ሰሞኑን ተጠናክሮ የቀጠለውን የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎችን ጥያቄ አልቀበል ያሉትና ሲኖዶሱ የወሰነውን ውሳኔ ለማስፈጸም ዝግጁ ያልሆኑት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን አባ ጢሞቴዎስ ወዳጃቸውን ፓትርያርክ ማትያስን ደብዳቤ በማጻፍ ኮሌጁ እንዲዘጋና ተማሪዎችም ግቢውን እንዲለቁ፣ ምረቃም እንደማይኖር እንዲደረግ ትእዛዝ ማስወጣታቸው ተሰማ፡፡ ደብዳቤው ተግባራዊ መሆኑ ግን አጠራጣሪ ሆኗል፡፡ ፓትርያርኩ የጻፉት ደብዳቤ ዛሬ የተሰበሰበውን ቋሚ ሲኖዶስ ያጨቃጨቀ ሲሆን በዋናነት ኮሌጅን መዝጋት የሚያበቃ ችግር አልተፈጠረም፡፡ የተፈጠረ ቢሆንም እንኳ በሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ እንጂ በእርስዎ ደብዳቤ ኮሌጁ ሊዘጋ አይችልም የሚል ጠንካራ ተቃውሞ ከጳጳሳት በኩል ቀርቧል፡፡ በተለይም አባ ሉቃስ ደብዳቤውን ከተቃወኑት መካከል ናቸው፡፡ ይህን ተከትሎም አባ ጢሞቴዎስ በአባ ሉቃስ ላይ የስድብ ውርጅብኝ ያወረዱባቸው ሲሆን “አንተ ሰዶማዊ አዋሳ ላይ ስታሳድም የኖርህ ባለፈውም ቀሚስ አሰፍተህ ፓትርያርክ እሆናለሁ ብለህ ስታሳድም አልነበርህም?” ማለታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በአጸፋውም አባ ሉቃስ “አንተ መሃይም እውር መቼም ከትምህርቱ የለህበት ለዚያ ነው ኮሌጁ ይዘጋ የምትለው” ማለታቸውን ምንጮቻችን አክለዋል፡፡ ይህን ዱላ ቀረሽ መዘላለፍ ተከትሎ ፓትርያርኩ ቆመው “ኧረ ስለ ማርያም ብላችሁ ተዉ” ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
“ባለቤቷን የተማመነች በግ…” እንደሚባለው ከፓትርያርክ ፓትያስ ጋር ባላቸው የጠበቀ ወዳጅነት ተመክተው ከሚገኙበት የጤንነት ሁኔታ የማየት ችግር አንጻር ጡረታ መውጣት ያለባቸው አባ ጢሞቴዎስ ኮሌጁን በርስትነት ይዘው ለዛሬዪቱም ቤተክርስቲያን ተስፋ የሆኑትንና የነገዪቱም ቤተክርስቲያን ወራሾች የሆኑትን የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎችን በማባረር ኮሌጁን የሚያዘጋ ደብዳቤ ማጻፍ ለቤተክርስቲያኒቱ ትልቅ ውድቀት እንደሆነ አያጠራጥርም፡፡ ደብዳቤውን የጻፉት ፓትርያርክም በምን መነሻነት ይህን እንዳደረጉ ግራ አጋቢ ሆኗል፡፡ ምንም ወዳጅ ቢሆኑ ወዳጅነት የሚገለጸው በሌላ በግል ጉዳይ እንጂ ቤተክርስቲያን ላይ ጥቁር ጠባሳ የሚጥልና ራሳቸውንም ትዝብት ውስጥ የሚከት ይህን መሰል ደብዳቤ በመጻፍ መሆን አልነበረበትም የሚሉ አሉ፡፡
እንደአንዳንድ ተንታኞች የቅድሰት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች በፓትርያርኩ ጥርስ ውስጥ የገቡት ፓትርያርኩ ወዳጄ አባ ጢሞቴዎስ ለምን ተነኩ በሚል ብቻ ሳይሆን ለፕትርክና እጩነት እኔን ትታችሁ አባ ሳሙኤልን ደግፋችኋል በሚል ሳይሆን እንዳልቀረ ይናገራሉ፡፡ ኮሌጁንና ተማሪዎቹን የመናፍቃን መፈልፈያ ሆኗል ሲሉ ይተቹ የነበሩት የማቅ ብሎጎችም አሁን ተማሪዎቹን ደግፈውና ቀድሞ ይደግፏቸው የነበሩትን አባ ጢሞቴዎስን እየተቹ መጻፋቸው ደግሞ ምን አይተው ይሆን እያሰኘ ነው፡፡
ለተማሪዎቹ የአካዳሚክ ነጻነት ጥያቄዎች አዎንታዊ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ለጥያቄዎቹ ሌላ መልክ በመስጠት የመማር ማስተማሩን ሂደት ሲያስተጓጉሉ የቆዩት አባ ጢሞቴዎስና አስተዳደራቸው ኮሌጁን በመዝጋትና ተማሪዎቹን በማባረር መፍትሄ የሚያመጡ መስሏቸው ከሆነ እጅግ ተሳስተዋል የሚሉት ምንጮች ችግሩን ከስር አጣርቶ ተገቢው ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በወዳጅነት ምክንያት በጭፍን ደብዳቤ ጽፎ ኮሌጅን ያህል ነገር መዝጋት ከበድ ያለ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል ይላሉ፡፡ የቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ተማሪዎች አሉብን የሚሏቸውን ችግሮች ማዳመጥና ተገቢውን መፍትሄ መስጠት ወቅቱ የሚጠይቀው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡

ምንጭ፡ ጎልጉል ጋዜጣ
No comments:
Post a Comment