ከፍተኛው ህገ መንግስታዊ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት የነበሩት አድሊ መንሱር ጊዚያዊ የግብፅ ሽግግር መንግስት ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሃላ ፈፀሙ፡፡
ለአራት ቀናት የዘለቀውን የግብጽ ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ወታደራዊ ሀይሉ ከስልጣን ባወረዳቸው ሙሃመድ ሙርሲ ምትክ ሀገሪቱን በጊዚያዊነት ይመራሉ፡፡
ቃለ መሃላ የፈጸሙት አዲሱ ፕሬዝዳንት አድሊ መንሱር ከአራት ቀን በፊት በፕሬዝዳንት ሙርሲ የግብጽ ከፍተኛው የህገ መንግስት ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ነበር የተሾሙት፡፡
አድሊ መንሱር ቃለ መሃላ በፈጸሙበት ወቅት በግብጽ መረጋጋትን ለመፍጠርናሽግግሩ የተቃና እንዲሆን በትጋት እሰራለሁ ብለዋል፡፡
የሽግግር ጊዜ ፕሬዝዳንቱ በአጭር ጊዜም ምርጫ ለማካሄድ እንደሚሰሩ የቢቢሲና አልጀዚራ ዘገባ ያስረዳል፡፡
No comments:
Post a Comment