እኛ የምንታገለው ነፃነታችንን ለማረጋገጥ እንጂ የተቃዋሚ መሪዎች ለመደገፍ (ወይ ለመቃወም) አይደለም። ትግላችን ዓላማ መሰረት ያደረገ ነው። ዓላማችን ነፃነታችን ነው። የነፃነት ዓላማና ትግል ምን ግዜም አይሞትም።
የተቃውሞ መሪዎች ሊሳሳቱ ይችላሉ፤ ሊቀየሩ ይችላሉ፣ ሊያፈገፍጉ ይችላሉ። ግን የነፃነት ዓላማችን ህያው ሁኖ እስከተገኘ (ነፃነት እስከፈለግን) ድረስ እኛ በመስመራችን አለን።
እኛ የምንቃወምበት ምክንያት ነፃነት ለሰው ልጅ እንደሚያስፈልግ ስለምንረዳ እንጂ መሪዎች ለመቀየር ስለምንፈልግ አይደለም። ስለዚህ የተቃውሞ መሪዎች የፈለጉትን መንገድ ቢከተሉ የኛ የነፃነት መንገዳችን ሊያሰናክል አይችልም።
መሪዎቻችን በዓላማቸው ቢፀኑ መልካም ነው፤ ካልሆነ ደግሞ እኛ ራሳችን ነፃነታችንን እናስከብራለን። ስለዚህ የአንዳንድ የተቃውሞ መሪዎች ንግግሮች እያመጣቹ ትግላችንን ለማደናቀፍ አትሞክሩ (ወይ የሚደናቀፍ አይምሰላቹ)። የኛ ድጋፍ ለነፃነት ጉዛችን እንጂ ለመሪዎች የተሰጠ ውለታ አይደለም።
ነፃነታችንን ለመጎናፀፍ እንጂ የሰው ገዢዎች ለመቀየር አልተነሳንም። ስለዚህ ትግላችን ህያው ነው። (በመሪዎቻችን የተፈጠረ አዲስ ባህሪይ የለም)።
ድጋፋችን በፖለቲካ መሪዎቻችን ትከሻ የተንጠለጠለ የዛፍ ቅጠል አይደለም። የድጋፋችን መሰረት የነፃነት አምሮታችን ነው፤ ይህን ሊቀለብስ የሚችል ሃይል ከቶ ሊኖር አይችልም።
Freedom is the cause.
It is so!!!
No comments:
Post a Comment