Friday, June 28, 2013

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄን እንርዳ!


ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ “Solidarity Movement for a New Ethiopia” (SMNE) “ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ነጻ ሊሆን አይችልም” እና “ከጎሳ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ እንስጥ” በሚል መሪ መፈክር በአቶ ኦባንግ ሜቶ እየተመራ ድምጻቸው ለታፈነው ኢትዮጵያውያን ድምጽ መሆኑን ቀጥሏል።

በኢትዮጵያ የህወሀት/ኢህአዴግ ቡድን ዜጎችን አያት ቅድመ አያቶቻቸው ካወረሷቸው ቀዬ እያፈናቀለ ግልጽነት በሌለው መልኩ መሬታቸውን ለአረብ እና ህንድ ቱጃሮች በርካሽ ሲቸበችብ፣ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄና ኦባንግ ሜቶም በበኩላቸው አልተኙም። ዓለም በደሀውና ድምጹ በታፈነው ኢትዮጵያውዊ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ እንዲገነዘብ ማድረግ ችለዋል። ኦባንግ ሜቶ ወደ ህንድ ሀገር ጭምር በመጓዝ በታላላቅ የህንድ ሚዲያዎች ስለጉዳዩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አቶ ኦባንግ ሜቶ አለምን እያቆራረጡ ኢትዮጵያውያን ድረሱልን ያሉበት ቦታ ሁሉ ይገኛሉ። አስከፊውን የአፈና ስርዓት ሸሽተው በጥገኝነት በሚኖሩባቸው ሀገራት ተጽእኖው ሲበረታባቸው አቶ ኦባንግ ሜቶ ዋስ ጠበቃ ሆነው ይከራከራሉ።

“ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ” በጥቂት ኢትዮጵያውያን የገንዘብ ድጋፍ እየታገዘ ይህን ሁሉ ማድረግ ከቻለ። ሁላችንም የአቅማችንን ብንረዳ ደግሞ ምን ያህል የተሻለ ስራ ሊሰራ እንደሚችል አያጠያይቅም።



የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ (ECADF) በሀገራችን ኢትዮጵያ ለውጥ ለማምጣት የሚተጉትን ሁሉ ይደግፋል ያበረታታል።

ስለሆነም “ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ” ማጠናከሪያ የሚውል የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ ጀምረናል። ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የበኩላችሁን ታደርጉ ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን።

ማሳሰቢያ፣ ገንዘቡ የሚላከው በቀጥታ “ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ” የባንክ አካውንት ነው። ንቅናቄዉ ለዚህ እንቅስቃሴ ሙሉ እውቅና ሰጥቷል። ዘመቻችን ምን ያህል የተሳካ እንደሆነ ለመገምገም ያመቸን ዘንድ ገንዘቡን ከላኩ በሗላ በዚህ ኢሜል አድራሻ ያሳውቁን “admin@ecadforum.com”

እናመሰግናለን!

No comments:

Post a Comment