው በኩል ለወያኔ አስታውቀውታል::ከታማኝ ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው አቶ በረከት ስምኦን በህወሓት ውስጥ ያሉትን እና ጠንካራ ስልጣናቸውን ተጠቅመው አደገኝነታቸውን በህግ አና በመንግስትን ላይ ለመጫን እየተደረገ ያለውን ሁኔታ ለሃያላኖቹ በዝርዝር መናገራቸው ታውቋል::ይህ ቢሆንም አብዛኛው ወታደራዊው መኮንን ከስብሃት ነጋ ቡድን ጎን በመሰለፉ የበረከት ቡድን እየተንቸራተተ እና እየተሸረሸረ መሄዱን ምንጮቹ ሲጠቁሙ ተሰሚነቱ መውረዱንም አክለው ገልጸዋል::
የበረከት ስምኦን ቡድን አስደንጋጭ የሆነበት ሌላው ጉዳይ የወይዘሮ አዜብ መስፍን የአዲስ አበባ ከንቲባነት ህልም በደብረጺሆን ትእዛዝ ሃይለማርያም ደሳለኝ እንደማይሰጣት መናገራቸውን ተከትሎ ሲሆን እንዲሁም ባለፈው ሰሞን ወደ አዲስ አበባ የመጣው የአውሮፓ የዲፕሎማቶች ልኡክ ማቅ አልብሰው እንደደብረጺሆን ከላኩት በኋላ መሆኑን ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል::በአሁኑ ወቅት የአሜሪካን እና የአውሮፓ መንግስታት በሕወሃት እየተካሄደ ያለውን ጉዳይ ከሽብርተኝነት ለይተው እንደማያዩት እና ይህ እየተደረገ ያለው የሰብኣዊ መብት ጥሰት እና አላስፈላጊ ሁኔታዎች ሃገሪቷን ወደ አደገኛ አቅጣጫ እየመራ መሆኑን የሃገሪቱ አምባገነናዊ መርሆዎች መለወጥ እና መሻሻል ያለባቸው መሆኑን አስፈላጊውን ስልኩለር ማስተላለፋቸው ታውቋል::የሕወሓት ታጋዮች በዚሁ የሚቀጥሉ ከሆነ አገሪቷ ነገ ወደማትወጣበት አዘቅት ውስጥ እየገባች እንደምትገኝ መረጃዎች እንዳላቸው እነዚህ መንግስታት አክለው አስቀምጠዋል::አቶ ሃይለማርያም ደሳለን ከዚሁ ማስጠንቀቂያ ጋር ተያይዞ በአጣብቂኝ ውስጥ የገቡ ሲሆን እንደምንጮቹ ዘገባ ከሆነ የተመረጡበትን ጊዜ ካጠናቀቁ በኋላ በስልጣን መቀጠል እንደማይፈልጉ ሲናገሩ ተደምጠዋል::
ባለፈው ሰሞን የአውሮፓ የልኡካን ቡድን የቃሊቲን እስር ቤት ለመጎብኘት በቦታው ደርሶ መከልከሉ ሲታወቅ ይህ ትእዛዝ የወረደው ካቶ ስብሃት እና ደብረጺሆን መሆኑን የእስር ቤቱ ባለስልጣናት ለእነዚህ ቡድኖች ቅርብ የሆኑ ናቸው::በፖለቲካው ቋንቋ እንደሚባለው ዋናው የስልጣን ሃይሉ ያለው በቦታው በተቀመጠው የበላይ አካል ሳይሆን በዙሪያው በሚሽከረከረው እና በተከበበው ሃይል እጅ ላይ እንደሆነ ሲያሳይ የአቶ ስብሃት ቡድን ከጀርባ ሆኖ የመንግስትን ስራዎች እየሰራ መሆኑ በእነ በረከት በኩል ስጋት በመፍጠሩ ወታደራዊውን ሃይል ከጎናቸው ማሰለፋቸው እነበረከት ደሞ ሃያላኑን ከጎናቸው ማሰለፋቸው ነገሩን አክርሮታል::ይሪትዮፕያ ህዝብ የበይ ተመልካች ነው::
በቅርብ ጊዜ በሙስና ላይ የተጀመረው ዘመቻ የነበረከትን ቡድን ለማዳከምእና ለማጥመድ በስብሃት ቡድን ተጠንቶ የተደረገ ሲሆንእንዲሁም ባለፈው አቶ ስብሃት በሚዲያ ቀርበው መቶ ሺህ የበላው አስር ሺህ የበላውን ያሳድዳል በማለት የተናገሩት ከዚህ በመከተል በረከትን እና አዜብን ቡድን በሙስና ለማጥመድ የማስጠንቀቂያ ደውል መሆኑ ታውቋል:: ሁኔታዎችን የተረዳች የምትመስለው አዜብ ነገሩ ያሳሰባት ሲሆን የተባለችውን ከማድረግ ውጭ ሌላ እንቅስቃሴ ለማድረግ ብትሞክር እድሜዋ እንደሚያጥር በቂ መረጃዎች የደረሷት ሲሆን አርፋ መቀመጥን መርጣለች::
እያየነው እንዳለነው ከሆነ አላስፈላጊ ናቸው ተብለው የታመነባቸው የወያኔ አባላት ከስልጣን ባቡር እየተንጠባጤቡ ሲሆን ይህ ከመርከቡ የማውረድ ሴራ የሚቀጥል ሲሆን የነበረከት ቡድን የሆኑ አጋሮችን በተለያየ ምክንያት ማሰናበት አንዱ ስራው ነው::ባለፈው የበረከት ወዳጅ የሆነው የወያኔው ሴኩቱሬ ከስልጣኑ መባረር ሳይንሰውበትምህርት ሽፋን ከሃገር እንዲወጣ ተደርጓል::ወያኔ ተከፋፍሏል:: የድርጀቱ ኢ ዲሞክራሲያዊ መሆን ይህን ችግር የፈጠረ ሲሆን የፖለቲካ መልካም ጎኖች አለመኖር ለጥቅም መገዛት የስልጣን ጥማት ሽብር መንዛት በአባላቱ መካከል ከፍተኛ ልዩነት እንዲፈጤር ያደረገ ሲሆን ለውጥ እንዲኖር የሚተጉ አባላት ቁጥር ማነስ ችግሩ እንዲባባስ አድርጎታል::
ምንጭ፡ ምንሊክ ሳልሳዊ ብሎግ
No comments:
Post a Comment