በኢትዮጵያ ሀገራችን የአገር አንድነት ከተናጋና የዜጎች መብት ከተደፈጠጠ አነሆ 22 ዓመታትን አስቆጥረናል። ዜጎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ሀብትና ንብረት እንዳያፈሩ አስቸጋሪ የሆነ ሁኔታ ተፈጥሮባቸዋል። ካፒታልና እውቀት ከቦታ ቦታ በመዘዋወር ዜጎችን እንዳያገለግሉ በክልል ድንበር ታግደዋል። ዜጎችም ለብዙ ዓመታት ከሰፈሩበት ቦታ አገርህ አይደለም በሚል ሰበብ የዘር ግንዳቸው መነሻ ወደሆነው ክልል እንዲሜለሱ ይገደዳሉ። በዚሁ መሰረትም በዚሁ ዓመት ብቻ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የአማራ ልጆች ከቤንሻንጉልና ከጉራፈርዳ በኢሀዴግ ካድሪወች ተፈናቅለዋል። ሃብት ንብረታቸውም ተዘርፈዋል። የአፋርና የጋንቤላ ልጆችም መሬታቸው ለባዕድ ስለተሸጠባቸው የመኖር መብታቸው ተገፏል፣ ለስደትም ተዳርገዋል።
ዝርዝሩን ያንቡ የቀረበውን ሊንክ በመጠቀም http://welkait.com/wp-content/uploads/2013/08/mead130824.pdf
No comments:
Post a Comment